Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 18ኛው የካዉንሰል ስብሰባ ተጠናቀቀ። ከነ | የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 18ኛው የካዉንሰል ስብሰባ ተጠናቀቀ።
ከነሐሴ 17-21/2014 ዓ.ም በመካነየሱስ ሴሚናሪየም ዶ/ር አማኑኤል ገ/ስላሴ አዳራሽ የተከናወነው ስብሰባ የተለያዩ የስራ ክፍሎችን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳቦችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡
በስብሰባው ማጠቃለያም ቤተክርስቲያኒቱን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚያገለግሉ ሰዎች የተመረጡ ሲሆን በዚህም መሰረት ቄስ ተሾመ አመኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ጸሐፊ፥ወንጌላዊ ታገሰች ዳኜ የሴቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ፥ አቶ ገመችስ ማቲዮስ የአስተዳደርና ፋይናስ መምሪያ ዳይሬክር ፥ አቶ ጉማቸው ኩሴ የስቲዋርድ ሺፕና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ ገመችስ ዲዲ የምስራች ድምጽ መገናኛ ዘዴዎች ዳይሬክተር ሆነው እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊ ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሃያ አንደኛው አብይ ጉባኤ በመጪው ጥቅምት ይካሄዳል፡፡
@The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY)