Get Mystery Box with random crypto!

#የያሬድ_ዉብ_ዜማ የያሬድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሺ /2/ በምን አንደበቴ እንዴት | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#የያሬድ_ዉብ_ዜማ

የያሬድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ
ስጦታዬ ነሺ /2/ በምን አንደበቴ
እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ/2/

ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ 
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ 
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ 
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሺ 
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ታምርሽንም በዓይኔ አይቻለሁ 
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ 
#አዝ
የእግዚአብሔር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ 
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ 
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሽ
ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኚ 
አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም 
በፊትሺም እንድቆም ለምስጋና 
ማርያም ልበልሽ በትህትና 
#አዝ
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም 
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም 
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር 
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሽን ይናገር 
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ 
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ 
ከጎኔ ነይ ስልሺ እጽናናለሁ 
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ 

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur