Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136.15K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 43

2023-02-01 20:48:03
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሚኒስትሮችና ለካቢኒ አባላት በሰጡት የወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ።

ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም.
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ።

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ምልዓተ ጉባኤ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ደሙ ወረዳ ሀሮ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ የሃይማኖት፣ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰት አስመልክቶ በሰፊው ተወያይቶ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት ልዩ ልዩ ሕግጋት ውጭ ጳጳስ ሾመናል ባሉ አካላት እና ተሹመናል በሚሉት አካላት ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግጋት በሚፈቅድለት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ የለያቸው ሲሆን፣ በዕለቱ ይኸው ውግዘት በመላው ዓለም ለሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮች ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምዕመናን ውግዘቱን እንዲያውቁት መንግሥትም በዚህ ጉዳይ የሚፈጠር ችግር እንዳይኖር ሰላም እንዲያስከብር ዓለም በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ መረጃ ኖሮት ቤተ ክርስቲያን ለወሰነችውም ውሳኔ ግንዛቤ እንዲወስድ በመግለጫ ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡
12.3K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 10:50:54
16.0K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 08:03:53
  ምስጢረ ሥጋዌ የክርስቶስ ሰው መሆን የመጨረሻው ክፍል | አምስቱ አዕማደ ምስጢራት |
ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!





15.8K views05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 16:43:06

ሠላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን ይህንን ዝማሬ ታዳምጡት ዘንድ እንዲሁም ለበገና ዝማሬ እና ትምህርት Subscribe ታደርጉ ዘንድ እንጋብዛለን። ለምትወዷቸው ሁሉ ሼር አድርጉላቸው ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
17.3K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 16:40:53


ሠላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን

ይህንን ዝማሬ ታዳምጡት ዘንድ
እንዲሁም ለበገና ዝማሬ እና ትምህርት Subscribe ታደርጉ ዘንድ እንጋብዛለን።

ለምትወዷቸው ሁሉ ሼር አድርጉላቸው ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
17.4K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 18:11:12 #የያሬድ_ዉብ_ዜማ

የያሬድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ
ስጦታዬ ነሺ /2/ በምን አንደበቴ
እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ/2/

ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ 
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ 
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ 
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሺ 
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ታምርሽንም በዓይኔ አይቻለሁ 
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ 
#አዝ
የእግዚአብሔር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ 
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ 
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሽ
ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኚ 
አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም 
በፊትሺም እንድቆም ለምስጋና 
ማርያም ልበልሽ በትህትና 
#አዝ
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም 
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም 
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር 
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሽን ይናገር 
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ 
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ 
ከጎኔ ነይ ስልሺ እጽናናለሁ 
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ 

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
23.3K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 09:40:09 ​​+ አበው ስለ እመቤታችን ዕረፍት እንዲህ አሉ

‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት የተለያየ ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ›› ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)

‹‹የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡

ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ (aka Doctor of Dormition)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አስተ ር እዮ ማርያም
ጎተበርግ ስዊድን

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
23.1K views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 08:38:27 #ሞትማ_ለመዋቲ_ይገባል ✞

ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪)
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(፪)

ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(፪)
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ(፪)
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(፪)
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያመልአከ ሞት፪)
#አዝ
ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(፪)
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(፪)
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(፪)
#አዝ
ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(፪)
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(፪)
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(፪)
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(፪)

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና
የመቅደስህ ታቦት።"
መዝ ፻፴፩፥፰

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
18.6K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 01:04:32 ❖ የድንግል ማርያም ወዳጆች ✞ እንኳን አደረሳችሁ

☞ አስተርዮ _ ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን
ትርጉሙም ፦ መታየት ወይም መገለጥ ማለት ነው፡፡

ጥር 21 ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት በሰማይና በምድር የተሰጣትን ፀጋና ክብር የገለፀችበት እለት ስለሆነ በዓሉም አስተርዮ ማሪያም ይባላል።

❖ የድንግል ማሪያም ጥበቃ ምልጃዋ አይለያቹ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
19.8K views22:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 22:18:37 ​​እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

† † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † †

† #ዕረፍተ_ድንግል †

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::

ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500 ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::

ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::

የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ
- ከአዳም በሴት
- ከያሬድ በሔኖክ
- ከኖኅ በሴም
- ከአብርሃም በይስሐቅ
- ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
- ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::

ከሌዊ ደግሞ በአሮን: አልዓዛር: ፊንሐስ: ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::

አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7) "ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ)

ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12 ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::

በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: (ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ)

ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14) "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ2 ዓመታት ቆዩ::

አርዌ ሔሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም: በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር ሲሆነው: ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::

በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች:: እርሷ 45 ዓመት ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3 ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::

የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች:: ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::

ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች:: በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ: ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና: ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::

ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ: ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ::
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ::" እንዲል::

ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ::
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ::
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::

በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ: እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል:: በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት ቆይታለች::

ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል::

በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ::

ለ2 ሳምንታት ቆይተው: ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል::

ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን: ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::

#ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_ሊቅ

ለዚህ ቅዱስ አባት ብጹዕ መባል ተገብቷል:: ክቡር: ምስጉን: ንዑድ ሰው ነውና:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቂሣርያ ቀዸዶቅያ የተወለደው ቅዱሱ ሰው ለደሴተ ኑሲስ ብርሃኗ ነው:: አባቱ ኤስድሮስ: እናቱ ኤሚሊያ: ወንድሞቹ ቅዱሳን "ባስልዮስ: ዼጥሮስ: መክርዮስና መካርዮስ" ይባላሉ::

የተቀደሰች እህቱም ማቅሪና ትባላለች:: ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ለቅድስና ያልበቃ አንድም ሰው የለም:: ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከማር በጣፈጠ ዜና ሕይወቱ እንደ ተጻፈው:-

በልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል::
ሥጋውያን ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድም የግሪክን ፍልሥፍና በልኩ ተምሯል:: በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል::
ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል:: እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች 11 ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር 11 ብቻ ነበር:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል:: ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን (በ381 ዓ/ም) መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል::

ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ33 ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
23.5K views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ