Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136.56K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 41

2023-02-04 16:19:22
አስቸኳይ

ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ በስናይፐር የታገዘ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል።

የጸጥታ ኃይሉ ፎቅ ላይ በመሆን በቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ወዳሉት ምእመናን በስናይፐር እየተኮሰ ሲሆን በዚህም አንዲት ሴት ተገድላለች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ምእመናንና ምእመናት ቆስለዋል።

ከውጪ በኩልም ሕገ ወጡ ቡድን ብር በመክፈል ያደራጃቸው ቡድኖች ድንጋይ በመወርወር ላይ ናቸው በዚህም የቤተ ክርስቲያኑን በር ሰብረውታል።
5.0K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 15:53:13 #መከራው_ክርስትናዬን_አጣፈጠው ✞

መከራው ክርስትናዬን አጣፈጠው
ስደቱ ማህተቤን አጠበቀው
በሞት መንደር በሀዘን ውስጥ በመከራ
አየውት እግዚአብሔርን ከኔ ጋራ

ክርስትያን ተብለን በክርስቶስ ስም የተጠራነው
በጥልቁ ውስጥም በእግዚአብሔር እንድናምን ነው
ለጥቂት ግዜ ቢበረታብን ስደት ሀዘኑ
አምላክ ግን መውጫ ያዘጋጃል በዚህ ተፅናኑ
#አዝ
በስደት ሳለን ካፋችን ቢደርቅ የፅዮን ዜማ
ከወንዙ አጠገብ ቁጭ ብለን ሰለን ድምፁን ሳንሰማ
በእግዚአብሔር ጊዜ ከባቢሎን ምድር እንለቃለን
መሰንቆአችንን ከአርያም ዛፍ ላይ እናወርዳለን
#አዝ
ደካሞች ሲሉን በስሙ ያን ጊዜ እንበረታለን
ድሆች ስንባል ባለጠጎች እናደርጋለን
በምድር ቅዱስ ህዝብ አድርጎ ለእርሱ ለየን
ጨለማው አልፎ በቸርነቱ ብርሀን አሳየን
#አዝ
ከፀጋ በላይ እንዳንፈተን ይከልለናል
በቁስላችን ላይ የፈውስን ዘይት ያፈስልናል
በጊዜም ቢሆን ያለ ጊዜውም በእርሱ እንፅና
እንኳን ስደቱን ሞቱን ሊገታው ይችላልና

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
5.7K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 15:34:29
የጉራጌ ሀገረ ስብከት ያስተላለፈው መመሪያ
#share
6.2K viewsedited  12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 14:19:31 በሻሸመኔ እና በመላው ምዕራብ አርሲ የምትገኙ ጠንካራ ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በሙሉ ይህንን ከዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ ያልተናነሰ ዘመን በጠንካራ መሠረት ላይ በታነፀው የሃይማኖታችሁ ጥንካሬ በጸሎት ፣ በጾም እና በፍፁም ክርስቲያናዊ ጥንካሬ ራሳችሁን ፣ ቤተ ክርስቲያናችሁን እና ሀገራችሁን እንድጠብቁ ሲሉም ጠይቀዋል።

በመሆኑም ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ፤ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ ቃል በማስተዋል የፌደራል መንግስትና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወገንተኝነታቸውን በማቆም እግዚአብሔር ፍርድ ከመስጠቱ በፊት ንስሐ በመግባት በግፍ የሚፈሰውን የንፁሐን ኦርቶዶክሳውያንን ደም እንዲያስቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል
8.8K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 14:19:31
"አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?" -ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በመንግሥት አካላት የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን አስመልክቶ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤተ ክርስቲያን እና በክርስቲያኖችን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የማሳደድ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል::

በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ እናስከብራለን በሚል በትግራይ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው በማለት ገልጸዋል።

በሻሸመኔ ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው ግፍ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለማጥፋት ከሚደረግ የዘር ጭፍጨፋ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።

አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?
8.5K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 13:20:28
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ ከፖሊስ ጋር በተደረገው ውይይት ሕዝቡ ወደ ቤቱ እንዲመለስ በከተማው የመጣ እንግዳ የለም የሚል ከፖሊሶቹ ሃሳብ የቀረበ ቢሆንም ሀገረ ስብከቱና የሀገር ሽማግሌዎች ሕገ ወጦቹ ግለሰቦች በአንድ ሆቴል ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከቅዱስ ሲኖዶስና ከአባቶቻችን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ግቢያችን ውስጥ ሆነን እየዘመርን እና ወንጌል እየተማርን ቤተ ክርስቲያናችን እንጠብቃለን፡፡

ሀገረ ስብከቱና የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት የመጡት ሕገ ወጥ ግለሰቦች ወደ መጡበት ቦታ ካልተመለሱ ሕዝቡን ማሰናበት አንችልም፣ ሕዝቡም እሺ አይለንም በሚል ለመንግሥት የጸጥታ አካላት ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

ከመንግሥት የመጡ አካላትም ሕዝቡ ከስሜተኝነት እንዲወጣ የሃይማኖት አባቶች እንዲያረጋጉት መመሪያ ሰጥተው መመለሳቸውን ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በንቃት ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቀ በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ የማረጋጊያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል።
9.3K views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 13:19:37
በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት ደረሰ!

በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት የደረሰ ሲሆን በአራቱ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

አብያተ  ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ምእመናን እስካሁን ድረስ በቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳሉ ናቸው። ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የጸጥታ ኃይል አባላት በዱላ እያባረሩ ይገኛሉ።

የከተማዋ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አካላት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ውጪ ላሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ነጠላ በማደል ሻሸመኔ ስታዲዮም ተገኝተው ሕገ ወጡን ቡድን እንዲቀበሉ እያስተባበሩ ያሉ ሲሆን በመኪና ከተማውን እየዞሩ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ሰዓት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ነገሌ ድረስ ያለውን ቦታ ተቆጣጥሯል።

ምንጭ: ተሚማ
8.0K views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 13:18:22
የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ግድያ እየፈጸሙ ነው።
በሻሸመኔ አንድ ወጣት ኦርቶዶክሳዊ ከመንግሥት አካላት በተተኮሰ ጥይት ሰማዕትነትን ተቀብሏል።


ተሿሚዎቹ በእነዚህ ንፁሀን ሰማዕታት ደም ላይ ተረማምደው ቤተ ክርስቲያንን ለመውረር መነሳታቸውን ስናስብ ሃይማኖት አልባነታቸውን እንረዳለን። ሰማዕትነታችሁ የከበረ ነው።

ምንጭ፡- ኢኦተቤ ቴቪ
8.1K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 11:56:01 ሰበር ዜና

ዛሬ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስና እና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት የፌደራል አካላት በመምጣት ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ምዕመናን ላይ ጭፍጨፋ እያደረጉ ይገኛሉ በእዚህ ሰዓት

አንድ ኦርቶዶክስ በዚህ ሰዓት ሞቷል።


ሁላችንም ኦርቶዶክሳዊያን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ነቅተን የአባቶችን አዋጅጨመጠበቅ ይኖርብናል በየትኛው ሰዓት ኢንተርኔት ሊዘጋ ስለሚችል ቤተክርስቲያን ጥሪ ስታደርግ ሁላችንም በአንድነት መነሳት አለብን


እግዚአብሔር የደረሰብንን ሁሉ ይመልከት
10.9K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 07:26:14
"ምዕመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል"
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስና እና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት በምእመናን ላይ ስጋት መፍጠሩን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማምሻውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን አሳወቁ።

ከሰሞኑን የሀገረ ስብከቱ አገልጋዮች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ይህንንም ለሚመለከተው የዞን ፀጥታ አካል ለማሳወቅና ጥበቃ እንዲያደርጉ ብንደውልም፣ መልእክት ብንጽፍም ሊመልሱልን አልቻሉም ብለዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለኦሮምያ ክልል የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ጥበቃና ከለላን በተመለከተ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስቀድሞ ደብዳቤ ቢጻፍም ምንም አይነት የቃልም ሆነ የተግባር መልስ እንዳልተሰጣቸውም ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም መንግሥት በሕገ ወጡ ቡድን የሚደረገውን ድርጊት ማስቆም ካልቻለ ምእመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል ብለዋል።

በመጨረሻም ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ:- የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኅን አግልግሎት ሥርጭት ድርጅት
13.3K views04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ