Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @memehirhenok
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 12.40K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2022-09-11 18:42:57
4.2K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 18:41:50 እንኳን ለዘመነ ሉቃስ ለ 2015 ዓ.ም አደረሳችሁ! አውደ ዓመትን ድሆችን፣ ምስኪናንን በማሰብ ለእነሱም እንደ አቅማችን በጎ ነገርን በማድረግ እግዚአብሔርን ደስ እናሰኘው። አዲሱ ዓመት ንስሐ የምንገባበት፣ ቅዱስ ቁርባን የምንቀበልበት፣ በአምልኮት ሕይወት በተለይም በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት የምንበረታበት ዓመት ይሁንልን!

"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ" መዝ 65፥11

መልካም አዲስ ዓመት!
4.1K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 05:38:28

4.6K views02:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 19:40:36
4.8K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 04:52:55
145 views01:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 04:52:44 #_የ_2014_ዓ_ም_የመጨረሻውና_የአዲሱ_ዓመት_መቀበያ

#_የንስሐ_እና_የቄደር_ጥምቀት_ጥሪ!

#_አዲሱን_ዓመት_በንስሐ_ሕይወት_እንቀበል!

#_ቅዳሜ_ጷግሜ_5_ጠዋት_2_ሰዓት

#_በወይን_አምባ_ቅድስት_ማርያም_ቤተ_ክርስትያን!

"የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም"

#_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

#_ቄደር_ለምን_እንጠመቃለን?

#_ቄደር_በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

የነፍስ ጉዳይ ነውና ሳትቸኩሉ በደንብ አንብቡት!

"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት ለጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።" 1ኛ ጴጥ 4፥3

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_ሼር_በማድረግ_የነፍስ_ግዴታዎትን_ይወጡ!

እግዚአብሔር "ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ" ስላለን ጾሙን በንስሐ፣ በቄደር እንቀድሰው። /ት.ኢዮ 1፥14/

ተወዳጆች ሆይ አዲሱን ዓመት በንስሐ ሕይወት እንድንቀበለው፤ እግዚአብሔር አዲሱን ዓመት እንዲባርክልን፣ ዘመናችንን የበረከት የረድኤት የስኬት የአምልኮት ሕይወት እንዲያደርግልን ቅዳሜ ጷግሜ 5 ጠዋት 2 ሰዓት በወይን አምባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን የቄደር ጥምቀት እና ንስሐ የመስጠት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። እባካችሁ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ኑ። በተቻለ መጠን ደጇ ሁለት ሰዓት ድረሱ!

በምትወዷት በእመቤታችን እማጸናችኃለሁ በ 2014 ዓ.ም የሠራነውን ኃጢአት ወደ አዲሱ ዓመት ይዘነው አንሻገር። ይልቁንም ኃጢአታችንን በንስሐ አራግፈን አዲሱን ዓመት በንስሐ ሕይወት እንቀበል።

የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር።

#_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣

ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣

ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን።

ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል።

በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል።

ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ ቅዳሜ ጷግሜ 5 ቀን ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ።

የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ።

የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም።

የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ።

ስለዚህ ቅዳሜ ጷግሜ 5 ቀን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ወይን አምባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ።

#_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ቤተ ኮርስቲያኑ በር ላይ ያወርዷቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ጷግሜ 3- 13-14 ዓ.ም
አዲስ አበባ
157 views01:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 21:34:40
1.1K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 21:34:34 እመቤታችን ስለ ጷግሜ እና ስለ ጷግሜ 3 ክብር ጥቅም ለአጼ ናዖድ የገለጠችላቸው!

#_በእውነት_ጷግሜ_3_ሌሊት_ሳትጸልዩ_እንዳይነጋባችሁ!

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ኢትዮጲያዊው ጻድቅ እና ደግ የሆነው አጼ ናዖድ እመቤታችንን በፍጹም ልቡ እና በፍጹም ሐሳቡ ይወዳት ነበር፡፡ ከፍቅሩም ጽናት የተነሳ ቅዱስ ኤፍሬም የሰባቱን ዕለታት ውዳሴ ማርያምን ደርሶ እንዳመሰገናት እሱም መልክአ ማርያምን ደረሰላት፡፡ በዚህም እንደ ቅዱስ ኤፍሬም በመልክአ ማርያም ያመሰግናት ነበር፡፡ በዚህም ፍቅሩ እና ትሕትናው እግዚአብሔር ብዙ ምስጢራትን ገልጾለታል፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ ወለላይቱ እመቤት ለአጼ ናዖድ ተገለጸችለትና ‹‹ወዳጄ ናዖድ ሆይ ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ›› አለችው፡፡ እሱም በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ‹‹እመቤቴ ሆይ በፊትሽ ቧለሟልነትን ካገኘሁ ከስምንተኛው ሺህ ዘመን ከጊዜዋ ጊዜ ደርሼ ከማያት ይልቅ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም በሞት ታሰናብቺኝ ዘንድ እለምንሻለሁ›› አላት፡፡

እመቤታችንም ‹‹እሺ በጎ የተወደደ ልጄ እንደ ወደድክ ያድርግልህ›› አለችው፡፡ ዳግመኛም እመቤታችን ‹‹ሌላ የምትጠይቀኝ ነገር አለህን›› አለችው፡፡ እሱም መለሰና ‹‹እኔ አፈርና ትቢያ ስሆን የሰማይ እና የምድር ንግሥት ከምትሆን ከእመቤቴ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርኩ፡፡ ስለዚህም ነገር ይህቺ ጳጒሚት የምትባለው ዕለት ከምን እንደተገኘች ልረዳ እወዳለሁ›› አለ፡፡

እመቤታችንም ለአጼ ናዖድ ‹‹ይህች ጳጒሚት የተባለችው ከአራቱ ዘመናት ባሉት ቀናት በትርፍ ሰዓት የተገኘች ናት፡፡ ስለዚህ ከአሥራ ሁለቱ ወሮች እያንዳንዱ ተቆጥራ አሥራ ሦስተኛ ወር በመሆን ጳጒሚት ትባለች፡፡ ይህቺ ዘመን ዘመነ ምጽአት ትባላለች፡፡ ዳግመኛም ይህቺ ዘመን ኃጢአት የሚሠረይባት፣ ጸሎትና ምጽዋት የሚያርግባት ወር ናት፡፡

ማንኛውም ሰው ሁሉ በዚህ ወር የጸለየ፣ የጾመ፣ የመጸወተ እንዲሁም በዚህች በሚዘንበው ዝናብ ሰውነቱን የታጠበ፣ የተጠመቀ ከደዌው ይፈወሳል፡፡ ዝናቡም የምሕረት ዝናብ፣ የሚወርደውም ጠበል የበረከት ነውና፡፡ በዚህችም ወር የቅዱሳን ነገሥታትና የመላእክትም ሁሉ በዓል የሚከበርባት ወር ስትሆን የሰማይ ደጃፎችም የሚከፈቱባት ወር ናት፡፡ ርኅወ ሰማይ ማለትም የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ የቸርነት በዓል ማለት ነው፡፡

በዚችም ወር በሦስተኛው ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሩፋኤል በዓል ነው፡፡ ከፍጡራን ወገን በሰማይም በምድርም የሚተካከለው የሌለ፣ የሳሌም ንጉሥና እንዲሁም ነብይ ሲሆን፣ አባት እና እናት እንዳለው የማይታወቅ፣ ሞቶ ተቀበረ የማይባል፣ የካህኑ የመልከ ጼዴቅ በዓል የሚከበረው በዚችው ዕለት ነው፡፡

ይህችንም ዕለት በጾምና በጸሎት፣ በምጽዋትም ያከበራትና ከፍ ከፍም ያደረጋት ሁሉ የሥላሴ ምሥጢር ይገለጽለታል፡፡ የልዑል እግዚአብሔርም መንፈስ በልቦናው ይሠርጽለታል፡፡

የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ቸርነት ይደረግለታል፣ የካህኑ የመልከ ጼዴቅ በረከት፣ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል በረከት፣ የቅዱሳን ነገሥታት የአብርሃ ወአጽብሐ በረከት ያድርበታል፡፡ ክብር ብልጽግና ይሆንለታል፣ በጸጋ ላይ ጸጋ ይጨመርለታል፡፡ ግርማ ሞገስ ይሰጠዋል፡፡ እንደ እግዚአብሔር ወዳጅ እንደ አብርሃም ጠላቶቹ ሁሉ ይጠፉለታል፡፡ በሞተም ጊዜ የእሳትን ባሕር ተሻግሮ እስከ ዘለዓለሙ በእውነት በመንግሥተ ሰማያት ነግሥ ይኖራል›› አለችውና ከእሱ ተሠወረች፡፡

የኢትዮጲያዊው ንጉሥ ናዖድም ከዕንቅልፉ በነቃ ጊዜ ፈጽሞ በመደሰት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ ራእዩን የገለጸችለትና ይህንም ተስፋ ሁሉ የሰጠችው እመቤታችንን አመሰገናት፡፡ ከዚያም ከስምንተኛው ሺህ አታድርሰኝ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ባመለከተው መሠረት ስምንተኛው ሺህ ከመግባቱ በፊት በነሐሴ ሰባት ቀን ዐረፈ፡፡ በዚያን ጊዜ ሰባተኛው ሺህ ተፈጸመ፡፡ ይለናል ተአምረ ማርያም፡፡

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እመቤታችን ለአጼ ናዖድ ስለ ጳጒሚት እና ጳጒሚትን በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት እና በምጽዋት ብናሳልፍ የምናገኘውን ክብር እና ጸጋ ስለገለጠችለት፤ በተለይም ጷግሜ 3 የሰማይ ደጆች የሚከፈቱበትና የሰው ልጆች ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር የሚደርስበት ልዩ እለት ነው።

እባካችሁ ጷግሜ 3 የበረታችሁ ሌሊት 6 ሰዓት ተነስታች እንደ እኔ ያላችሁ ደካሞች ደግሞ ሌሊት 9 ሰዓት ተነስታችሁ ዘወትር የምትጸልዩትንና ሰዓት አልበቃ እያላችሁ ያቋረጣችሁትን ጸሎቶች በሙሉ ለምሳሌ ውዳሴ ማርያም፣ መልክአ ማርያም፣ መልክአ ኤዶም፣ ሰኔ ጎልጎታ፣ ጸሎተ ባርቶስ፣ ጸሎተ አርጋኖን፣ ሠይፈ ሥላሴ፣ ሠይፈ መለኮት፣ ዳዊት፣ መልክአ ሚካኤል፣ መልክአ ገብርኤል፣ መልክአ ሩፋኤል፣ መልክአ ዑራኡል፣ ውዳሴ አምላክ ወዘተ በርትታችሁ ጸልዩ፡፡

የዓመት በረከት ስለሆነ እንዳቅማችሁ በፍጹም ጸሎት ሳትጸልዩ ሌሊቱ እንዳይነጋባችሁ፡፡ እንቅልፋችሁን ነገ ታካክሳላችሁ፡፡ አደራ አደራ አደራ!

ጷግሜ 2-13-14 ዓ.ም
አዲስ አበባ
1.7K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 21:32:04

627 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 21:15:26

870 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ