Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

የቴሌግራም ቻናል አርማ egbcc — የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
የቴሌግራም ቻናል አርማ egbcc — የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
የሰርጥ አድራሻ: @egbcc
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.31K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።
"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 18:44:17
194 viewsMelaku Syume, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:58:53
533 viewsMelaku Syume, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:58:44 የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ፍቅር እና ሰላምን መስበክ ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን
********
የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ፍቅር እና ሰላምን መስበክ እንዲሁም የአብሮነት እሴቶችን ማጠናከር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር "የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለአብሮነት እሴቶች መጠናከር" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃኑ ትውልድን በሃይማኖት መርሆዎች በመቅረጽ ለሰላም ግንባታ ሚናቸው የላቀ ነው ያሉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ፣ የችግሮች መንስኤ ከመሆን መቆጠብ ይኖርባቸዋልም ብለዋል።
በአንዳንድ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የሌሎችን ሃይማኖት አለማክበር እና ማንቋሸሽ ይስተዋላል ያሉት ዳይሬክተሩ ይህ አካሄድ ሊታረም እንደሚገባ ገልፀዋል።
በዘላቂነት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሃይማኖት ሚዲያ ካውንስልን ለማቋቋም የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መደረሱንም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣  በአገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተሸረሸሩ የመጡ እሴቶች መበራከት እና በየቦታው የሚፈጠሩ ችግሮች የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የቤት ስራዎቻቸውን ላለመስራታቸው ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
በርካታ አማኞች ያሉባት አገሪቱ የሚገዳደል እና መንገድ የሚዘጋ ትውልድ ተበራክቶባታል ያሉት ዋና ፀሐፊው መገናኛ ብዙሃኑ ከመነቃቀፍ ይልቅ መደጋጋፍን እኛ እና እነሱ ከሚል የጥላቻ ትርክት በላይ  አብሮነትን መስበክ አለባቸው ብለዋል።
ተገቢ ባልሆነ አካሄድ ውስጥ እየተጓዙ ለሚገኙ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃንም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ሰላምን እንዲሰብኩ እንመክራለን ያሉት ዋና ፀሐፊው፣ ይህ ካልሆነ ግን በሕግ የሚጠየቁበት ሁኔታ መኖሩን አብራርተዋል።
@Ethiopian Broadcasting Corporation
540 viewsMelaku Syume, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:43:58 ታዋቂው ሰባኪና ጸሃፊ ሪክ ዋረን ከ43 አመታት አገልግሎት በኋላ የመጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ማቅረቡን ክርስቲያን ሄድ ላይንስ ዘገበ።
‘አላማ መር ህይወት’ የተሰኘው በበርካታ ቋንቋዎች የተተረጎመው ታዋቂ መጽሃፍ ጸሃፊ መጋቢ ሪክ ዋረን ለ43 አመታት የሳድል ባክ ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን የአገልግሎቱ መጨረሻው የሆነውን ስብከቱን ከ40 አመታት በፊት በአገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ ‘ህይወታችሁን ዘለአለማዊ ዋጋ ባለው ላይ አውሉት’ በማለት በድጋሚ ሰብኳል።
በአሜሪካ ካሊፎርኒያ የሚገኘው ሳድል ባክ ቤተክርስቲያን 40,000 አባላት ያሉት ሲሆን ከ 40 አመታት በፊት በፈረንጆቹ 1980 ዓ.ም በሪክ ዋረን እና ባለቤቱ ኬይ ዋረን በላግና ሂልስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረ ቤተክርስቲያን ነው።
መጋቢ ሪክ ዋረን የአገልግሎቱ መጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ያቀረበው በአንድ የቤተክርስቲያኒቱ አባል በተሰራውና በመጀመሪያዎቹ 15 ዓመታት ይጠቀምበት በነበረው የእንጨት ፑል ፒት ላይ ሲሆን "ለ43 ዓመታት እናንተን መውደድ፣ ለእናንተ መጸለይ፣ ማገልገል ፣ መቃብር አጠገብ ቆሜ ማጽናናት ፣ አልጋ አጠገብ ቆሜ ማበረታታት፣ ሰርጋችሁ ላይ መሰበክ ፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት መምከር እና ማስተማር እግዚአብሄር ለእኔ የሰጠኝ ትልቅ ዕድል ነበር በማለት ምዕመናኑን አመስግኗል።
526 viewsMelaku Syume, 15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:58:49

565 viewsMelaku Syume, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:04:52
604 viewsMelaku Syume, 12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:04:42 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 18ኛው የካዉንሰል ስብሰባ ተጠናቀቀ።
ከነሐሴ 17-21/2014 ዓ.ም በመካነየሱስ ሴሚናሪየም ዶ/ር አማኑኤል ገ/ስላሴ አዳራሽ የተከናወነው ስብሰባ የተለያዩ የስራ ክፍሎችን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳቦችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡
በስብሰባው ማጠቃለያም ቤተክርስቲያኒቱን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚያገለግሉ ሰዎች የተመረጡ ሲሆን በዚህም መሰረት ቄስ ተሾመ አመኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ጸሐፊ፥ወንጌላዊ ታገሰች ዳኜ የሴቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ፥ አቶ ገመችስ ማቲዮስ የአስተዳደርና ፋይናስ መምሪያ ዳይሬክር ፥ አቶ ጉማቸው ኩሴ የስቲዋርድ ሺፕና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ ገመችስ ዲዲ የምስራች ድምጽ መገናኛ ዘዴዎች ዳይሬክተር ሆነው እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊ ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሃያ አንደኛው አብይ ጉባኤ በመጪው ጥቅምት ይካሄዳል፡፡
@The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY)
818 viewsMelaku Syume, 12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:21:31

772 viewsMelaku Syume, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:35:18

988 viewsMelaku Syume, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ