Get Mystery Box with random crypto!

በጾም በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ ወበጸሎት ትትሐሠይ መንፈስ /2/ መአልትና ሌሊት በጾም | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በጾም

በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ
ወበጸሎት ትትሐሠይ መንፈስ /2/

መአልትና ሌሊት በጾም ጸሎት ተግቶ
አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ
አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት
ስጋ ካልደከመች በጾምና ጸሎት
አዝ
ሙሴ የተባለው ያ የእግዚአብሔር ሰው
ፊቱን የበራለት አርባ ቀን ጾሞ ነው
በሲና ተራራ ተቀብሎ ህግን
እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድን
አዝ
የጸሎት እናቷ ስለሆነች ጾም
ትህትናን ይዘን ደግሞም አንድ ሆነን
ብንተጋ በጸሎት ከንስሐ ጋራ
ጾም ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ
አዝ
አንድበትም ይጹም ዓይንም ይረጋጋ
ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ
ድሀን ከመበደል ልብም ተመልሶ
መጾምስ እንዲህ ነው የበደለን ክሶ

ዘማሪ መምህር አቤል ተስፋዬ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur