Get Mystery Box with random crypto!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @muradtadesse
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 84.99K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 344

2022-08-31 18:15:54 የፈጅር (የሱብሒ) ሶላት የደረሰ ጊዜ «ተነስ! ሂድና መስጅድ ስገድ!» አለችው። «እዚሁ ነው የምሰግደው!» አላት። «ሸሪዓው'ኮ ወንዶች መስጅድ ሂዳችሁ በጀማዓህ እንድትሰግዱ አዟል!» አለችው። «ሸሪዓው'ማ ከ1 በላይ እስከ አራት ማግባትንም ፈቅዷል!» አላት።

እርሷም ፈጠን አለችና «መስገጃውን እዚህ ላንጥፍልህ ወይንስ ሳሎን?» አለችው።

ከዚያ በኋላ ምን እንደተከሰተ አልሰማሁም¡



(የሰሙ ሰዎች ከሱ-ን'ናው ይልቅ ፈርዱን ላስቀድም ብሎ መስጂድ ሂዶ ሰግዷል ብለውኛል። ከፈርዱ ባሻገር ሱ-ን'ናውን ስለመተግበሩ ግን እነርሱም የሰሙ አይመስለኝም¡)
9.3K viewsedited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:06:58 የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«ፍጻሜውን ሳትመለከቱ ማንም በሚሠራው ሥራ አትደነቁ።»
[ሲልሲለቱ-ስ'ሶሒሓህ: 1334]
8.8K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:05:31
8.8K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:14:02 አስተውላችሁ ከሆነ…
በአሁኑ ወቅት ከበርካታ የዘመናችን ከተሜ ሴቶች ይልቅ ገጠሬ ወንዶች የተሻለ ሐያእ አላቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም።


እኛ'ኮ ድሮ በዘመናችን ሴት ቁሞ ሲያወራን እንኳን ቀና ብለን ልናይ ላባችን ግጥም ብሎ ይሸፍነን ነበር።

ዛሬ'ማ ጭራሽ የሴት ደፋሪም መጣ እያላችሁ ነው!

ነስአሉልሏሃ ሰላመተ ወልዓፊያህ!
9.3K viewsedited  14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:07:52
በተቃራኒው ደግሞ የበፊቱ ህገ ወጥ መጅሊስ የነገውን ስብሰባ በመቃወም ይህንን ደብዳቤ ለአማራ ክልል መንግስት ጽፏል። ህገ ወጡ ማን እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ስለሆነ፤ ህግ የሚከበር ከሆነ ይህንን ደብዳቤ የጻፉ የቀድሞ የመጅሊስ አባላት በቀጥታ ወደ እስር ቤት መወርወር አለባቸው።


ደስ የሚለው ነገር «ኦዲትዬ» እየመጣች ነው!

ደግሞ የነዚህስ ዓይን አውጣነት ይለያል።
9.2K viewsedited  14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:01:35
የአማራ ክልል መጅሊስ ምርጫ በነገው ዕለት ይካሄዳል። በመጅሊስ ጉዳይ ከሁሉም ክልል በላይ ይበልጥ የተጎዳው ይህ ክልል፤ በአላህ ፈቃድ የተሻሉ መሪዎች እንዲሾሙበት እንመኛለን። አላህ ያግዛቸው።
8.7K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:59:15
1.7K views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:54:18
ከቻልክ ከሰዎችም በላይ ለአላህ የበለጠ ሐያእ ይኑርህ። ቢያንስ ግን ከሰዎች ሐያእ የምታደርገውን ያክል ሐያእ አድርግ። ሰዎች ፊት ለማድረግ የምታፍረውን ነገር አላህ ፊት እንደት ታደርጋለህ? መብራትም ይጥፋ፣ በሩም ይዘጋ፣ ከሰዎችም ተሰወር፤ ብቻ ግን በየትኛውም ሁኔታ ከአላህ እይታ በፍጹም አትሰወርም። አስተውል!
||
t.me/MuradTadesse
1.9K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:50:30
እነዚህን 4 ነገሮች አስተውሉ!
1.9K views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:22:19
(…أَلَا إِنَّ اللهَ عَزَّ وَجَلَّ يَضْحَكُ إِلَى رَجُلَيْنِ :
رَجُلٍ قَامَ فِي لَيْلَةٍ بَارِدَةٍ مِنْ فِرَاشِهِ وَلِحَافِهِ وَدِثَارِهِ ، فَتَوَضَّأَ ، ثُمَّ قَامَ إِلَى صَلَاةٍ، فَيَقُولُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ لِمَلَائِكَتِهِ: مَا حَمَلَ عَبْدِي هَذَا عَلَى مَا صَنَعَ؟ فَيَقُولُونَ: رَبَّنَا رَجَاءَ مَا عِنْدَكَ، وَشَفَقَةً مِمَّا عِنْدَكَ، فَيَقُولُ: فَإِنِّي قَدْ أَعْطَيْتُهُ مَا رَجَا ، وَأَمَّنْتُهُ مِمَّا خَافَ .
وَرَجُلٍ كَانَ فِي فِئَةٍ ، فَعَلِمَ مَا لَهُ فِي الْفِرَارِ، وَعَلِمَ مَا لَهُ عِنْدَ اللهِ ، فَقَاتَلَ حَتَّى قُتِلَ فَيَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ: مَا حَمَلَ عَبْدِي هَذَا عَلَى مَا صَنَعَ؟، فَيَقُولُونَ: رَبَّنَا رَجَاءَ مَا عِنْدَكَ ، وَشَفَقَةً مِمَّا عِنْدَكَ .
فَيَقُولُ: فَإِنِّي أُشْهِدُكُمْ أَنِّي قَدْ أَعْطَيْتُهُ مَا رَجَا وَأَمَّنْتُهُ مِمَّا خَافَ " أَوْ كَلِمَةً شَبِيهَةً بِهَا ".)

رواه الطبراني في "الكبير" (8532) .
2.7K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ