Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136.56K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 40

2023-02-05 10:22:54
በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት በዳሰነችኛ ቋንቋ ቅዱስ ወንጌልን ሲማሩ ከነበሩ ወገኖች መካከል 1182 አዳዲስ አማንያን ብጹዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ብጹዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድንና እስካንዲናቪያን ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ በተገኙበት በኦሞ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት በማግኘት የቤተ ክርስቲያን አባላት ሆነዋል፡፡
17.9K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 09:53:47
አስቸኳይ መረጃ፡፡

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ/አሰበ ተፈሪ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾሙት አካላት በጥር 27/2015 ዓ/ም እንደሚመጡ በቂ መረጃ ለሕቡ ሰለደረሰ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን ከሕገ ወጦች ወረራ በንቃት እንዲጠብቁ ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት በከተማው የሚገኙትን 4 አብያተ ክርስቲያናት በንቃት እየጠበቀ መዋሉ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወቃል፡፡

ከቀኑ 11፡45 ስዓት ላይ የመጡት ሕገወጥ ቡድን ለመንግሥት አካል እንደማይመለሱ ሲነግሩት ሙሉ ወጪ ችሎ እንዲያድሩ አድርጓል። በዚህ መሀል 10 የማይሞሉ ዱላ ይዘው እየዘፈኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ እነሱን ትቶ ቤተክርስቲያ እየጠበቁ ባሉት ላይ ተኩስ ተከፈተ።

በተኩስና አስለቃሽ ጭስ እስከ 2ስዓት ምዕመናን ሲያዋክብም አምሽቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ ከበው ህዝቡን በተኩስ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ በዱላ እያሰቃዩ ሙሉ ህዝቡን እንዳስወጡና የሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ አንዳንድ የመምሪያ ሓላፊዎች ሞታችን በልደታ ብለው ግቢ ውስጥ ቀርተዋል፡፡

እስከምሽቱ 4ስዓት ላይም ቤተክርስቲያን ማን እንደሚገባ መመሪያ ከመንግስት እንጠብቃለን ብለው ከቆዩ በኋላ እና 5 ሰዓት ላይ ከሆቴል ጠርተው ሕገወጡን ቡድን አስገብተዋል፡፡ የጸጥታ እና የመንግስት አካላት ዛሬ እሑድ 4ስዓት ተደራደሩ ወይም ለሕገ ወጡ ቡድን ንብረት አስረክቡ ብለው አባቶችን እያስገደዱ ይገኛሉ።
አባቶች ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የምንመራ እንጂ በግል ምንወስነው አይደለም ብለዋል።

የጸጥታ ኃይሎች ተደራድረው ገብተዋል ለማለት ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ የመምሪያ ኃላፊዎችን አስገድደው ፎቶ ለማንሳት ሲሞክሩ እንደነበረ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መረጃውን ያደረሱን ገልጸዋል።
634 viewsedited  06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 21:59:33 አብይ ሽማግሌ ልኳል

ዛሬ አሁን ከመሽ በአትሌት ደራርቱ ቱሉ የሚመራ ሽማግሌዎች ከአራት ኪሎ ከጠቅላዩ ወደ ቤተክህነት መጥተው አባቶች እግር ወድቀው እባካችሁ እርቅና ሰላም ያስፈልጋል ስለዚህ አሁን ተነሱ ወደ ቤተመንግሥት መሄድ አለብን ብለው ሲማፀኖ አምሽተዋል

የእኛ አባቶች ደግሞ አሁን በአሁን የሚሆን ነገር የለም ዛሬ ይሄ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ብዙ ለምነን ተማፅኖ አቅርበናል ስለዚህ ዛሬ አይሆንም ቋሚ ሲኖዶስ ይምከርበት ሲኖዶሱ ይነጋገርበትና ያኔ መልስ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል!
16.5K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 21:31:32
"የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?"
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ



የሲዳማ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ እንዲሁም የምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ምሽት የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሻሸመኔ አብያተክርስቲያናትን በመሥበር ምእመናንን በግፍ በማሠርና በመደብደብ ከየአካባቢው ባመጧቸው ቡድኖች አብያተክርስቲያናት ተቆጣጥረዋል ሲሉ ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በስልክ ገልጸዋል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ "የክልል መንግሥታት ዝምታ የሚያስተዛዝብ ነው። ቢያንስ ተው አለማለታቸው ለምንድን ነው?" ያሉ ሲሆን ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የሰጡትን መግለጫ ምእመናን እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
በ13 ወረዳዎች ሊቃነ ካህናት በግፍ መታሠራቸውን ገልጸዋል።
የብፁዕነታቸውን መልእክት በዩቲዩብ ገጻችን ይከታተሉ።

ምንጭ: EOTC TV
16.0K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:15:04
በአሰበ ተፈሪ/ጭሮ/ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእመናን እየወረወሩና ተኩስ መጀመራቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጹ።
ምእመናን ከጠዋት ጀምረው ቤተ ክርስቲያኗን ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን የዞኑ የጸጥታ ኃይል "በሁለታችሁ አንገባም" በማለት ገለልተኛ ለመሆን ሞክሮ ውሏል።
ነገር ግን ከመሼ ከክልል የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የክልሉ ልዩ ኃይልን ጨምሮ ተኩስ በመክፈት አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእምናን እየወረወረ መሆኑን ምእምናን በስልክ ገልጸውልናል።
መረጃውን ያደረሱን ምእመናን አክለውም የጸጥታ ኃይሉ ቤተ ክርስቲያኑ ከቦ እየተኮሰና እያወከበ ቢሆንም ምእመኑ ግን ከግቢ አልወጣም ብሏል።
17.8K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:01:17
ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
16.9K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 18:54:32 መንግሥትም ሰላም እና ደህንነትን ከማስጠበቅ ባለፈ የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብትን እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብትን በመገደብ ያለአግባብ ታግተው መቆየታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከዚህ ቀደም መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸውም ሳይታቀቡ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ አቡነ ያሬድን በሕገ ወጥ መልኩ የዜግነት መብታቸው ተጥሶ በደረቅ ሌሊት በማሰር እና በማዋከብ ከሀገረ ስብከታቸው ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደየ አህጉረ ስብከታቸው እንዳይሄዱ ማስፈራሪያ በመላክ የቤተ ክርስቲያችንን ክብር እና ልዕልና እጅጉን የሚጎዳ እና አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመባት ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የየሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን በሕገ ወጥ መልኩ በማሰር እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባለመወጣቱ ቤተ ክርስቲያናችን እጅጉን አዝናለች፡፡

ከዚህም አልፎ መንግሥትም በቤተ ክርስቲያችን በኩል በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ችላ በማለቱ ምክንያት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ሕገ ወጦቹ መንግሥትን ተገን በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጥ መልኩ ወረራ ለመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያንችንን ለመጠበቅ በወጡ ምእመናን ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የአደባባይ የግድያ ወንጀል ተፈጽሟል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያልታወቁ ምእመናንም ላይ ከፍተኛ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 

ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር በተመለከተ ተገቢውን ሕጋዊ የሰላም እና የደህንነት ከለላ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ብትሰጥም ይህንን ማሳሰቢያ ወደጎን በመተው መንግሥት ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ እና በማስፈጸም ከላይ የተገለጹትን አሳዛኝ ድርጊቶች በይፋ በአደባባይ ፈጽሟል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1. በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንና እና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስር እና ወከባ ቅዱስ ሲኖዶስ በፅኑ አውግዟል፤
2. በጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ፍጹም ታወግዛለች፤ ተገቢውን ሲኖዶሳዊ እና ሃይማኖታዊ ጸሎት በማድረግ በሁሉም አጥቢያ ሥርዓተ ፍትሐት እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ጾመ ነነዌን ሙሉ የሱባዔ ጊዜ በማድረግ ጥቁር ልብስ ያለውን ትርጓሜ በመግለጥ እንድንሰነብት መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
3.1. ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምትገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንድትመሩ እና እንድትከታተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.2. በየትኛውም እንቅስቃሴ ይህንን ጥቁር ልብስ በመልበስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ንቁ በመሆን እንድትፈጽሙ፤ ሆኖም ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዓለም አቀፍ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ካወጀበት ቀን በኃላ በተለያዩ ከተሞች የጥቁር ልብስን ሆነ ተብሎ ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን በመረዳታችን ምዕመናን ያላችሁን ተመሳሳይ አልባሳት በመጠቀም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በእንቅስቃሴያችሁ ሁሉ እንድትፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.3. በነዚህ ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ በድምጽ ማጉያ እንዲከናወን እና የሙሉ ጊዜ ሆኖ በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት እየተጠበቀ በተመሳሳይ ሰዓታት ለአምስት ደቂቃ ያህል በማያቋርጥ ደወል በመደወል የማስተጋባት ሥራ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.4. ይህንንም የየአህጉረ ስብከት፤ የወረዳ ቤተ ክህነት እና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በመከታተል እንድታስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3.5. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የኦርቶዶክስ ዓለም፤ እውነቱን የምታውቁና የምትደግፉ ማናቸውም ኃይማኖታዊም ሆነ ማህበራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመደገፍ በአንድነት ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
4. በነዚህ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ እንደሆነ
4.1. በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በእልልታ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.2. የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 
5. ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
16.4K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 18:54:32
ሰበር ዜና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረው አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል በሕገ ወጥነት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ የተባሉ ግለሰብ መሪነት ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን  ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው  እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡
13.2K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 17:33:01
አሰላ

የከተማው ህዝብ በሌለበት ከበቆጂ የሌላ እምነት ተከታዮችን በአይሱዚ በማምጣት መንበረ ጵጵስናውን ሰብረው ገብተዋል። ስድስት ፓትሮል መኪና ያጀባቸው የክልሉ ልዩ ኃይል ሲሆን ከገቡ በኋላ በተሿሚው የገዳሟን ምዷየ ምጽዋት በመሥበር ለአጃቢዎቹ የፀጥታ ሰዎች ሕገ ወጥ ተሿሚው ገንዘቡን አድለዋል። የከተማው ፖሊስ ሊቀ ጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ያሬድን አፍኖ ምሽት ከከተማው ማስወጣቱ ይታወቃል።

ምንጭ eotc tv
14.4K viewsedited  14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 17:32:23
ከደቂቃዎች በኋላ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት መግለጫ ይሰጣል
14.6K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ