Get Mystery Box with random crypto!

የህንድ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ 'ማለቂያ የሌለው ሀዘን' ሲሉ ገልፀውታል ትናንት በህንድ ከፍተኛ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

የህንድ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ
"ማለቂያ የሌለው ሀዘን" ሲሉ ገልፀውታል

ትናንት በህንድ ከፍተኛ የባቡር አደጋ የደረሰ ሲሆን ከ260 በላይ ንፁሀን የሞቱ ሲሆን ከ1000 በላይ በሚሆኑት ደግሞ ከባድና ቀላል አደጋ ደርሶባቸዋል።

ይህንን አደጋ በማስመልከት ፓትርያርኩ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በደረሰው አደጋ ከልብ ማዘናቸውን በመግለጽ ለሞቱት ነፍሳቸውን ይማር ለተጎዱት ደግሞ ፈጣሪ ምህርት እንዲያደርግላቸው እንፀልያለን ብለዋል።

ፓትርያርኩ "ማለቂያ የሌለው ሀዘን" በሚል በገለፁበት መልዕክታቸው ህንዳውያንና መላው ዓለም በዚህ አደጋ ለሞቱትና ለተጎዱት ሁሉ በፀሎት እንዲያስቧቸው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ለሞቱት ነፍስ ይማር ለተጎዱት ምህረት ያውርድላቸው

@ortodoxtewahedo