Get Mystery Box with random crypto!

'አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

"አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?" -ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በመንግሥት አካላት የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን አስመልክቶ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤተ ክርስቲያን እና በክርስቲያኖችን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የማሳደድ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል::

በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ እናስከብራለን በሚል በትግራይ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰበሰበ ወራሪ ቡድን ጋር በማበር በጠራራ ፀሐይ ሕግ ሲጥስና የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆኖ ማየት እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው በማለት ገልጸዋል።

በሻሸመኔ ከተማ በኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው ግፍ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለማጥፋት ከሚደረግ የዘር ጭፍጨፋ ተለይቶ የሚታይ አይደለም።

አንድ ሀገርን እመራለሁ የሚል መንግሥት የሕዝቡን በሕይወት የመኖር ሰብዓዊ መብት ማክበር እና ማስከበር ካልተቻለው መንግሥትነቱ ምኑ ላይ ነው?