Get Mystery Box with random crypto!

ታዋቂው ሰባኪና ጸሃፊ ሪክ ዋረን ከ43 አመታት አገልግሎት በኋላ የመጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ማቅረ | የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

ታዋቂው ሰባኪና ጸሃፊ ሪክ ዋረን ከ43 አመታት አገልግሎት በኋላ የመጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ማቅረቡን ክርስቲያን ሄድ ላይንስ ዘገበ።
‘አላማ መር ህይወት’ የተሰኘው በበርካታ ቋንቋዎች የተተረጎመው ታዋቂ መጽሃፍ ጸሃፊ መጋቢ ሪክ ዋረን ለ43 አመታት የሳድል ባክ ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን የአገልግሎቱ መጨረሻው የሆነውን ስብከቱን ከ40 አመታት በፊት በአገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ ‘ህይወታችሁን ዘለአለማዊ ዋጋ ባለው ላይ አውሉት’ በማለት በድጋሚ ሰብኳል።
በአሜሪካ ካሊፎርኒያ የሚገኘው ሳድል ባክ ቤተክርስቲያን 40,000 አባላት ያሉት ሲሆን ከ 40 አመታት በፊት በፈረንጆቹ 1980 ዓ.ም በሪክ ዋረን እና ባለቤቱ ኬይ ዋረን በላግና ሂልስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረ ቤተክርስቲያን ነው።
መጋቢ ሪክ ዋረን የአገልግሎቱ መጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ያቀረበው በአንድ የቤተክርስቲያኒቱ አባል በተሰራውና በመጀመሪያዎቹ 15 ዓመታት ይጠቀምበት በነበረው የእንጨት ፑል ፒት ላይ ሲሆን "ለ43 ዓመታት እናንተን መውደድ፣ ለእናንተ መጸለይ፣ ማገልገል ፣ መቃብር አጠገብ ቆሜ ማጽናናት ፣ አልጋ አጠገብ ቆሜ ማበረታታት፣ ሰርጋችሁ ላይ መሰበክ ፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት መምከር እና ማስተማር እግዚአብሄር ለእኔ የሰጠኝ ትልቅ ዕድል ነበር በማለት ምዕመናኑን አመስግኗል።