Get Mystery Box with random crypto!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

የሰርጥ አድራሻ: @muradtadesse
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 85.94K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 347

2022-08-31 22:09:41
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ [Part: ③⑥④]


#ቁርኣን
5.0K views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:00:39
በዚህ ወንድማችን ጉዳይ የተጨነቃችሁ ካላችሁ፦
የሰራዊቱ አመራሮች ሐዘን ላይ ሁነው የሚሠቃዩትን ደካማ እናቱን ከጭንቀት አሳርፈው ለማሳደር በተሰጣቸው የእጅ ስልክ ደውለው " ..መጥታችሁ መውሰድ ትችላላችሁ! ሁሉንም ነገር አጣርተናል! አሁን ካልደረሳችሁና ምናልባት ለቀነው ሊጠፋ ስለሚችል ነገ እስክትመጡ እዚሁ ይደር!" ሲሉ ቀልባቸውን አሳርፈዋቸዋል፡፡


መልዕክቱን ያሰራጫችሁ በሙሉ ትመሰገናላችሁ።
5.8K views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:52:36
አንድ መታወቅ ያለበት ነገር… ከትናንት በፊት ጀምሮ እስከ ትናንት ምሳ ሰዓት ድረስ ከወልዲያ እስከ ኮምቦልቻ ባሉ ከተሞች በሚገኘው ማኅበረሰብ ዘንድ አለመረጋጋት ነበር። ወልዲያ በህወሃት ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውላለች ተብሎ ስለተወራ የባለፈው አይነት ክስተት ዳግም ሊከሰት ነው በሚል ብዙዎች ጓዛቸውን ሸክፈው ከተማቸውን ለቀው ለመውጣት ሞክረዋል።


ትናንት ከዙህር በኋላ ጀምሮ መረጋጋት የተስተዋለውና ባንኮችም ወደ መደበኛ ሥራቸው የተመለሱት፤ የወልዲያ አለመያዝ ስለተረጋገጠና ግምባር ላይም ሌሎች አንጻራዊ ለውጦች ስላሉ ነው። ህዝቡ አሁን ሲረጋጋ ጦርነቱ የቆመ ነው የሚመስለው። እውነታው ግን ግምባር ላይ ህይዎታቸውን እየገበሩ ለሌላው መረጋጋት መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ ጀግኖች መኖራቸው ነው። ጦርነቱ በአንድ ሃገር ዜጎች መካከል የሚደረግ መሆኑ የሚያሳፍር ቢሆንምና በውይይት መፈታት የሚችል ቢሆንም፤ ያለ ሐቃቸው ተወረው ቀያችንን አናስደፍርም ብለው ጠላታቸውን እየተዋጉ የሚገኙት የወርቄ ጀግኖችን አለማድነቅ አይቻልም። ከነርሱ መካከል ሟቾችን አላህ ከሸሂዶች ጎራ ይመድባቸው፣ የቆሰሉትን አላህ ዓፊያቸውን ይመልስላቸው። እነዚህ ጀግኖች በሚያደርጉት ተጋድሎ የሚገኘውን ድል ከተማ ውስጥ ሆቴል ላይ ተወሽቆ የሚያወራ «የምስራቅ አማራ ፋኖ፣ ገለመሌ…» የሚባል የዩ ቲዩብና የፌስቡክ አውደልድል በሐሰት ድላቸውን ሊቀማቸው አይገባም። ቢያንስ እያፈራችሁ!


የሚመለከተው የመንግስት አካልና ህዝቡ ለዚህ አካባቢ ወገኖቻችን ተገቢውን ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል። አሁንም ቢሆን ከጦርነት ይልቅ የሰላም አማራጮችን መጠቀም አይዘንጋ።

አላህ ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን።
||
t.me/MuradTadesse
5.7K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:37:54 «ያ ረሱለላህ
"ራሴን ልሰጠዎት ፈልጌ ነው የመጣሁት" (ከኔ የሚፈልጉት ጉዳይ አለ?) ብላ የትዳር ፍላጎቷን አንጸባረቀች። ነብዩም  صلى الله عليه وسلم ቀና ብለው (አተኩረው) አይዋት። ከዚያም አቀረቀሩ። እሷም ምላሽ ሳታገኝ ለረጂም ሰአት ስትቆይ ይሄን የታዘበው ባልደረባቸው رضي الله عنه ያ ረሱለላህ ኧረ ለኔ ዳሩኝ ብሎ ጠየቃቸው። ለሷ ስጦታ የሚሆን ነገር (መህር) አለህን ብለው ጠየቁት----? ቡኻሪ ዘግበውታል።

-----------------------------------
አግባኝ ማለት እንደምትችዪ

ወንድ ልጅ ዝምታው አለመፈልግን ጠቋሚ ሊሆን እንደሚችል

አግባኝ ያለችን ሴት አይ ማግባት አልችልም፣ አይሆንልኝም ማለት ግፍ እንዳልሆነ

ማጨት የፈለገ ማየት ብቻም ሳይሆን ደጋግሞና አስተውሎ ማየት እንደሚፈቀድለት

ተመልካች ወንዶች ባሉበት ቦታ አግባኝ ማለት፣ መቆም፣ መልሱን ቁጭ ብሎ መጠበቅ፣ ወንዶችን ማውራት እንደምትችይ (ድምጽሽ ዐውራህ እንዳልሆነ)»

منقول
6.2K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:25:55
6.7K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:09:29
ሰው ሲጨክን አዕዋፋት ሊዘይሩን ይሆን?
7.4K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:54:46 ".....It was sensless እኮ? መቶ ማንሞላ ሰዎች (ተነጋግረን) ልንፈታ የምንችለውን ችግር በመቶሺዎች እንዲያልቁ አደረገ..."

Jawar Muhammed
8.8K viewsedited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:39:17 እውነት ለመናገር በእናትና አባቱ ዘንድ ተወዳጅ እንደሆነ ልጅ፣ ሁሌም ዱዓእ እንደሚያደርጉለትና እንደተቀመረቀ ልጅ የሚያስቀና የለም።

የዛሬ ልጆች ግን በብዛት በወላጆቻችን እንኳን ልንመረቅ ባልተረገምንና ቀልባቸው ባላገኘን!

ወላጆቻችን በህይዎት ካሉ እንጠቀምባቸው። ወደ አኺራህ ሂደው ከሆነ ትልቁ ለሟች የሚደረገው ነገር ዱዓእ ነውና አላህ እንዲምራቸው ዘወትር ዱዓእ ከማድረግ በተጨማሪ ከሷሊሕ ልጅ ለሟች ወላጅ የሚጠበቁ በጎ ተግባራትን ሁሉ እናድርግላቸው።

በህይዎት ካሉ ግን በነርሱ ሰበብ ምንዳ መሸመት ባንችል እንኳ ቢያንስ ከእርግማናቸው ለመጠበቅ እንሞክር።
እነርሱ ማለት'ኮ ሳይማሩ ያስተማሩን፣ ለራሳቸው እየተራቡ እኛን ያበሉን፣ ለነርሱ የተቀዳደደና የቆሸሸ ልብስ ለብሰው እኛ ከጓደኞቻችን አንሰን የበታችነት ስሜት እንዳይሰማን ያለ አቅማቸው ብራንድ ያለበሱን፣ እየደከሙ ያጠነከሩን፣ የመኖራቸው ተስፋ፥ የዓይናቸው ማረፊያ፥ የህሊናቸው መርጊያ ያደረጉን… ናቸው።

ሐቂቃ እነርሱ በልጅነት ጊዚያችን ያደረጉልንን ነገር በተወሰነ መልኩ የምንረዳው እኛንም አላህ ወፍቆን ልጅ በሰጠን ጊዜ እንጂ የነርሱ ውለታ በምን ይለካል! አላህ እርሱን በብቸኝነት ከማምለክ ቀጥሎ ለነርሱ መልካም መዋልን ማዘዙ የጉዳዩን ከባድነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል።


አላህ ይወፍቀን!
9.0K viewsedited  16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:25:11
«መጽሐፉ (የሥራ መዝገቡን ሲያየው) እንዲያስደስተው የፈለገ ሰው፤ ኢስቲጝፋርን (አላህን ምህረት መጠየቅን) ያብዛ።»
9.3K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 18:15:54 የፈጅር (የሱብሒ) ሶላት የደረሰ ጊዜ «ተነስ! ሂድና መስጅድ ስገድ!» አለችው። «እዚሁ ነው የምሰግደው!» አላት። «ሸሪዓው'ኮ ወንዶች መስጅድ ሂዳችሁ በጀማዓህ እንድትሰግዱ አዟል!» አለችው። «ሸሪዓው'ማ ከ1 በላይ እስከ አራት ማግባትንም ፈቅዷል!» አላት።

እርሷም ፈጠን አለችና «መስገጃውን እዚህ ላንጥፍልህ ወይንስ ሳሎን?» አለችው።

ከዚያ በኋላ ምን እንደተከሰተ አልሰማሁም¡



(የሰሙ ሰዎች ከሱ-ን'ናው ይልቅ ፈርዱን ላስቀድም ብሎ መስጂድ ሂዶ ሰግዷል ብለውኛል። ከፈርዱ ባሻገር ሱ-ን'ናውን ስለመተግበሩ ግን እነርሱም የሰሙ አይመስለኝም¡)
9.3K viewsedited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ