Get Mystery Box with random crypto!

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ ከፖሊስ ጋር በተደረገው ውይይት ሕዝቡ ወደ ቤቱ እንዲ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ ከፖሊስ ጋር በተደረገው ውይይት ሕዝቡ ወደ ቤቱ እንዲመለስ በከተማው የመጣ እንግዳ የለም የሚል ከፖሊሶቹ ሃሳብ የቀረበ ቢሆንም ሀገረ ስብከቱና የሀገር ሽማግሌዎች ሕገ ወጦቹ ግለሰቦች በአንድ ሆቴል ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከቅዱስ ሲኖዶስና ከአባቶቻችን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ግቢያችን ውስጥ ሆነን እየዘመርን እና ወንጌል እየተማርን ቤተ ክርስቲያናችን እንጠብቃለን፡፡

ሀገረ ስብከቱና የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት የመጡት ሕገ ወጥ ግለሰቦች ወደ መጡበት ቦታ ካልተመለሱ ሕዝቡን ማሰናበት አንችልም፣ ሕዝቡም እሺ አይለንም በሚል ለመንግሥት የጸጥታ አካላት ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

ከመንግሥት የመጡ አካላትም ሕዝቡ ከስሜተኝነት እንዲወጣ የሃይማኖት አባቶች እንዲያረጋጉት መመሪያ ሰጥተው መመለሳቸውን ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በንቃት ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቀ በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ የማረጋጊያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል።