Get Mystery Box with random crypto!

ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግስት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም ! | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግስት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም !
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕነታቸው በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሻሸመኔ ከተማ በኦሮሚያ ክልል መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ኦርቶዶክሳውያንን ከክልሉ የማጽዳት ዘመቻ የሚመስል ኢሰብዓዊ እና ኢሕገመንግስታዊ ድርጊት መፈፀሙ መላው ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ ድርጊት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አያይዘውም ለሕዝብ የተቋቋመው መንግስት የሕዝብን ሰብዓዊ መብት አለማክበሩ ሳያንስ በአንዳንድ አካባቢዎች ፣ ብሎም መንግስት በሚመራቸው ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ኦርቶዶክሳውያን መልበስ የምትችሉት እኔ የመረጥኩላችሁን ብቻ ነው በሚል ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን ቀኖናዊ ትዕዛዝ ምዕመናን እንዳይፈጽሙ ብሎም እንዲሸማቀቁ በማድረግ እያካሄደ ያለው አፈና ዲሞክራት ነኝ ከሚል መንግስት የማይጠበቅ ፣ መብታችንን የረገጠ እና ከቀደሙ አፋኝ መንግሥታት ሥርዓት የተለየበትን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚያዳግት ተግባር ነው ።

ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ከምን ጊዜውም በላይ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ እና አቅጣጫ ብቻ በመከተል የመብት ጥያቄያችን በተግባር እስከሚመለስ እና የመኖር መብታችንን እስከምናረጋግጥ ድረስ በሰላማዊ መንገድ ትግላችንን እንድንቀጥል እያሳሰብን ፤ የጸጥታ አካላትም ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ጠባሳ ከመጣልና ሰላማዊ ክርስቲያኖችን ከማሳደድ እንድትቆጠቡ እንጠይቃለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።