Get Mystery Box with random crypto!

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ወጡን “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” እንደማትቀበልና ቤተ ክርስቲያ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ወጡን “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” እንደማትቀበልና ቤተ ክርስቲያንን የመክፈል ሙከራን እንደምታወግዝ አስታወቀች፡፡

ከስድስቱ ኦሬንታል እህት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ የሆነችው የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በፓትርያርኳ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አግናጢዎስ ኤፍሬም ፪ኛ በኩል ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጻፈችው ይፋዊ ደብዳቤ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ በለየው ሕገ ወጥ ቡድን የተፈጸመውን “ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት” በማውገዝ ከቅድስት ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጎን መቆሟን ገልጻለች፡፡

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ሕጋዊ እና ሐዋርያዊ ቅዱስ መሪነት ብቻ የምትቀበል መሆኑን በመግለጽ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ የተከሰተው ፈተና እንዲያልፍ በጸሎት እንደምትለምን ገልጻለች፡፡