Get Mystery Box with random crypto!

#ብፁዓን አባቶች ጅጅጋ ገቡ። ዛሬ በጅጅጋ ከተማ በገራድ ዊልዋል አየር መንገድ ሲደርሱ ደማቅ አ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#ብፁዓን አባቶች ጅጅጋ ገቡ።

ዛሬ በጅጅጋ ከተማ በገራድ ዊልዋል አየር መንገድ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው በቅዱስ ሲኖዶስ አዲስ የተሾሙት ብፁዓን ኤጲስ ቆጶሳት እና ብፁዓን አባቶች ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ
የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ
የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ
ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ
የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ
ብፁዕ አቡነ ገሪማ
የጌዴኦ አማሮ ና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ
በምስራቀ ፀሀይ ቅድስ ኪዳነምሕረት እና ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ሲገቡ የቤተክርስቲያን ሊቃውት ካህናት አባቶች የአብያተ ቤተክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ሀላፊዎች እና ሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ማኀበራት እና ምእመናን በመገኘት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

መረጃ ምንጭ :አማኑኤል የጅጅጋ ወጣቶች መንፈሳዊ ማኀበር

@ortodoxtewahedo