Get Mystery Box with random crypto!

#ሞትማ_ለመዋቲ_ይገባል ✞ ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪) የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል( | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ሞትማ_ለመዋቲ_ይገባል ✞

ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪)
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(፪)

ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(፪)
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ(፪)
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(፪)
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያመልአከ ሞት፪)
#አዝ
ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(፪)
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(፪)
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(፪)
#አዝ
ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(፪)
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(፪)
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(፪)
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(፪)

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና
የመቅደስህ ታቦት።"
መዝ ፻፴፩፥፰

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur