Get Mystery Box with random crypto!

ሌሎች አይዶል ሾው ስላላቸው እኛ አይዶል ሾው ሊኖረን ግድ አይደለም። ሌሎች መዝሙር ስላላቸው እኛ | Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

ሌሎች አይዶል ሾው ስላላቸው እኛ አይዶል ሾው ሊኖረን ግድ አይደለም። ሌሎች መዝሙር ስላላቸው እኛ መዘመር አይጠበቅብንም። ሌሎች የቢድዓና የዘመን መለወጫ በዓል ካላቸው እኛ እንድናከብር አንገደድም። ምክንያቱም እኛ ሌሎች እነርሱም ሌሎች ናቸው። እኛ ሌሎችን አንሆንም አልተፈቀደልንምና።

ሙስሊሞች በሁሉም ቦታ መሳተፍ አለብን ብለን ሙዚቃ አንዘፍንም፣ አልኮል ቤት አንከፍትም፣ የወለድ ግብይት ውስጥ አንገባም። ልክ እንዲሁ ሁሉ ሙስሊሙ በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ አለበት ብለን የኩፍር ፖለቲካ ውስጥ አንዘፈቅም። የኢስላም ህግና መንገድ ሁሉ ከሌሎች ልዩ ስለሆነ።

ሌሎች ያደረጉትን ሁሉ እኛ "ኢስላማዊ" እያልን የምናደርገው ከሆነማ ከሌሎች በምን ተለየን? ኢስላም የመጣው ደግሞ ከሌሎች ሊለይ ነው። የኢስላምና የኩፍር መንገዶች የተለያዩ ናቸው፤ አይቀላቀሉም፤ አይገናኙም። ይህንንም ድንበር ለማስጠበቅ ሸሪዓ ከሌሎች ጋር መመሳሰልን በጥቅሉ ከልክሏል።

አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፦
«ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደእነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው።»
[አል-ሐዲድ፡ 16]

ኢብኑ ተይሚ-ይ'ያህ እንዲህ ይላል፦
«እንደእነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ ማለቱ አጠቃላይ ከነርሱ ጋር መመሳሰልን መከልከሉ ነው። በተለይም ደግሞ ከነርሱ ጋር በቀልብ መድረቅ በኩል ከመመሳሰል መከልከሉ ነው። የልብ መድረቅ ደግሞ የወንጀሎች ፍሬ ነው።»
[ኢቅቲዳኡ ሲራጦ-ል-ሙስተቂም ፡43]»

ኢስማዒል ኑሩ