Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @memehirhenok
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 12.40K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2021-02-05 12:44:28 ለሕክምና መጥተው ከስኳር እና ከደም ግፊት በሽታ በእንጦጦ ማርያም ጸበል የዳኑ እናት ምስክርነት!

ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!

ለረጅም ዓመት በስኳር እና በደም ግፊት ሲሰቃዩ ነበር። ያለ መድኃኒት እንቅልፍ አይወስዳቸውም ነበር። ከዚህ ችግር እና ሕመም በእንጦጦ ማርያም ጸበል ተፈውሰዋል። ለሚያምን እና ወለላንቱን እመቤት የያዘ ከዚህም የበለጠ ይደረግለታል።
4.2K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 05:12:18
4.6K views02:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 05:09:53 ለሁለት ዓመት በጭንቅላት ዕጢ ስትሰቃይ የነበረች፤ ዕጢው ጭንቅላቷ ተከፍቶ ካልወጣ ዕድሜ የለሽም ትሞቻለሽ የተባለች እህት በእንጦጦ ማርያም ጸበል ተፈውሳ የሰጠችው ምስክርነት!

ሼር በማድረግ ተአምሯን ለሁሉም ግለጡ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ወጣቷ በጭንቅላት ዕጢ ለሁለት ዓመት ተሰቃይታለች። ሐኪሞቹም ዕጢው ጭንቅላቷ ውስጥ እንዳለና ለሕይወቷ አስጊ እንደሆነ በኤም አር አይ አረጋግጠው በአፋጣኝ ጭንቅላቷ ተከፍቶ ዕጢው መውጣት እንዳለበትና ይህንን የማታደርግ ከሆነ ግን የሞት አፋፍ ላይ እንዳለች ነግረዋታል።

እሷን የሕክምና ውጤቷን ይዛ እንጦጦ ማርያም መጥታ ተአምረኛና ፈዋሽ ጸበሏን ተጠምቃ ቅብዓ ቅዱስ ተቀብታ ከጭንቅላት ዕጢ ድናለች።
5.0K views02:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-02 14:03:34
4.7K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-28 18:06:27
6.7K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-28 18:06:02 ታላቅ የንግሥ በዓል ጥሪ

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ነገ ጥር 21 የእመቤታችን በዓለ እረፍቷ ስለሆነ በእንጦጦ ማርያም እንደተለመደው በደማቅ ሁኔታ ስለሚከበር መጥታችሁ የእናታችሁን በረከት እና ረድኤት ተቀበሉ።

በዚህ ቀን ሞት የማይገባት እናታችን ስለ እኛ በተለይም በሲዖል ስለሚሰቃዩት ነፍሳት "አይደለም አንዴ ሰባቴ ልሙትላቸው" ብላ በሥጋ ያረፈችበት ቀን ነውና ጸሎቷ ምልጇዋ እንዳይለያችሁ መጥታችሁ አንግሡ።

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
ጥር 20-5-13 ዓ.ም

ከእንጦጦ ማርያም
5.9K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-26 06:19:00 ዓይነ ጥላ፣ የመተት አጋንንት እና የዛር መንፈስ ወዘተ በሐኪሞች እና በሕክምና መሣሪያዎች ላይ በማደረ የሚያሠሩት ስህተት!

ክፍል ሠላሳ



6.2K views03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-24 18:56:42 ረቡዕ ጥር 19 እንጦጦ ማርያም የቄደር ጥምቀት እና ንስሐ የመሰጠት አገልግሎት አለ!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ የነፍስ ግዴታዎትን ይወጡ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ባለፈው ታህሳስ 27 የቄደር ጥምቀት አዘጋጅተን ብዙ ሰው ተጠምቆ ነበር። በተለያዩ ምክንያቶች ባለፈው ያልተጠመቃችሁ ሰዎች ጥር 19 ረቡዕ ጠዋት 3 ሰዓት የቄደር ጥምቀት አለ መጥታችሁ ተጠመቁ። ጥምቀት አንድ ነው ግን የምንጠመቅበት ምክንያት ልዩ ልዩ ነው።

1ኛ/ የልጅነት ጥምቀት ይህም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማሕጸነ ዮርዳኖስ ተወልደን የቅድስት ሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት ነው(የክርስትና ጥምቀት)

2ኛ/ የፈውስ ጥምቀት ነው። ይህም አንድ ሰው ሲታመም በጽኑ እምነት ንስሐ በመግባት ከደዌ እና ከክፉ መናፍስት እድናለሁ እላቀቃለሁ ብሎ የሚጠበቀው የጸበል ጥምቀት ነው።

3ኛ/ የንስሐ ጥምቀት (ቄደር) ነው።

ቀድር ማለት በአረብኛ እድፍ ርኩስ ማለት ነው። መጽሐፉ ወደ ግዕዝ ከተተረጎመ በኋላ ቄደር ተብሏል።

የቄደር ጥምቀት ለምሳሌ እሮብና አርብ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣ ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን።

ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል።

በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል።

እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለባችሁ ቄደር የምትጠመቁት ንስሐ ገብታችሁ ንስሐችሁን ጨርሳችሁ ነገር ግን ቄደር ሳትጠመቁ የቀራችሁ ብቻ ናችሁ።

ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ ጥር 19 ቀን ረቡዕ ጠዋት 3 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ።

የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ።

ስለዚህ ጥር 19 ረቡዕ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እንጦጦ ማርያም ቤተ ክርስትያን። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ።

አደራ ጥምቀቱ ጸበሉ ቦታ ሳይሆን እንጦጦ ማርያም ቤተ ክርስትያን አዳራሽ ውስጥ ነው።
6.6K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-23 07:08:03 #_የማሕፀን_ዕጢውን_እመቤታችን_ነቅላ_አወጣችላት!

60 ሺ ብር የተጠየቀችበትን በነፃ ተፈወሰች!

ሼር በማድረግ ለልጆችዋ አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ይህች ከታች የምትመለከቷት እህታችን አሥራተ ሥላሴ ትባላለች። እንጦጦ ማርያም ጸበል ትጠመቃለች። ታዲያ ከአምስት ቀናት በፊት ማሕፀኗ አካባቢ በሚሰማት ክፉኛ ሕመም ምክንያት ወደ ኮርያ ሆስፒታል ሄዳ ተመረመረች።

ሐኪሞቹም የማሕፀን ዕጢ እንዳለባትና እሱም በኦፕራሲዮን መውጣት እንዳለበት ካልወጣ ግን ወደ ሌላ ነገር እንደማቀየር ነገሩዋት። ዕጢውን ከማሕፀንዋ በኦፕራስዮን ለማውጣት ስልሳ ሺህ ብር መክፈል እንዳለባት ነገሯት።

እርሷ ግን እመቤቴ ከገደልሽኝ አንቺው ግደዪኝ ብላ እንጦጦ ማርያም እየተጠመቀች ጸበሏንም በርትታ እየጠጣች ከታች እንደምትመለከቱት ከቀናት በፊት የማሕፀን ዕጢውን ወለላይቱ እመቤት የእንጦጦዋ ንግሥት ኘቅላ አወጥታላታለች።

ስልሳ ሺ ብር የተጠየቀችበትን ስልሳ ሣንቲ ሳትከፍለበት፣ ማሕፀኗ ተቀዶ ይወጣል የተባለው በእመቤታችን ኪነ ጥበብ የሐኪም እጅና ቢላዋ ሳይነካት በነፃ ድናለች።

እህቶቼ እንደዚህ አይነት ችግር ሲገጥማችሁ ቸኩላችሁ ኦፕራስዮን ሆናችሁ የማትወጡት ችግር ውስጥ ከመግባታችሁ በፊት እናታችሁ ጋር መጥታች ጸልያችሁ ጸበሏን ተጠምቃችሁ ጠጥታችሁ በምልጃዋ ተጠቀሙ።

ስንት እህቶያችን በማሕፀን ዕጢ ምክንያት ኦፕራስዮን ተደርገው ልጅ መውለድ አቅቷቸዋል። ስንት እህቶች የማሕፀን ዕጢ እየተባለ በሐኪሙ ስህተት ማሕፀናቸው ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

ስንት እህቶች በማሕፀን ዕጢ ምክንያት ሙሉ ማሕፀናቸው ወጥቶ ማሕፀን አልባ ሆነዋል። ይህ ሁሉ ችግር የሚገጥመን ቸኩለን በመወሰናችን፣ በእምነታችን እና በእመቤታችን ጸጋ ባለመጠቀማችን ነው።

ጥር 15-5-13 ዓ.ም
አዲስ አበባ
4.3K views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-20 19:00:43 ከ 200 ዓመት በላይ በቤተሰብ በግ ዶሮ ሲገበር የነበረው የቤተሰብ ዛር ከነመገልገያው ዕቃ እንጦጦ ማርያም መጥተው ጥለውት የሰጡት አሰገራሚ ምስክርነት!

እመቤታችን በሕልም ተገልጻላቸው "ጫጩቷን እንዳትረሺ ይዘሻት ሂጂ" አሏት።

ይህ ከቤተሰቦቻችን ጀርባ ያለ ለዓመታት የተሸከምነው ሕይወታችንን ያጎበጠ: ቤተሰባችንን የበጠበጠ ጣጣ ነው።

ዛሬ ላይ ሆነን በተለያዩ በሽታዎች የምንሰቃየው፣ ወገቤን፣ እራሴን፣ እጄን፣ እግሬን፣ ትከሻዬን፣ ልቤን፣ ሆዴን፣ ማሕፀኔን፣ ነርቭ፣ ስትሮክ ወዘተ እያልን መከራችንን የምናየ፣ በብዙ ዓይነት የካንሰር በሽታ ጤናችንን እና ዕድሜአችንን የምናጣው በቤተሰብ በአያት በቅድመ አያት እና በምንጅላት በኩል ባለው የዛር መንፈስ ነው። በዘር ሐረጋችን ውስጥ የቤተሰባችን ጣጣ ካለ ሕይወታችን ጣጣ ይበዛዋል።

እባካችሁ ከነጠላችሁ በስተጀርባ ያለውን የቤተሰብ ጣጣና የክፉ መናፍስትን ምስጢር እወቁ ከእነሱም ተላቀቁ!

ቪዲዮን ተመልክታችሁ የቤተሰባችሁ የባዕድ አምልኮ ኮተት ካለ አምጡና ጣሉት።
4.6K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ