Get Mystery Box with random crypto!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም | ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ተጉዘዋል።

ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አአባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን የሐምሌ 2015 ዓ.ም የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግሥ ለማክበር ዛሬ ድሬዳዋ ከተማ ገብተዋል ።

ዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ,ም ቅዱስነታቸው ድሬዳዋ ከተማ ሲገቡ በአውሮፕላን ማረፊያ እና በመንበረ ጵጵስናው ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የድሬዳዋ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የድሬዳዋ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ካህናትና ምእመናን ደማቅ አቀባበል አድርውላቸዋል።

ቅዱስነታቸው በአቀባበሉ ላይ ለተገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል ።

@ortodoxtewahedo