Get Mystery Box with random crypto!

ከ 200 ዓመት በላይ በቤተሰብ በግ ዶሮ ሲገበር የነበረው የቤተሰብ ዛር ከነመገልገያው ዕቃ እንጦጦ | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ከ 200 ዓመት በላይ በቤተሰብ በግ ዶሮ ሲገበር የነበረው የቤተሰብ ዛር ከነመገልገያው ዕቃ እንጦጦ ማርያም መጥተው ጥለውት የሰጡት አሰገራሚ ምስክርነት!

እመቤታችን በሕልም ተገልጻላቸው "ጫጩቷን እንዳትረሺ ይዘሻት ሂጂ" አሏት።

ይህ ከቤተሰቦቻችን ጀርባ ያለ ለዓመታት የተሸከምነው ሕይወታችንን ያጎበጠ: ቤተሰባችንን የበጠበጠ ጣጣ ነው።

ዛሬ ላይ ሆነን በተለያዩ በሽታዎች የምንሰቃየው፣ ወገቤን፣ እራሴን፣ እጄን፣ እግሬን፣ ትከሻዬን፣ ልቤን፣ ሆዴን፣ ማሕፀኔን፣ ነርቭ፣ ስትሮክ ወዘተ እያልን መከራችንን የምናየ፣ በብዙ ዓይነት የካንሰር በሽታ ጤናችንን እና ዕድሜአችንን የምናጣው በቤተሰብ በአያት በቅድመ አያት እና በምንጅላት በኩል ባለው የዛር መንፈስ ነው። በዘር ሐረጋችን ውስጥ የቤተሰባችን ጣጣ ካለ ሕይወታችን ጣጣ ይበዛዋል።

እባካችሁ ከነጠላችሁ በስተጀርባ ያለውን የቤተሰብ ጣጣና የክፉ መናፍስትን ምስጢር እወቁ ከእነሱም ተላቀቁ!

ቪዲዮን ተመልክታችሁ የቤተሰባችሁ የባዕድ አምልኮ ኮተት ካለ አምጡና ጣሉት።