Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 136.15K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-03-12 21:34:10
ምን ያስጨንቀናል?

እንኳን ደስ አላችሁ የሥነ ልቡና የምክክር አገልግሎታችንን በአዲሱ ቢሮአችን በአዲስ መልኩ ጀምረናል።

የምንሰጣቸው አገልግሎት፦
ድብርት/ድባቴ (Depression)
ብቸኝነት(Loneliness)
የመኖር ጣዕም እና አላማን ማጣት(Purpose and meaning of life)
የተለያዩ የሱስ ፈተናዎች (Drug addictions)
የትዳር የምክክር አገልግሎት (Married therapy)
እራስን የማጥፋት ሐሳቦች(Suicidal thoughts)
ልበ-ሙሉነትን እንዴት ማምጣት እንችላለን (self-confidence)
የልጅነት መጥፎ ጠባሳ/ክስተት(Trauma)
ጭንቀት(Anxiety)
የማንነትን ቀውስ(Identity crisis)
እና ሌሎች የሚያስጨንቁንን ነገሮች ሁሉ በዓለማዊው እና መንፈሳዊ መንገድ የምክክር አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን። ከታች ባለው ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በቴሌግራም አካውንት ቴክስት በመላክ ቀድመው ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።

ቢሮአችን አዲስ አበባ ፒያሳ Downtown ሕንጻ(ፒያሳ የገበያ ማዕከል) ላይ

0912085085 ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን (Certified psychiatrist from yale,Sydney and Harvard University)

Telegram account- @Orthodoxtewahed0

ይደውሉ ይመዝገቡ የምክክር አገልግሎቱን ያግኙ።
13.5K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-12 18:13:54 ​​​«በዐቢይ ጾም የተከለከሉ»
ክፍል 2

(ለሚጠጡ፣ ለሴቶች፣ ላገቡ፣ ለወለዱ፣ ለካህናት)

የአጽዋማትን ሱታፌ አስመልክቶ የተከለከሉ ነገሮች አሉ። የሚከተሉትን እንመልከት።

“በዐቢይ ጾም ሰርግ ማድረግም አይገባም፣
ሰውን ወደ መጠጥ ቤት መጥራትም አይገባም፣
ሰው ሁሉ ከሚስቱ ጋር አይተኛ” በማለትም መጠጥ እና የባልና ሚስት ሩካቤም ተከልክሏል። (ፍት.ነገ አን 15፥592 – 593)

በተጨማሪም “በዓቢይ ጾም አያጊጡ፣ ሴቶች ጌጣቸውን ይተው፣ ሁሉም ለእያንዳንዱ በጾመ ዐርብዓ እና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይቀባዋል፣ በምንጣፍ የሚገናኙ ሰዎች ከጋብቻ ህግ የወጣ ነው፣ ክብርት በምትሆን በሰሙነ ሕማማት ይህቺን ኃጢአት የሚሠራት ወዮለት!” ብሎ ጌጥን ከልክሎ ሩካቤን በሰሙነ ሕማማት ይበልጥ መከልከሉት «ወዮለት» በሚል ቃል ጠበቅ ያደርገዋል። (ፍት.ነገ አን 15፥597)

እንደገናም “በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሳት፣ ክህነት መስጠት፣ ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም፣ በእነዚህ ቀናት ለሚሞቱ ሰዎች ግንዘትና ፍታት በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጂ” (ፍት.ነገ አን 15፥600) ካለ በኋላ ቁጥር 601 ላይ “በዓርባው ቀናትም ደስታ ማድረግ መጋባት ክህነት መሾም ክርስትና ማንሳት አይገባም፤ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል” በማለት ልዩ ምክንያትን (Exception) ብቻ ክርስትና ለማንሳት በመፍቀድ አዝዘዋል።

“በዐቢይ ጾም የሰማእታት በዓል ልናከብር አይገባም፣ የሰማእታት መታሰቢያ በእሑድ በቅዳሜ ይሁን እንጂ” (ፍት.ነገ አን 15፥591) በማለት የንግሥ ክብረ በዓላት በተለይ ከሰንበት ውጪ ባሉት ዕለታት ተከልክለዋል።

ጾም ላይ ብቻ ሳይሆን ትንሳኤንም ጨምሮ “በዕለተ እሑድ የትንሳኤ ዕለት ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም” (ፍት.ነገ አን 15፥601) በማለት ይከለክላል።

“ዓቢይ ጾምንና እሮብንና አርብን የማይጾም ሰው ካህን ከሆነ ይሻር ምእመን /ሕዝብ/ ቢሆን ይለይ” የሚልም ለውግዘት የሚያበቃም ህግ አለ። (ፍት.ነገ.አን 15፥589)

በተቃራኒው ከካህናት ወገን የማይገባ ጾም የጾመም የተከለከለ መሆኑን “ከስዑር ቅዳሜ ዉጪ ሰንበታን የጾመና በሰሙነ ሕማማት ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል የቀኑን ሥርዓት አስቀድሞ ቢያውል ከክህነቱ ይሻር” ተብሏል። (ፍት.ነገ.አን 15፥590) ለምመን ደግሞ ቀኖና የሚያስፈልገው መሆኑ ነው።

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
14.1K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-12 14:15:44 በጾም

በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ
ወበጸሎት ትትሐሠይ መንፈስ /2/

መአልትና ሌሊት በጾም ጸሎት ተግቶ
አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ
አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት
ስጋ ካልደከመች በጾምና ጸሎት
አዝ
ሙሴ የተባለው ያ የእግዚአብሔር ሰው
ፊቱን የበራለት አርባ ቀን ጾሞ ነው
በሲና ተራራ ተቀብሎ ህግን
እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድን
አዝ
የጸሎት እናቷ ስለሆነች ጾም
ትህትናን ይዘን ደግሞም አንድ ሆነን
ብንተጋ በጸሎት ከንስሐ ጋራ
ጾም ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ
አዝ
አንድበትም ይጹም ዓይንም ይረጋጋ
ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ
ድሀን ከመበደል ልብም ተመልሶ
መጾምስ እንዲህ ነው የበደለን ክሶ

ዘማሪ መምህር አቤል ተስፋዬ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
14.5K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-12 09:01:19 ✥ የዐቢይ ፆም የመጀመሪያ ሳምንት ✥

• በመምህር ዶ/ር ዘነበ ለማ •
═════●◉❖◉●══════
✥ ዘወረደ ✥
═════●◉❖◉●══════
✢ Share ✢
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
15.0K viewsedited  06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-11 17:17:39  ✞ ዘወረደ
"በእርሱ ፍቃድ"

በእርሱ ፍቃድ በአባቱ ፍቃድ
በመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ
ከሰማያት ወረደ
ከድንግል ማርያም ተወለደ

ዓለሙን እንዲሁ ወደደና
ከሰማያት በላይ ወረደና
በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት
ተወሰነ አምላከ አማልክት
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
ኢየሱስ ፈራጅ ነዉ
አዝ
ቅድመ ዓለም ተወልዶ ያለ እናት
ድህረ ዓለምም ያለ አባት
የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥም ሰው ሆነ
ሁሉ በእርሱ ይኸው ተከናወነ
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
ክርስቶስ አምላክ ነዉ
አዝ
የማይታይ ታየ በምድር
ረቂቁ ገዘፈ ስለፍቅር
ሥጋን ተዋህዶ ሆነልን ፈውስ
አማኑኤል የነገስታት ንጉሥ
ከሰማያት የወረደው
ፍቅር ስቦት የመጣዉ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም
እግዚአብሔር እርሱ ነዉ
   
ዲ/ን ቀዳሜጸጋ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
17.2K views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-11 15:48:49 ​​ዘወረደ

የመጀመሪያ የአቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ «ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ዮሐ.3-13፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ”ገላ 4፥4 እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ።

ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው፡፡

ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው። እኛም በዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀር እንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ።

በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ በሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም በመፆም ልዑል እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን።

ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
17.4K views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-11 07:22:32 ​​​«በዐቢይ ጾም የተከለከሉ»
ክፍል 2

(ለሚጠጡ፣ ለሴቶች፣ ላገቡ፣ ለወለዱ፣ ለካህናት)

የአጽዋማትን ሱታፌ አስመልክቶ የተከለከሉ ነገሮች አሉ። የሚከተሉትን እንመልከት።

“በዐቢይ ጾም ሰርግ ማድረግም አይገባም፣
ሰውን ወደ መጠጥ ቤት መጥራትም አይገባም፣
ሰው ሁሉ ከሚስቱ ጋር አይተኛ” በማለትም መጠጥ እና የባልና ሚስት ሩካቤም ተከልክሏል። (ፍት.ነገ አን 15፥592 – 593)

በተጨማሪም “በዓቢይ ጾም አያጊጡ፣ ሴቶች ጌጣቸውን ይተው፣ ሁሉም ለእያንዳንዱ በጾመ ዐርብዓ እና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይቀባዋል፣ በምንጣፍ የሚገናኙ ሰዎች ከጋብቻ ህግ የወጣ ነው፣ ክብርት በምትሆን በሰሙነ ሕማማት ይህቺን ኃጢአት የሚሠራት ወዮለት!” ብሎ ጌጥን ከልክሎ ሩካቤን በሰሙነ ሕማማት ይበልጥ መከልከሉት «ወዮለት» በሚል ቃል ጠበቅ ያደርገዋል። (ፍት.ነገ አን 15፥597)

እንደገናም “በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሳት፣ ክህነት መስጠት፣ ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም፣ በእነዚህ ቀናት ለሚሞቱ ሰዎች ግንዘትና ፍታት በሆሣዕና በዓል ቀን ይነበብ እንጂ” (ፍት.ነገ አን 15፥600) ካለ በኋላ ቁጥር 601 ላይ “በዓርባው ቀናትም ደስታ ማድረግ መጋባት ክህነት መሾም ክርስትና ማንሳት አይገባም፤ ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና ይደረግለታል” በማለት ልዩ ምክንያትን (Exception) ብቻ ክርስትና ለማንሳት በመፍቀድ አዝዘዋል።

“በዐቢይ ጾም የሰማእታት በዓል ልናከብር አይገባም፣ የሰማእታት መታሰቢያ በእሑድ በቅዳሜ ይሁን እንጂ” (ፍት.ነገ አን 15፥591) በማለት የንግሥ ክብረ በዓላት በተለይ ከሰንበት ውጪ ባሉት ዕለታት ተከልክለዋል።

ጾም ላይ ብቻ ሳይሆን ትንሳኤንም ጨምሮ “በዕለተ እሑድ የትንሳኤ ዕለት ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም” (ፍት.ነገ አን 15፥601) በማለት ይከለክላል።

“ዓቢይ ጾምንና እሮብንና አርብን የማይጾም ሰው ካህን ከሆነ ይሻር ምእመን /ሕዝብ/ ቢሆን ይለይ” የሚልም ለውግዘት የሚያበቃም ህግ አለ። (ፍት.ነገ.አን 15፥589)

በተቃራኒው ከካህናት ወገን የማይገባ ጾም የጾመም የተከለከለ መሆኑን “ከስዑር ቅዳሜ ዉጪ ሰንበታን የጾመና በሰሙነ ሕማማት ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል የቀኑን ሥርዓት አስቀድሞ ቢያውል ከክህነቱ ይሻር” ተብሏል። (ፍት.ነገ.አን 15፥590) ለምመን ደግሞ ቀኖና የሚያስፈልገው መሆኑ ነው።

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
13.6K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 21:25:44 ​​«ጾም እስከ ስንት ሰዓት ነው?»
ክፍል 1


እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! ?
የቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን ሥርዓቱ በልኬት እና በምክንያት የታጀበ ነው። ጾምን ስንመለከት አብዛኞቻችን በተለምዶ ሰዓት ሳንጠብቅ (እስከ 3፣ 6፣ 7፣ 9፣ 11 ሰዓታት እያልን) እንጾማለን እንጂ የአዋጅ አጽዋማት የተወሰነ የተገደበ ሰዓት አላቸው።

ፍትሐ ነገሥታችን “ሕማማት እስከ 12 ሰዓት ይጹሟቸው፥ ሌሎቹን አጽዋማት በዓለ ልደት እና ጥምቀት ረቡዕ እና ዐርብ የሚውሉባቸው ካልሆኑ በቀር እስከ 9 ሰዓት ይጹሙ” (ፍት.ነገ አን 15፥565-566) ብሏል።

የአጽዋማትን ዝርዝር ካስቀመጠ በኋላም በዚሁ አንቀጽ ቁጥር 572 ላይ ደግሞ “በእነዚህ በታዘዙት ጾሞች ከቀኑ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ይጹሙ፣ ... ከዚህ አብልጦ የጾመ ግን ዋጋው ይበዛለታል፣ ከጥሉላት ምግቦች መታቀብ ካልሆነ በቀር እሑድና ቅዳሜ ግን አይጹሙ” ብሎ ወስኗል።

ዐቢይ ጾም ሁዳዴ፣ ጾመ ዐርብዓ ግን ይለያል። “በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ ይጹሙ፣ ሌሎቹን ሳምንታት እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ፥ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ይጹሙ” ብለዋል። (ፍት.ነገ.አን 15፥595)።

ፍትሐ ነገሥት ቁጥር 578 ላይ ደግሞ “(የሰሙነ ሕማማትን) ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ይጹሟቸው፣ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው፣ ሁለቱን በአንድነት መጾም የማይቻለው ግን ቅዳሜን ይጹም” ተብሎ ህግ ተሠርቷል።

ይቀጥላል
በቀጣይ ክፍል በዐቢይ ጾም የተከለከሉ ነገሮች ምንድን ናቸው?

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
14.4K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 21:13:54 እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም
      አደረሳቹ አደረሰን!

"ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥"
ትንቢተ ኢዮኤል 2:15
13.1K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 13:22:08 ​​​​ዐቢይ ጾም

ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ አቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡

ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡-

. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ

. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ

. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም 'ትዕቢት' 'ስስት' 'ፍቅረ ነዋይ' ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡

በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡-

1. ዘወረደ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡

2. ቅድስት
ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡

3. ምኩራብ
ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡

4. መጻጉዕ
ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡

5. ደብረ ዘይት
ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡

6. ገብርኄር
ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡

7. ኒቆዲሞስ
ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡

8. ሆሳዕና
ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
17.8K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ