2024-03-13 14:44:25
ባለ ትዳሮችን ብቻ ሳይሆን የዝሙት ሱሰኞችንም ይጨምራል ሁላችሁም ሼርርርርርር : አድርጉ !!!
ዝሙት የሚሰራውን ብቻ ሳይሆን በዝሙት ሀሳብና ፍትዎት የታመምነውንም ይጨምራል ይህ ትምህርት ለእገሌ ነበር ሳይሆን ለኔ ነው ብለን ልናነበው ይገባል ለሁላችንም ይሆን ዘንድ ከኔ የበረታችሁ አስቡኝ በጸሎታችሁ
ከ10 አንዱ ሊማርበት ስለሚችል ሸር አድርጉት
በጾም ወራት ባለትዳሮች ከግብረ-ስጋ ግንኙነት እንዲታቀቡ ቤተክርስትያን የምትመክረው
#መጽሐፍ_ቅዱሳዊ_ነውን?
፠ ከባለትዳር ወዳጄ ለተጠየኩት ፠
በቤተክርስትያችን ትምህርት ሰው ለአቅመ አዳም እና ለአቅመ ሔዋን ከደረሰ በኋላ ሕይወቱን የሚመራበት ሁለት አይነት ምርጫ አለው፤ ጋብቻ ወይም ምንኩስና።
❖ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለምንኩስና እንዲህ ብሎ ነበር።
#መነኩሴ ፡- ማለት መናኝ ፣ ብቻውን የሚኖር ፣ሴት የማያውቅ ድንግል፣ የገዳም ሰው፣ ባተሌ፣ ከዓለም ከሕዝብ ከገንዘብ የተለየ ማለት ነው /አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት እና
ምንኩስና በኢትዮጵያ ላይ እንደተገለጠው/፡፡
#ምንኩስና- ለሴትም ለወንድም ይሰራል፤ ዓላማው በትዳር አሳብ ሳይጠላለፉ በሙሉ ጊዜ ፈጣሪን የማገልገያ መንገድ ነው፡፡
በአንድ ወቅት ጌታ ስለ ጋብቻ ሕግ ባስተማረ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ‹‹የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም ›› ሲሉት እንዲህ ብሎ ዘርዝሮ ነገራቸው።
ከሴት ርቆ ከወንድ ርቆ ንጽህናን ጠብቆ መኖር ስጦታ ነው እንጂ ሁሉ የሚችለው
አይደለም ሲል ‹‹ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም›› አለ። ማቴ 19፡11፡፡
ቀጠለና ቁጥር 12 ላይ ‹‹በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም
የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው።›› አለ፡፡
ይሄ የጌታ ንግግር የሚያረጋግጠው .. ሶስት ነገሮችን ነው። ደግሞም ብልቶቻቸውን ለግብረስጋ ግኑኝነት የማይጠቀሙበት ሰዎች አሉ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ጃንደረባ ማለት ብልቱ የተቆረጠ ማለት ነውና፡፡
1. የመጀመሪያዎቹ በጌታ አገላለጽ በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የሚወለዱ ያላቸው ፦
አካል ሳይኖራቸው የሚወለዱ ወይም አካሉ ቢኖርም ተፈጥሮአዊ ሙቀት ሳይኖራቸው የሚወለዱት ናቸው።
2. ሁለተኛዎቹ ደግሞ ሰው የሰለባቸው ጃንደረቦች ናቸው / ይሄ በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች በጎሳዎች መካከል ሲጣሉ እና ለጋብቻ ማጫ እንደሚሰልቡ የሚታወቁ ቦታዎች አሉ… የሚገርመው ነገር እነሱ በጉዳዩ ሊጠቀሙ የሌላውን መጠቀሚያ አካል ቆርጦ ማጫ
ማቅረብ… ምን ያህል… ኢ ፍታዊነት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡
3. በጌታ አነጋገር ሶስተኛው አይነት ጃንደረባነት ‹‹ስለ መንግሥተ ሰማያትም
ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ›› ያላቸው ሲሆኑ... ይሄም ምንኩስና ነው፤ ለመንግስተ ሰማያት ተብሎ ከጾታ ግኑኝነት ራስን ማራቅ ማለት ነው።
❖ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሰለምንኩስና ምን አለ?
1ኛ ቆሮ 7፡17 ቅዱስ ጳውሎስ "እንዳያገቡ አወዳለው" ማለቱ ሲሆን ነገር ግን ‹‹ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም
እንደዚያ።>> በማለት ሁሉ ተመሳሳይ ጸጋ እንደሌለው አረጋግጧል…አንዱ እንደዚህ /አያገባም/ ሁለተኛው እንደዚያ ሲል ደግሞ /ያገባል/ ማለት ነው፡፡
ልክ ጌታ በማቴ 19 ፡12 ‹‹ ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው ›› እንዳለ ሊቀበለው የሚችል ሁሉ አይደለም፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ዘርዘር ሲያደርገው፦
1ኛ ቆሮ 7፡32 ‹‹ነገር ግን ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአል። በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው›› ስለሆነም ቅዱስ ጳውሎስ በአጠቃላይ መልዕክቱ ልባቹ እንዳይከፈል ከቻላችሁ አታግቡ ብሎ መክሯል … በመጨረሻው ንግግሩም ‹‹ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ያላገባም የተሻለ አደረገ።›› በማለት ድንግልን ማግባት መልካም ቢሆንም የተሻለው ግን አለማግባት ነው፡፡
ስለዚህ ነገር አንድ የቤ/ክ ሊቅ እንዲህ ብለው ነበር ጳውሎስ ጋብቻን ክቡር ነው ቢልም እርሱ አላገባምና ይ ብልጠቱን ተመልከቱ ብለው ነበር፡፡
እንግዲህ ይሄን የቅዱስ ጳውሎስ ብልጠቱን ማየት /አለማግባት/ ሳይቻለን ቀርቶ ጸጋችን ጋብቻ መሆኑን አውቀን ለማግባት ከመረጥን ደግሞ ቅድመ ጋብቻ ወሲብ እንደማይገባ አውቀን የምንጋባው በድንግልና ነው፡፡ ‹‹ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር፥ የወደደውን ያድርግ፤ ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ።›› 1ኛ ቆሮ7፡36፡፡
ስለድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር ማለት…. ቆሞ ቀረ ተባልኩ ብሎ ያፈረ ሰው ቢኖር… ያግባ ነው የሚለው… ድንግል ሆኖ በመኖሩ ያፈረ ሰው ድንግልናውን በጋብቻ ብቻ ነው የሚያጣው ማለት ሲሆን ይሄም የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ሰው ድንግልናውን ጠብቆ እስከጋብቻ መጽናት እንዳለበት ያረጋግጣል… ‹‹ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ›› 1ኛ ቆሮ7 ፡38፡፡ የሚለው ቃል መጋባት በድንግልና መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
አረ ቅዱስ ጳውሎስ እንደዚህም ብሏል ‹‹ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤>> 1ኛተሰ 4፡5፡፡
አንድ መተርጉም ቅዱስ ጳውሎስ "የራስን ዕቃ በክብር ማግኘት" ያለው .. የሚገኝ የራስህ የሆነ የትዳር አጋርህን አካል ነው…. እሱም ያንተ የሆነ ንብረት ነው…. ግን በቅድስና እና በክብር ያገኝ ዘንድ የተባለው ደግሞ በህጋዊ ትዳር በሰርግ ደስታ…. በጋብቻ ስርዓት ተቀበለው ሲል ነው ብሎ ተርጉሞታል… ይሄን የሰማች አንድ እህት በወቅቱ …. እኔማ… ‹‹ብር አምባር ሳላሰኝ›› ሞቼ ነው ብላ ፎክራ ነበር… እኛም ይበል ብለን አልፈነዋል…
እንዲህ አይነቱን አቋም እናበረታታለን…እስካሁን ጉዳዩ ተጠብቆ ካለ… እንዲው አልሆነ ቦታም ከወደቀም… ድጋሚ አይነሳምና ከተክሊል ርቆ በመዓስባን ጋብቻ ለመጋባት የነፍስን ድንግልና በንስሐ መመለስ ነው፡፡
#ይቀጥላል
በቀጣይ ክፍል በጋብቻ ወስጥ ግብረ ስጋ ግኑኝነት በመጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ይገለጻል ??
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
12.7K views11:44