Get Mystery Box with random crypto!

በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት ደረሰ! በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕት | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት ደረሰ!

በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት የደረሰ ሲሆን በአራቱ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

አብያተ  ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ምእመናን እስካሁን ድረስ በቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳሉ ናቸው። ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የጸጥታ ኃይል አባላት በዱላ እያባረሩ ይገኛሉ።

የከተማዋ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አካላት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ውጪ ላሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ነጠላ በማደል ሻሸመኔ ስታዲዮም ተገኝተው ሕገ ወጡን ቡድን እንዲቀበሉ እያስተባበሩ ያሉ ሲሆን በመኪና ከተማውን እየዞሩ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ሰዓት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ነገሌ ድረስ ያለውን ቦታ ተቆጣጥሯል።

ምንጭ: ተሚማ