Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136.56K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 39

2023-02-05 23:03:32 #መሐረነ_አብ_ሙሉ_ፀሎቱ

ሼር በማድረግ ማታ ማታ ከአባቶች ጋር በጋራ እንጸልይ

#ሼር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
4.6K viewsedited  20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 23:03:07 "መሐረነ አብ" ሙሉ ጸሎቱ #በዜማ

ሼር በማድረግ ማታ ማታ ከአባቶች ጋር በጋራ እንጸልይ

#ሼር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
4.2K views20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 20:34:02 #ተው_ዓለም_ተመለስ

ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
በቁጣ መዓቱ ይቀጣሃል ጌታ ይቀጣሃል ጌታ

ትውልዱ ተመታ በታላቅ በሽታ /፪/
ኧረ በልክ ይሁን ጭፈራና ደስታ /፪/
በማዕበል በጎርፍ እያየህ ሲቀጣ/፪/
አሁንም ተመለስ የከፋ ሳይመጣ /፪/
#አዝ
ነነዌን ሊያጠፋ የወረደው እሣት /፪/
አንተን እዳይመታህ ተነሳ ለጸሎት/፪/
ዓለም ብትሰጥኽ አንተ እድትተጋ /፪/
ሀልወተ እግዚአብሔር እንደምን ይዘንጋ
#አዝ
ችግር ለበዛበት እጅግ ለታወከው/፪/
አምላክ መሐሪ ነው ለተንበረከከው/፪/
የዓለም መድሐኒት የዓለሙን ቤዛ /፪/
ጠይቀው ምሕረትን ሠው ሆይ ልብ ግዛ
#አዝ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
ተው ዓለም ተመለስ ተው ዓለም ተገታ
በቁጣ መዓቱ ይቀጥሃል ጌታ ይቀጣሃል ጌታ።

ሊቀ መዘምራን
ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
11.0K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 19:54:32
የነነዌ ጾም ሥርዓተ ጸሎት መርሐ ግብር

ምንጭ: EOTC TV
13.9K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 19:37:37 ነነዌን ሊያቃጥል

ነነዌን ሊያቃጥል የወረደው እሳት (፪)
ተመልሶ ዐረገ(፪) በሀዘን በጸሎት (፪)
ስለሆነ ከልብ የሀዘናቸው ምንጩ (፪)
ነበር እንደ ራሔል (፪)እንባን እየረጩ (፪)
ለነነዌ ሰዎች ደስታን ያበሰረ (፪)
ጋሻ እና ጦራቸው(፪)ጾም ጸሎት ነበረ (፪)
እንኳን የሰው ልጆች እንስሳት ሳይቀሩ(፪)
በዮናስ ስብከት (፪)ፆም ጸሎት ተማሩ(፪)

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
12.1K views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 19:29:00 ​​ጾመ ሰብአ ነነዌ
በርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል


ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡

ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም የካቲት 7 ቀን ትጀመራለች፡፡

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/ ፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡

በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡

ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡

ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛ ነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡

እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ  መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ››  ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡

እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ  ንብረታችሁን  ሳይኾን እኔን  ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡

እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡

ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡

እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡

ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡

የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል  ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡

ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡

በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን  ‹‹አንተ  ላልደከምክበት  እና በአንድ  ቀን በቅሎ  ላደገ ቅል  ስታዝን እነሆ  በታላቂቱ  ነነዌ ከተማ  ያሉ ከአንድ  መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ  የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ  ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡

ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ  ተመለሱ፤  እኔም ይቅር  እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡

ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡

ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
12.0K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 17:53:38
ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡

በጾመ ነነዌ የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ድርሻ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡

የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው፡፡

በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።
14.2K views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 14:55:07
መርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን

አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትርያርክ
አንዲት ቤተክርስቲያን


#Share
16.8K views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 14:52:46
ኦሮሚያን የኦርቶዶክሳውያን እስርቤት ማድረጉ ቀጥሏል።

በአዲስ አበባ አጎራባች ዞኖች በይበልጠጥም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሰበታ መሥመር የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በአፈሳ መልክ መጋዙ ቀጥሏል። በጅማ እና ሻሸመኔ በምዕራብ አርሲ ወረዳዎች በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ የወረዳ ሊቃነ ካህናት አባቶች ቀሳውስት ዲያቆናት በጅምላ እየታሠሩ መሆኑ መረጃዎች እየደረሱን ነው።

ትላንት የታሰሩ ምእመናን ምግብና ውሃ እንዳያገኙ ተደርገዋል። የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እስካሁን ዝምታን መርጠዋል።

ምንጭ: EOTC TV
15.9K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 10:25:04
ደሴ
ጥር 28/05/2015
ታላቅ ሰላማዊ ሠልፍ እየተደረገ ይገኛል
19.0K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ