Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136.56K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2023-02-08 19:04:18
ፍርድ ቤቱ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

የቤተክርስቲያናችንን የሕግ ጉዳይ የሚከታተለው ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ በቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን ላይ የደረሰውን ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰትን አስመልክቶ ቤተ ክርስቲያን ክስ መመስረቷን በማውሳት የክሱ ሂደት የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ክርክር የተከናወነ ሲሆን ለየካቲት 3/2015 ዓ.ም ተጨማሪ ቀጠሮ መያዙ ገልጿል።
15.2K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 19:02:47
የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ወጡን “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” እንደማትቀበልና ቤተ ክርስቲያንን የመክፈል ሙከራን እንደምታወግዝ አስታወቀች፡፡

ከስድስቱ ኦሬንታል እህት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ የሆነችው የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በፓትርያርኳ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አግናጢዎስ ኤፍሬም ፪ኛ በኩል ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጻፈችው ይፋዊ ደብዳቤ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ በለየው ሕገ ወጥ ቡድን የተፈጸመውን “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” በማውገዝ ከቅድስት ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጎን መቆሟን ገልጻለች፡፡

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ሕጋዊ እና ሐዋርያዊ ቅዱስ መሪነት ብቻ የምትቀበል መሆኑን በመግለጽ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ የተከሰተው ፈተና እንዲያልፍ በጸሎት እንደምትለምን ገልጻለች፡፡
14.7K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 19:00:50
ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግስት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም !
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሻሸመኔ ከተማ በኦሮሚያ ክልል መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ኦርቶዶክሳውያንን ከክልሉ የማጽዳት ዘመቻ የሚመስል ኢሰብዓዊ እና ኢሕገመንግስታዊ ድርጊት መፈፀሙ መላው ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ ድርጊት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አያይዘውም ለሕዝብ የተቋቋመው መንግስት የሕዝብን ሰብዓዊ መብት አለማክበሩ ሳያንስ በአንዳንድ አካባቢዎች ፣ ብሎም መንግስት በሚመራቸው ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ኦርቶዶክሳውያን መልበስ የምትችሉት እኔ የመረጥኩላችሁን ብቻ ነው በሚል ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን ቀኖናዊ ትዕዛዝ ምዕመናን እንዳይፈጽሙ ብሎም እንዲሸማቀቁ በማድረግ እያካሄደ ያለው አፈና ዲሞክራት ነኝ ከሚል መንግስት የማይጠበቅ ፣ መብታችንን የረገጠ እና ከቀደሙ አፋኝ መንግሥታት ሥርዓት የተለየበትን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚያዳግት ተግባር ነው ።

ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ከምን ጊዜውም በላይ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ እና አቅጣጫ ብቻ በመከተል የመብት ጥያቄያችን በተግባር እስከሚመለስ እና የመኖር መብታችንን እስከምናረጋግጥ ድረስ በሰላማዊ መንገድ ትግላችንን እንድንቀጥል እያሳሰብን ፤ የጸጥታ አካላትም ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ጠባሳ ከመጣልና ሰላማዊ ክርስቲያኖችን ከማሳደድ እንድትቆጠቡ እንጠይቃለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
13.2K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 11:02:46
ይነበብ

ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች የዝማሬ ዳዊትን የዩቲዩብ ገጽ subscribe አድርጉ አገልግሎቱን አግዙ እያልን ብዙ ግዜ ብንናገርም በፍቅር ጥያቄያችንን ተግባራዊ ያደረጉ ጥቂት ብቻ ናቸው። ለምን ጥቂቶች ብቻ?

ምንም የማይጠቅመን ቦታ ስንርመሰመስ አይደል የምንውለው? መንፈሳዊ ተግባራትን ለመፈጸም እጃችን እሚታሰረው ስለምንድን ነው? መንፈሳዊ አገልግሎትን ልትደግፉ የምትችሉበት አንዱ እና ዋነኛው መንገድ ይህ እንደሆነ ጠፍቷችሁ ነው?

አሁንም ደግመን እንጠይቃለን እግዚአብሔር በፈቀደልን መልኩ መልካም አገልግሎት ወደናንተ ለማድረስ እየሰራን ነው። ከዚህ በብዙ መስራት እንድንችል ግን የእናንተም ድጋፍ ያስፈልገናል። ምን እናግዝ ካላችሁን ሁላችሁም ይህን ጽሁፍ የምታነብ በጠቅላላ ከስር ባስቀመጥነው አድራሻ በመግባት ዝማሬ ዳዊትን Subscribe እንድታደርጉ በቅዱስ ገብርኤል ስም እንጠይቃለን።

በተጨማሪም ይህን መልዕክት ለሁሉም ባለ ማዕተብ አድርሱልን። ለምትሰጡን መልካም ምላሽ እግዚአብሔር ያክብርልን።

https://bit.ly/2O1Z3d8
https://bit.ly/2O1Z3d8
ወይም
https://www.youtube.com/channel/UC8iS8VUpEphoIVnfhsC2WdQ
6.3K views08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 10:00:43 ​​ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጸሐፊ  ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌ  ጋር በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችን ጉደይ ውይይት አደረጉ።

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኀን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ጥር ፳፭  ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ጄኔቭ፣ ስዊትዘርላንድ በሚገኘው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በመገኘት ከዋና ጸሐፊው ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌ ጋር ውይይት አደረጉ። 

ብፁዕነታቸው  ዋና ጸሐፊው በቅርቡ ለዚህ ከፍተኛ ኃላፊነት በመመረጣቸው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ስም የደስታ መልእክት አስተላልፈዋል።

ቤተ ክርስቲያን የምክር ቤቱ መስራችና ንቁ አባል በመሆን የበኩልዋን ሚና እየተወጣች መሆኑን አስታውሰው ይህ ግንኙነት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ወቅታዊ ሁኔታ ያብራሩላቸው ሲሆን የችግሩ ዋነኛ ምንጭ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖና እና ሕግጋት የጣሱ ጥቂት አፈንጋጭ አካላት ድርጊታቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕልውና ላይ የሚያስከትለውን ታላቅ አደጋ በመገንዘብ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወገዙና የተለዩ ቢሆንም መንግሥት የሕግ የበላይነትንና የሕዝብን ሰላም የመጠበቅ ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ ሐዘንና ጭንቀት ፈጥሯል።

በዚህም ጳጳሳት እየተሳደዱ፣ ካህናት እየታሰሩ፣ ምዕመናን እየተደበደቡ ይገኛሉ። እንዲህም ሆኖ ሕግ የጣሱት አካላት በንስሐና በይቅርታ ቢመለሱ ቤተ ክርስቲያን በሯን ክፍት አድርጋ እየጠበቀች ትገኛለች። ምክር ቤቱ ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ልዕልና፣ ለሕግ የበላይነት፣ ለሰላምና ለፍትሕ አጋርነቱን እንዲገልጽ ብፁዕነታቸው ጠይቀዋል።

ዋና ጸሐፊው  ለተደረገላችው ዝርዝር ማብራሪያ አመስግነው ይህች ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን በወቅቱ የገጠማት ፈተና በእጅጉ አንደሚያሳስባቸውና ጉዳዩን በቅርበት መከታተላቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በብፁዕነታቸው በኩል ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ሰላምታና መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።  ከብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ጋር መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ሃይለ ጊዮርጊስ በስዊትዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የጄኔቫ አጥቢያ ሰበካ ጉባኤ አመራር ተወካዮች በውይይቱ ተሳትፈዋል።

ውይይቱን ተከትሎ ዋና ጸሐፊው በማግስቱ አጋርነታቸውን የሚያሳይ መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫቸው ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት የተመሰረተች፣ ሁልጊዜም ለአንድነትና ለሰላም የደም መስዋዕትነትም ጭምር ስትከፍል የኖረች ናት ብለዋል። አዲስ ሲኖዶስ ለመመስረት በሚደረገው ሙከራ ማዘናቸውን ገልጸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲጠበቅ በጸሎት እግዚአብሔርን ጠይቀዋል። የሚመለከታቸው የፖለቲካ ኃይላት ሁሉ ሕጋዊ ሰውነት ያላት ቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጉዳይዋን በአላት መንፈሳዊ ቀኖና እና ሕግ ለመፍታት ብሎም የምዕመኗን ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ: ኢኦተቤ ቴቪ
8.7K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 18:52:22
አብይ አህመድ የዘመናችን ኔሮን ቄሳር
16.5K viewsedited  15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 17:45:57
በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲ በማለት ኦርቶዶክሳዊያኑ ላይ ታላቅ በደል እያደረሱ ይገኛል።
15.4K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 12:11:19
#ተጨማሪ_የእስር_ዜና

ሕገወጡን ቡድን ትቃወማላችሁ በሚል መንግሥት በኦርቶዶክሳውያን ላይ እያደረሰ ያለው እስር እንደቀጠለ ሲሆን በትናንትናው ዕለት በማኅበረ ቅዱሳን የሻምቡ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ደረጄ ገለታ እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳን የቡሌሆራ ማእክል አገልጋዮች ቀሲስ እሸቱ ታደሰ እና ቀሲስ መንግሥቱ መኮነን መታሰራቸው ታውቋል።
19.7K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 10:23:35
በጅማ የኦርቶዶክሳውያን እስር እንደቀጠለ ነው፡፡

ዛሬ ጠዋት የማኅበረ ቅዱሳን ጅማ ማእከል ሰብሳቢ እና የደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑትን አቶ ታዬ ደሳለኝ ታስረዋል፡፡

በተጨማሪም ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ማንም መንቀሳቀስ አይችልም መባሉን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡
21.7K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 21:54:12
እናቴ ቤተክርስቲያን በኔ በኃጥያተኛው ልጇ በደል ጥቁር ለበሰች! የሕይወቴ ጥቁሩ ታሪክ

ቤተክርስቲያን ጥቁር ልብስ ለብሳ እኔ ሌላ ልብስ አልለብስም። የአባቶቼን ትዕዛዝ እቀበላለው አከብራለው ጥቁር እለብሳለው እጾማለው እጸልያለው!
9.9K views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ