Get Mystery Box with random crypto!

#_የማሕፀን_ዕጢውን_እመቤታችን_ነቅላ_አወጣችላት! 60 ሺ ብር የተጠየቀችበትን በነፃ ተፈወሰች! | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_የማሕፀን_ዕጢውን_እመቤታችን_ነቅላ_አወጣችላት!

60 ሺ ብር የተጠየቀችበትን በነፃ ተፈወሰች!

ሼር በማድረግ ለልጆችዋ አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ይህች ከታች የምትመለከቷት እህታችን አሥራተ ሥላሴ ትባላለች። እንጦጦ ማርያም ጸበል ትጠመቃለች። ታዲያ ከአምስት ቀናት በፊት ማሕፀኗ አካባቢ በሚሰማት ክፉኛ ሕመም ምክንያት ወደ ኮርያ ሆስፒታል ሄዳ ተመረመረች።

ሐኪሞቹም የማሕፀን ዕጢ እንዳለባትና እሱም በኦፕራሲዮን መውጣት እንዳለበት ካልወጣ ግን ወደ ሌላ ነገር እንደማቀየር ነገሩዋት። ዕጢውን ከማሕፀንዋ በኦፕራስዮን ለማውጣት ስልሳ ሺህ ብር መክፈል እንዳለባት ነገሯት።

እርሷ ግን እመቤቴ ከገደልሽኝ አንቺው ግደዪኝ ብላ እንጦጦ ማርያም እየተጠመቀች ጸበሏንም በርትታ እየጠጣች ከታች እንደምትመለከቱት ከቀናት በፊት የማሕፀን ዕጢውን ወለላይቱ እመቤት የእንጦጦዋ ንግሥት ኘቅላ አወጥታላታለች።

ስልሳ ሺ ብር የተጠየቀችበትን ስልሳ ሣንቲ ሳትከፍለበት፣ ማሕፀኗ ተቀዶ ይወጣል የተባለው በእመቤታችን ኪነ ጥበብ የሐኪም እጅና ቢላዋ ሳይነካት በነፃ ድናለች።

እህቶቼ እንደዚህ አይነት ችግር ሲገጥማችሁ ቸኩላችሁ ኦፕራስዮን ሆናችሁ የማትወጡት ችግር ውስጥ ከመግባታችሁ በፊት እናታችሁ ጋር መጥታች ጸልያችሁ ጸበሏን ተጠምቃችሁ ጠጥታችሁ በምልጃዋ ተጠቀሙ።

ስንት እህቶያችን በማሕፀን ዕጢ ምክንያት ኦፕራስዮን ተደርገው ልጅ መውለድ አቅቷቸዋል። ስንት እህቶች የማሕፀን ዕጢ እየተባለ በሐኪሙ ስህተት ማሕፀናቸው ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

ስንት እህቶች በማሕፀን ዕጢ ምክንያት ሙሉ ማሕፀናቸው ወጥቶ ማሕፀን አልባ ሆነዋል። ይህ ሁሉ ችግር የሚገጥመን ቸኩለን በመወሰናችን፣ በእምነታችን እና በእመቤታችን ጸጋ ባለመጠቀማችን ነው።

ጥር 15-5-13 ዓ.ም
አዲስ አበባ