Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136.15K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-01-19 07:15:06
Bole mickael

እንኳን አደረሳችሁ
15.0K viewsedited  04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-18 15:26:39
ከፈረንሳይ ለጋሲዮን የተላከ

"እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።" የፈረንሳይ ለጋሲዮን ወጣቶች

ሰፈራቸውን በዚህ መልኩ አድምቀውታል። አስካሁን በውስጥ ከተላኩልኝ ፎቶዎች አ.አ ውስጥ በአርማችን የተዋበችው የፈረንሳይ ለጋሲዮን ሰፈር ናት።

ሌሎቻችሁም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከሰፈራችሁ ድባብ ጋር በፎቶ አድርጋችሁ በውስጥ ላኩልን።

@Zimaredawitmessanger
18.3K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-18 07:07:46 ​​​​ጾመገሀድ
በየኔታ ዘለዓለም ሐዲስ


ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት ስለሆኑ ነው።

እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡

ገሀድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሀድና ጋድ፡፡ #ገሀድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል።

በሌላም በኩል #ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡

ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ከመ ይደሉ ንጹም እሎንተ ክልኤተ ዕለታተ ዘእምቅድመ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት እስመ እላ ዕለታት ህየንቴሆሙ ለረቡዕ ወዓርብ ሶበ ይከውን ላዕሌሆሙ በዓለ ልደት ወጥምቀት ወበዝንቱ ይትፌጸም ለነ ክልኤቱ ግብር ግብረ ጾም ወግብረ በዓል ወከመዝ ሥሩዕ ውስተ አብያተ ክርስቲያኖሙ ለግብፃውያን ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሑድ ይጹሙ በዕለተ ዐርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት በከመ ተናገርነ ቅድመ ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሀል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ፡፡

ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው በይረሙን (መገለጥ፣ ገሀድ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዓርብ እስከምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ በማለት ይገልጸዋል፡፡

ከላይ እንዳየነው ጥምቀት ወይም ልደት እሑድና ቅዳሜ ከዋሉ ጾሙ መጀመር ያለበት ዓርብ መሆኑን ተመልክተናል ይህንም መነሻ በማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ሰኞ ሲሆን ዓርብ እስከ አንድ ሰዓት፣ ቅዳሜ እስከ ስድስት፣ እሑድ እስከ ቅዳሴ መውጫ እስከ ሦስት በመቁጠር የጾሙን ሰዓት 13 ሰዓት ያደርጉታል ይህም ከላይ የተገለጠውን ስንክሳር መነሻ በማድረግ የመሚናገሩት ስለሆነ አክብረን እንቀበለዋለን ቅዳሜ እስከ ስድስት ለመጾሙም ሃይ ምዕ 20 ተጠቃሽ ነው።

በሌላ በኩልም ጋድ አንድ ቀን ነው ሰኞ ሲሆን እሑድን ብቻ ከጥሉላት እንከለከላለን እንጅ ቅዳሜን አይጨምርም በማለት ይህን የሚቃወሙ አሉ ስንክሳር የተናገረውን ምን እናድርገው ተብለው ሲጠየቁም ስንክሳር የታሪክ እንጅ የሥርዓት መጽሐፍ አይደለም የሚል መልስ ነው የሚሰጡት፡፡

ይህ ጥያቄ ወደሌሎች ሊቃውንት ሲቀርብ የሚሰጡት መልስ ደግሞ ስንክሳር ታሪክ ብቻ ሳይሆን ሥርዓትም የተካተተበት መጽሐፍ መሆኑን ይናገራሉ በእርግጥ ስንክሳር ማለት እስትጉቡእ ስብስብ ማለት ስለሆነ ሥርዓተ ቤተ ክርስተቲያንን ከሠሩ አበው ታሪክ የተሰበሰበ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ከላይም እንዳየነው ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ስለዚህ አባቶቻችን አዘዙን በማለት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጻፉ አበው አዘዙን አለ እንጅ ስንክሳርን የጻፉ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ ያንጸባረቁበት አይደለም ስንክሳርም ቢሆን ምንም ቁጥሩ ከአዋልድ መጻሕፍት ቢሆን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነውና ጥምቀትና ልደት ሰኞ ከሆኑ ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት ተከልክለን ቅዳሜንም እስከ ስድስት ሰዓት ጹመን የአበውን ትዕዛዝ ማክበር አለብን፡፡

በሌላም በኩል ጋድ አንድ ነው እሱም የጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው የልደት ዋዜማ የለውም የሚሉም አሉ እንዲህ ለሚሉት መልሱ አጭር ነው ጾመ ነቢያት ስንት ነው የሚል ጥያቄ ማንሣት ነው እንደሚታወቀው ጾመ ነቢያትን ስንጾም ቀናቱ አርባ አራት ናቸው 40 ጾመ ነቢያት፣ 3ቱ የፊልጶስ ደቀ መዛሙርት የጾሙትና አብርሐም ሦርያዊ ተራራ ያፈለሰበት ጾም፣ አንዱ ጾመ ገሀድ ነው ስለዚህ በበዓለ ልደት ዋዜማ የምንጾመው ገሀድ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡

ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በተግሳፁ አንዳስቀመጠው "ስለ ፆም ክርክር በተነሳ ጊዜ ሁሌም ቢሆን ለፆም አድሉ "

"" መልሱ እንዲህ ከምስክር መምህራን ሲሆን ይሻላል፡፡ እኛ ከምንናገረው፡፡

የኔታ ዘለዓለም ሐዲስ ማለት የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ምክትልና የ፬ቱ መጻሕፍተ ትርጓሜ መምህር ናቸው፡፡ (እንዲያው የኔ ብጤ የፌስቡክ አርበኛ እንዳይመስሉህ ብዬ ነው!)

DN YORDANOS ABEBE

ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

#ሼር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.1K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-17 23:26:54
፨ጾመ ገሃድ(ጋድ)፨
15.5K views20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-17 21:00:05
ሰላም፡ለኵልክሙ። እነሆ ግእዝን በአንድ ወር ኮርሳችን በ11 ኛው ዙር ትምህርት መርሐ-ግብር ተመልሷል።

በመሆኑም የግእዝ ቋንቋን ቀለል ባለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናል ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን እናጥና ፥ ዕንወቅ።

ትምህርቱን ከ14 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው፤ ስልክ ወይም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም መማር ይቻላል።

 ምዝገባው በዚህ ውስጥ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ በሚላከው መሠረት ቻናል መቀላቀል ነው
@Geez202
@Geez202
@Geez202
                

ለበለጠ መረጃ በ @Geez202 ውስጥ ይደርስዎታል ወይም ከታች በተቀመጠው በመደወልም ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድናዳርስ በአክብሮት እንጠይቃለን
መሠረተ፡ግእዝ
@MesereteGeez -
14.1K views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-17 08:53:57 እስቲ ሁላችሁም በየአካባቢያችሁ ለጥምቀት በዓል በምን አይነት ሁኔታ እየተዘጋጇችሁ እንደሆነ ለዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች አጋሩ።

ከስር ባስቀመጥነው የመልዕክት መቀበያ የአካባቢውን ስም ከፎቶ ጋር አድርጋችሁ ላኩልን።

@Zimaredawitmessanger
14.6K viewsedited  05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-16 21:12:55
፨የአእላፋት ዝማሬ እንዲቀጥል እንፈልጋለን፨

አሁን በዶንኪ ቱዩብ ቀጥታ ስርጭት



16.6K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-16 09:26:52 ​​​​✞ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም "ሥላሴ" እና "ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ሥሉስ_ቅዱስ

ምሥጢራት በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም::

+እግዚአብሔር አንድም ነው: ሦስትም ነው:: ጊዜ ሣይሠፈር ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም: በአካል: በግብር ሦስትነቱ: በባሕርይ: በሕልውና: በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው::

+ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው:: ዓለምን ከፈጠረ በሁዋላም ምሥጢረ ሥላሴ (መለኮት) ብለን የምንማረው ትምሕርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው::

+ይኼውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው:: ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርሕ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት: ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም::

+እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ:- ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው:: ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ያውቃል::

በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ: ወልድ: መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን : በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል::

+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት::

+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

በዓለ ሥላሴ በዚህ ቀን የሚከበረው ስለ 2 ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን 2ኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

#ሕንጻ_ሰናዖር

ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

+ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

+ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

+መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

+ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

+ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

#ቅዳሴ_ቤት

ልክ የዛሬ 324 ዓመት: አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት: (በ1684 ዓ/ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

+ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

+ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ/ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
17.9K views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-15 22:49:56
ጴንጤ ጥምቀት ጀመሩ እንዴ

@ortodoxmezmur
17.3K views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-15 11:33:50 ​​​​#እንኳን_አደረሳችሁ_ጥር_6_ግዝረት

ግዝረት ከጌታችን ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው፡፡ እነዚህ ንዑሳን በዓላት የሚባሉትም ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ፣ ግዝረት፣ ቃና ዘገሊላ፣ ልደተ ስምዖን፣ ደብረ ዘይት፣ የመጋቢት መስቀልና መስቀል ናቸው፡፡ ነቢያት ይወርዳል፤ ይወለዳል ብለው በትንቢት ይጠባበቁት የነበረው መሲሕ የዓለም ብርሃን፣ የነፍሳት ጠባቂ መሆኑን አምነን የምናከብራቸው ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡

ከእናቱና ከደቀመዛሙርቱ ጋር በሰርግ ቤት የተገኙበት ቃና ዘገሊላ፣ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትና አረጋዊ ስምዖንን የሰላሳ ዓመት ጎልማሳ የሆነበት “ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ዐይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና” በማለት የተናገረበት ልደተ ስምዖን ከንዑሳን በዓላት ይመደባሉ፡፡ የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግዝረት በመሆኑ ሀተታዬን ወደ እሱ እመልሳለሁ፡፡

ፍቅር ወልድን ከዙፋኑ ስቦት ወርዶ ሥጋ ማርያምን ተዋሕዶ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ማሕፀኗን ዓለም አድርጎ ከቆየ በኋላ ታኅሣሥ ሃያ ዘጠኝ በዘመነ ማቴዎስ ተወለደ፡፡ በተወለደ በስምንተኛ ቀኑ ሥርዓተ ኦሪትን ሊፈጽም ተገረዘ፡፡ ግዝረትን በስምንተኛው ቀን መፈጸሙ፣ በተወለደ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ መሔዱ ሕገ ኦሪትን ሊያጸና፣ ሊፈጽም፣ ምሳሌውን በአማናዊው ሊተካ እንጂ ኦሪትን ሊሽር ላለመምጣቱ እማኝ ምስክር ነው፡፡ የተሻረ ነገር መታሰቢያ የለውም የተፈጸመ፣ በምሳሌና በትዕምርታዊነት የተወከለ ግን ጥንተ ታሪኩን፣ ትንቢቱን ጠይቀን ምሳሌውን ከትርጓሜ መጻሕፍት እንረዳለን፡፡

ግዝረት አይሁድ የአብርሃም ልጅ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማኅተም ነው፡፡ በሕግና በሥርዐት የሚመሩ መሆናቸውን አንድ አምላክ ማመናቸውን የገለጡበት ነው፡፡ አይሁድ በግዝረት የአብርሃም ልጅነታቸውን እንዳረጋገጡ፣ ክርስቲያኖችም በጥምቀት የሥላሴ( ልጅነታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ይህም የሚሆነው ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ መሆኑን ያስረዳል፡፡ በሐዲስ ኪዳን ጥምቀት እንጂ መገረዝ፣ አለመገረዝ አይጠቅምም፡፡ በሐዲስ ኪዳን ግዝረት በፍቃድ እንጂ እንደ አይሁድ እኛም የአብርሃም ልጆች እንድንባል የምንገረዝ አይደለም፡፡

ለእኛ ለክርስቲያኖች ከሥላሴ በመንፈስ ቅዱስ መወለድ እንጂ መገረዝ የአብርሃም ልጆች አያሰኘንም፡፡ አለመገረዝ እንደማይጠቅም ቢያውቅም ጌታችን መገረዝ ያስፈለገው ሕገ ኦሪትን ለመፈጸም ሲሆን በእኔ ግን ምስጢረ ጥምቀትን ፈጽሜ አድናችኋለሁ ሲለን( ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የማይጠቅምና ለነገረ ድኅነት የማያበቃ ነገር ቢያጋጥመን እንኳ በጥበብና በማስተዋል እንድናደርገው ሲያስተምረን ነው፡፡ ሥርዐተ ኦሪታችንን ስላፈረሰብን ለሞት አበቃነው ብለው ምክንያት እንዳያገኙና ይህንን ስበብ አድርገው ከነገረ ድኅነት ተለይተው እንዳይቀሩ የሚያደርጉትን በማድረግ፣ የሚወዱትን በመውደድና አብሯቸው የሥርዐታቸው ተካፋይ በመሆን በፍቅር ስቦ ወደ አማናዊው ድኅነት፣ ወደ ጥምቀትና የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ወደማመን መልሷቸዋል፡፡

የመምህሩን አሰረፍኖት የሚከተለው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በደርቤን በሚያስተምርበት ወቅት ጢሞቴዎስ( ሲከተለው መገረዝ አለመገረዝ ጥቅምም ጉዳትም እንደሌለው እያወቀ የገዘረው( በዙሪያው ብዙ አይሁድ ስለነበሩ እነርሱን ላለማስከፋትና ላለማስደንበር መሆኑን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ “.. የኦሪት ሕግ ለማዳን ብቁ አለመሆኗን እየደጋገመ በድፍረት ይሰብክ የነበረው መምህረ አሕዛብ ቅዱስ ጳውሎስ እንኳ አይሁድን( ላለማስደንበር ሲል ሥርዐተ ኦሪትን ይፈጽም ነበር፡፡” /1978፣ 29/ በማለት ገልጸዋል፡፡

ግዝረት ለእስራኤል ከአብርሃም ለመወለዳቸው ምልክት ብቻ ሳይሆን የአብርሃምን ሃይማኖት ለመያዛቸውም መታወቂያ ነበረች፡፡ ጌታችንም ምንም እንኳ የባሕርይ አምላክ ቢሆን በሥጋ( የአብርሃም ልጅ ነውና የአብርሃም ልጅነቱን የአብርሃምን ሃይማኖት ማጽናቱን ለማስረገጥ ግዝረትን ፈጸመ፡፡

አንድም በግዝረት ደም ይፈስሳለና አብርሃም በዘጠና ዘጠኝ ዓመቱ በመገረዝና ደሙን በማፍሰስ አበ ሰማዕታት ተብሏልና ግዝረት የሰማዕትነት ምሳሌም ነው፡፡

ጥር ስድስት በሚነበበው ስንክሳር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አረጋዊ ዮሴፍን ሕፃኑን የሚገርዝ ባለሙያ ፈልጎ እንዲያመጣ እንደነገረችው፣ አረጋዊውም ባለሙያውን ፈልጎ እንዳመጣ ይናገራል፡፡ ባለሙያውም ሕፃንን በደምብ ያዙልኝ ብሎ ለመግረዝ ሲሰናዳ ባለሙያ ሆይ ደሜ ሳይፈስ መግረዝ ትችላለህን ብሎ እንደጠየቀው፣ ከስቅለቱ በፊት ደሙ እንደማይፈስ እንዳስተማረው፣ በዚህም ምክንያት ለመግረዝ የመጣው ባለሙያ፣ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን አምኖ እንደሰገደለት ለመግረዣ ያዘጋጀው ምላጭም እሳት ላይ እንደተጣደ ቅቤ መቅለጡን ይተርካል፡፡

በመቀጠልም ክርስቶስ ዘር ምክንያት ሳይሆነው እንደተፀነሰ፣ ማኅተመ ድንግልናዋን ሳይለውጥ እንደተወለደ እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል “ሳይከፈት ገብቶ ሳይከፍት እንደወጣ” ስለት ምክንያት ሳይሆነው፣ በግዝረት ምክንያት ደም ሳይፈስ በተአምራት ተገረዘ፡፡

በአጠቃላይ ግዝረት በኦሪት የአብርሃም ልጅነትን፣ የአብርሃምን ሃይማኖት መያዝን ማረጋጋጫ ማኅተም ሲሆን በሐዲስ ኪዳን በጥምቀት ተተክቷል፡፡ ለአማናዊው ግዝረት /ለጥምቀት/ ምሳሌ በመሆኑም በሥራ የአብርሃም ልጅነትን፣ በእምነት የሥላሴ ልጅነትን አግኝተንበታል፡፡ ወርደህ ተወልደህ፣ በነፍስ በሥጋ፣ ከተቆራኘን ባለጋራ አድነን ብለን የተጣራነው ተሰመቶ፣ ሥርዓተ ኦሪትን ፈጽሞ ወደ ሥርዓተ ሐዲስ የሚያሸጋግረን መሆኑን ያመንበት፣ በጥምቀቱ ቦታ በዮርዳኖስ የተቀበረው የባርነታችን ደብደቤ የሚቀደድ መሆኑን በምሳሌ ያወቅንበት ግዝረት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.9K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ