Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @memehirhenok
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 12.40K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2022-08-29 11:44:41 የጌታ ወዳጅ የነፍሳት አማላጅ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቃል-ኪዳን እና እረፍት

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ እሷን ለሚወዱ እና ለልጆችዋ አዳርሱ!

ተወዳጆች ሆይ ዛሬ ነሐሴ 24 ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና መንበረ ማርያም ማር ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘላለማዊ ጽኑ ቃል-ኪዳን ተቀብለው ያረፉበት ቀን ነው፡፡ ስለዚህ እስኪ ለዛሬ የማር ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ጌታ የገባላትን ቃል-ኪዳን እንድንጠቀምበት እንመልከት፡፡

እናታችን ማር ቅድስት ክረስቶስ ሠምራ በጣና ባሕር ውስጥ በጸሎት ሳለች ለክብሩ ጌትነት ስግደት፣ ለስም አጠራሩ ምስጋና የሚገባው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሷ መጣ፡፡ ከጌታችን ጋር ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል እና እናቱ ወለላይቱ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም መጣች፡፡

አሥራ አምስቱ ነብያትና አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት፣ ጻድቃን፣ ሰማእታት፣ ደናግልና መነኮሳት እንዲሁም ሌሎችም በየማዕረጋቸው መጡ፡፡ ሔሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት፣ አለቃቸው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ተከትለውት መጡ፡፡ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት በየነገዳቸው መጡ፡፡

ከእነዚህ ሁሉ በኃላ የእሥራኤል ንጉሥ ዳዊት በገናውን ይዞ ‹‹ልጄ ሆይ ስሚ ጆሮሽን አዘንብይ ወገኖችሽንና ያባትሽን ቤት እርሺ፣ ንጉሥ ውበትሽን ወዷልና፣ እርሱ ታጋሽ ነውና›› እያለ በገናውን ይደረድር ነበር፡፡ ንጉሥ ዳዊት እንዲህ እያለ በሚዘምርበት ጊዜ በዚያ ያሉ ቅዱሳን በሙሉ ‹‹የእግዚአብሔር ባለሟል፣ ወዳጅ ይህች ክረስቶስ ሠምራ በእውነት ብፅዕት ነች›› እያለ ዘመሩ፡፡

በዚያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዛሬ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ልወስድሽ መጥቻለሁ›› አላት፡፡ አይ መታደል እኛ ኃጥአን በጭንቅ ስንሞት ቅዱሳን ግን በጌታ ክብር ይሞታሉ፡፡ ጌታም ‹‹እውነት እውነት እልሻለሁ፣ እነግርሻለሁ በፍጹም ደስታ መታሰቢያሽን ያደረገውን በመንግሥተ ሰማያት አስደስተዋለሁ፡፡ በችግሩ ወይም በጭንቁ ጊዜ በመታመን ስምሽን ቢጠራ፣ እኔ ከመከራ ሥጋ፣ ከመከራ ነፍስ አድነዋለሁ፡፡

የገድልሽን ዜና የሚናገረውን መጽሐፍ የጻፈ፣ ያጻፈ እኔ ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያንሽን የሠራ፣ ያሠራ፣ ያሳነጸ እኔ በመንግሥተ ሰማያት ንጽሕ አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ፡፡ በስምሽ የተራበ ያበላ፣ እኔ በዕለተ ዓርብ ከተቆረሰው ሥጋዬ አበላዋለሁ፡፡

በስምሽ ለተጠማው እፍኝ ውኃ ያጠጣ እኔ በዕለት ዓርብ ከጎኔ ከፈሰሰው ደሜ አጠጣዋለሁ፡፡ በዓልሽ በሚከበርበት ዕለት ጧፍ፣ ዕጣን፣ ዘቢብ፣ ንጹሕ ስንዴ ሌላም መባዕ ያገባውን መሥዋዕቱን እንደ አብረሃምና እንደ መልከ ጼዴቅ መሥዋዕት አድርጌ እቀበለዋለሁ›› አላት፡፡

በዚህን ጊዜ ማር ቅድስት ክርስቶስ ሠምራም ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ባርያህ ባለሟልነትን በፊትህ ከገኘሁስ አንድ ጊዜ እናገር ዘንድ ፍቀድልኝ›› አለችው፡፡ ጌታም ‹‹ትናገሪ ዘንድ ፈቅጄልሻለሁ›› አላት፡፡ እሷም ‹‹ሥጋዬ የምቀበርበትን ወይም የማያርፍበትን ቦታ ወዴት ታዛለህ›› አለችው፡፡

አይ መታደል ቅዱሳኑ በገድላቸው አይደለም ለነፍሳቸው ለሥጋቸው ማረፍያ ይጨነቃሉ፡፡ እኛ እንኳን ለሥጋችን ለነፍሳችን አልሆን ብለናል፡፡ ጌታም ‹‹መቃብርሽ በዚች ጓንጉት በምትባል ደሴት ውስጥ ነው›› አላት፡፡ ጌታም መልሶ ‹‹ነገር ግን ሥጋሽ በመሬት ውስጥ ይቀበራል ስላልኩሽ ሐዘን አይግባሽ፣ በኃለኛው ዕለት እኔ አስነሳዋለሁና›› አላት፡፡

ማር ቅድስት ክርስቶስ ሠምራም ‹‹አቤቱ እንዲህ ከሆነ መታሰቢያዬን ያደረገ፣ ስሜን እየጠራ፣ በስሜ በታነጸው ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ የሚቀበረውን እስከ ስንት ትውልድ ድረስ ትምርልኛለህ›› አለችው፡፡ ጌታም ‹‹እስከ አሥር ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ›› አላት፡፡ ጌታም ይህን ቃል-ኪዳን በሰጣት ጊዜ ፈጽማ ተደሰተች፡፡

ዳግመኛም ጌታ ‹‹ይህችን ደሴት እንደ ደብረ ታቦርና ደብረ ዘይት ስሟ የተጠራ ይሁን፣ ይህችን ሥጋሽ ያረፈበትን ቦታ ቀደስኳት አከበርኳት፣ መጽሐፍ የተናገረውን አልሰማሽን፣ ቦታ ሰውን የሚያከብረው አይደለም ሰው ቦታን ያከብረዋል እንጂ፡፡ ስለዚህም ስላንቺ ይቺን መካነ መቃብርሽን ቀደስኳት አከበርኳት፡፡ ስሟም ደብረ ፍቅር፣ ደብረ ምሕረት ተብሎ ይሰየም ወይም ይጠራ፡፡

እውነት እውነት እልሻለሁ ሥጋሽ ከተቀበረበት ሄዶ መካነ መቃብርሽን የተሳለመ የእናቴን የማርያምን መካነ መቃብር እንደተሳለመ ይቆጠርለታል፡፡ እውነት እውነት እልሻለሁ አንቺን ያከበረ ሁሉ እኔ በሰማያዊ መንግሥቴ አከብረዋለሁ፡፡ አንቺን የወደደ ሁሉ እኔም እወደዋለሁ፡፡ ወዳጄ ክረስቶስ ሠምራ ሆይ ይህ የዛሬ በዓልሽ የደስታና የተድላ ቀን ነው›› አላት፡፡

ዳግመኛም ጌታ ‹‹ክብርሽ ከአሮንና ከሙሴ ጋር የተካከለ ነው፡፡ ክብርሽ ከጴጥሮስ እና ከጳውሎስ ክብር ጋር የተካከለ ነው፡፡ ክብርሽ ሰይጣንን ድል ካደረገው ከሕፃኑ ቂርቆስ ክብር ጋር የተካከለ ነው፡፡ ክብርሽ ከእንጦንስና ከመቃርዮስ ክብር ጋር የተካከለ ነው፡፡ ክብርሽ ፀሐየ ልዳ እየተባለ ከሚጠራ ከጊዮርጊስ ክብር ጋር የተካከለ ነው፡፡ በደብረ ጽዮን ከሊቀ ዲያቆናት ከእስጢፋኖስ ጋር ትዘምሪ ዘንድ በክብር ተካክለሻል፡፡ በእውነት አንቺን የሚወዱ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፣ አንቺን የሚያከብሩ ሁሉ አንቺ ካለሽበት ቦታ ገብተው ካንቺ ጋር ይደስታሉ›› አላት፡፡

እናታችን ማር ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ከጌታ ዘንድ ይህን አምላካዊ ቃል ከሰማች በኃላ ነሐሴ ሃያ አራት ቀን በሦስት መቶ ሰባ አምስት ዓመቷ የከበረች ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፡፡ (ዕድሜዋን ልብ ይሏል?) ቅዱሳን መላእክትም እልል እያሉ ነፍሷን ይዘው ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አድርሰው በአሸናፊ እግዚአብሔር ፊት አደረሷት ሰገደችም፡፡

ጌታም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ‹‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራን እናቴ ድንግል ማርያም ወደምትኖርበት ውሰዷት›› አለው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ይዟት ሲሄድ እጅግ የሚያስደንቅና ከፀሐይ ይልቅ የሚያበራ መንበር አየች፡፡ እሷም ይህን መንበር ባየችውም ጊዜ በጣም አድርጋ ወደደችው፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ክርስቶስ ሠምራን ‹‹ምን ትመለከቻለሽ› አላት፡፡ እሷም ‹‹ያን ብሩህ የሆነ መንበር እመለከታለሁ›› አለችው፡፡ መልአኩም ‹‹ይህ መንበር ላንቺ ቢሆን ትወጃለሽን›› አላት፡፡ ‹‹አዎን ጌታዬ ለእኔ ቢሆን እወዳለሁ›› አለችው፡፡ ‹‹እንግዲያውስ ላንቺ የተዘጋጀ ነው›› አላት፡፡

በዚያን ጊዜ ማር ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ‹‹ጌታዬ መኖሪያሽ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ነው ብሎኝ አልነበረምን፡፡ ታዲያ እንዴት ይህ መንበር ላንቺ የተዘጋጀ ነው ትለኛለህ›› አለችው፡፡ ወዳጆቼ ማር ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለእመቤታችን ያላትን ፍቅር ክብር እና አብራት ለመኖር ያላትን ፍላጎት ልብ አላችሁ፡፡

ቅዱስ ሚካኤልም ‹‹ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ለምን ቸኮልሽ›› ብሏት ወደ እመቤታችን መኖሪያ ወስዶ አደረሳትና ‹‹ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እግዲህ ተመልከች›› አላት፡፡ እሷም በተመለከተች ጊዜ ያየችው እመቤታችንን ሰው ሆና ሳይሆን ከፍታዋ ወይም ቁመቷ የላቀ ተራራ መሰለቻት፡፡ እሷም ‹‹ድንግል ማርያም ነች ብለኸኝ አልነበረምን ታዲያ እንዴት ተራራ ልትሆን ቻለች›› አለችው፡፡ መልአኩም ‹‹ምስጢሯ እስኪገለጽልሽ ድረስ ትንሽ ታገሽ›› አላት፡፡ ከዚያም ቀና ብላ ብትመለከት ወለላይቱ እመቤታችን ድንግል ማርያምን አየቻት፡፡ ማር ቅድስት ክርስቶስ ሠምራም እንደ አሞራ በራ አንገቷን አቅፋ ሳመቻት፡፡
3.3K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:42:29

1.0K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:48:08

3.2K views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:59:16
2.8K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:58:42 #_የንስሐ_እና_የቄደር_ጥምቀት_ጥሪ!

#_አዲሱን_ዓመት_በንስሐ_ሕይወት_እንቀበል!

#_እሑድ_ነሐሴ_22_ጠዋት_2_ሰዓት

#_በወይን_አምባ_ቅድስት_ማርያም_ቤተ_ክርስትያን!

"የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም"

#_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

#_ቄደር_ለምን_እንጠመቃለን?

#_ቄደር_በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

የነፍስ ጉዳይ ነውና ሳትቸኩሉ በደንብ አንብቡት!

"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት ለጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።" 1ኛ ጴጥ 4፥3

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_ሼር_በማድረግ_የነፍስ_ግዴታዎትን_ይወጡ!

እግዚአብሔር "ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ" ስላለን ጾሙን በንስሐ፣ በቄደር እንቀድሰው። /ት.ኢዮ 1፥14/

ተወዳጆች ሆይ አዲሱን ዓመት በንስሐ ሕይወት እንድንቀበለው እሑድ ነሐሴ 22 ጠዋት 2 ሰዓት በወይን አምባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን የቄደር ጥምቀት እና ንስሐ የመስጠት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። እባካችሁ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ኑ። በተቻለ መጠን ደጇ ሁለት ሰዓት ድረሱ!

የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር።

#_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣

ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣

ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን።

ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል።

በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል።

ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ እሑድ ነሐሴ 22 ቀን ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ።

የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ።

የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም።

የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ።

ስለዚህ እሑድ ነሐሴ 22 ቀን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ወይን አምባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ።

#_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ቤተ ኮርስቲያኑ በር ላይ ያወርዷቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ነሐሴ 19- 11-14 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2.7K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 11:52:58

4.3K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 17:00:00
5.1K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 16:59:51 በዚህን ጊዜ ቅዱስ ቶማስ ‹‹አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችንስ በብርሃን ደመና በመላእክት ምስጋና ታጅባ አርጋለች›› ብሎ ወለላይቱ እናት ዓለም ለምልክት የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው፡፡ እነሱም ተረጋጉ ሰበኗንም ለበረከት ተካፍለው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሄደዋል፡፡

ታዲያ በዓመቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ትንሳኤዋን ቶማስ አይቶ፣ በነፍሱ ተደስቶ፣ እንዴት እኛ ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምሮ በፍቅር፣ ሊያዩ የእመቤታችንን የትንሳኤ ምስጢር ሱባዔ ገቡ፡፡ ሱባኤያቸውን ከፈጸሙ በኋላ ነሐሴ 16 ቀን ያሰቡትን አደረገላቸው፡፡ ጌታችንም እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፣ቅዱስ እስጢፋኖስን ዋና ዳያቆን አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቁርቦ የእናታቸውን የወለላይቱን የእመቤታችንን እርገቷን አሳይቷቸዋል፣ብዙ ሚስጢርም አካፍሏቸዋል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ቅዱሳን ሐዋርያት በእመቤታችን ትንሳኤ ምክንያት ከጌታቸው እጅ ጸጋ መለኮት ለማግኘት በቅተዋል፡፡ ይህም ሰማያዊ ቅዱስ ቁርባንን በጌታ መለኮታዊ እጅ መቀበል ነው፡፡ እንዲሁም ከእናታቸው ከወለላይቱ ከወላዲተ አምላክ ከትንሳኤዋ በረከት ተላፋይ ሆነዋል፡፡ በዚህም ብዙ ሰማያዊ ሚስጢራትን ለማየት በቅተዋል፡፡

ብዙዎች ስለ እመቤታችን እረፍት ሳይሆን እርገት አልዋጥ አልገለጥ ይላቸዋል፡፡ የእመቤታችን እርገት ሊደንቀን አይገባም፡፡ እንኳን እሷ በዘመነ አበው የነበረው ደገኛው ሄኖክ እና ቀናተኛው ነቢዩ ኤልያስ አንዱ ከሞት ፊት በመሰወር፣ አንዱ በእሳት መንኩራኩር ወደ ሰማይ ከነ ሥጋቸው ለማረግ በቅተዋል፡፡ /ዘፍ. 5÷24፣ 2ኛ ነገ 2÷11/

ወዳጆቼ እመቤታችን ባታርግ ነበር የሚገርመው፡፡ ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ ከሞት ፊት ተሰወረ አረገ፡፡ እሷ ግን ሕይወቷን ከልጇ ጋር ስላደረገች፣ የሞትን መድኃኒት ስለ ወለደች አረገች፡፡ ነብዩ ሄኖክንና ነብዩ ኤልያስን ከሞት ፊት ሰውሮ ያሳረገ ልጇ እናቱን ቢያሳርጋት ሊደንቀን አይገባም፡፡

እመቤታችን አንደ ሰው ሞት ተገብቷት ሳይሆን የሞተችው ሞቷ በሲዖል ላሉ ነፍሳት የዘላለም ሕይወት ስለሆነ ነው፡፡ የእመቤታችን የሥጋ እረፍት ከሰው የሚለይበት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ስለሆነ ነው፡፡ እመቤታችን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ በመሆኗ በትንሳኤዋና በእርገቷ ከልጇ ትንሳኤና ዕርገት ተሳታፊ ናት፡፡

ወለላይቱ አዛኝቱ ፍቅሯን እንደ ውኃ በአንጀታችን፣ እንደ ቅቤ በአጥንታችን ታስርጽልን፡፡

ሱባኤውን በሰላም አስጀምራ በሰላም ላስፈጸመችን፣ ለብርሃነ እርገቷ ላደረሰችን ለወለላይቱ ለወላዲተ አምላክ በቅዱሳን መላእክት፣ በጻድቃን በሰማእታት ጥዑም አንደበት ምስጋና ይድረሳት፡፡ የዓመት ሰው ትበለን!!!

ነሐሴ 15/12/12 ዓ.ም
አዲስ አበባ
5.7K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 16:59:51 #_የእመቤታችን_እረፍትና_እርገት!

/ሦስቱ የእመቤታች የእረፍት ታሪክ እና ልጇን የመሰለችበት እርገት/

‹‹አይደለም አንዴ ሰባቴ ልሙትላቸው›› ያለች ደንግል ማርያም፣ በእኛ መቼም አትዘነጋም!

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለወለላይቱ ልጆች አድርሱ!

ተወዳጆች ሆይ የወለላይቱ የእመቤታችን የእረፍቷ ጊዜ ሲደርስ ጥቂት ታመመች፡፡ እመቤታችን የአምላክ እናት እንደመሆኗ መጠን ሕመም ባይገባትም የሰው ልጅ እንደመሆኗ መጠን ነው የታመመችው፡፡ አገልጋይዋ ቅዱስ ዮሐንስ በኤፌሶን ወንጌልን እያስተማረ ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ በደመና ተጭኖ ወደ እመቤታችን መጣ፡፡ ሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት በጸጋ አውቀው በደመና ተጭነው መጡ፡፡ ሁሉን የምታጽናና እመቤት ሐዋርያትም ሲያጽናኗት ‹‹ልጅሽ አምላካችን ነውና ደስ ይበልሽ!›› አሏት፡፡

እመቤታችንም በአልጋዋ ጠርዝ ተቀምጣ ‹‹ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ወደ ዘላለማዊው ዓለም እንደምሄድ በምን አወቃችሁ›› አለቻቸው፡፡ ሐዋርያትም ‹‹መንፈስ ቅዱስ በደመና ጭኖ እንደ ዓይን ጥቅሻ ያመጣን አንቺ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ልትሄጂ ስለሆነ ነው›› አሏት፡፡

እመቤታችንም ድምጿን ከፍ አድርጋ ‹‹ጌታዬ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈጽሜ አመሠግናለሁ፡፡ የእኔን አገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሠግኑኛል›› አለች፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያትም ከእነሱ መለየቷን ሲያውቁ ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ጠየቁ፡፡ ወለላይቱ ወላዲተ አምላክም እጇንም በላያቸው ላይ ዘርግታ ባረከቻቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ እልፍ አእላፍ መላእክት አጅበውት እያመሰገኑት መጥቶ አረጋጋት፡፡ በሰማይ ያዘጋጀላትን ተድላ ደስታ ነገራት፡፡ ጌታችንም ከገነት ያመጣውን አፒሊያኖስ የሚባል መዓዛው ለነፍስ የሚጣፍጥ፣ የሚመስጥ አበባ በአፍንጫዋ እያሸተተች፣ በጆሮዋ የመላእክትን ምስጋና እየሰማች ያለ ጻር ያለ ጋር በተመስጦ፣ በደስታ ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ፡፡

ጌታችንም ንጽህት ነፍሷን የብርሃን መጎናጸፊያ አልብሶ በመላእክት ዝማሬ ጥር 21 ቀን ወደ ሰማይ አሳረጋት፡፡ ነብዩ ዳዊት ‹‹ነፍሴ ሆይ ወደ እረፍትሽ ግቢ እግዚአብሔር መልካም ነገርን አድርጎሻልና›› እንዳለ /መዝ. 114÷7/ እመቤታችንም በልጇ ደስታ ወደ ሰማይ እረፍቷ ገባች፡፡

በሌላ ታሪክ እመቤታችን በእረፍቷ ጊዜ ጌታችን ሲመጣ ‹‹ልጄ ወዳጄ እኔ አንተን ወልጄ እንዴት እሞታለሁ? በእውኑ ሞት ለእኔ ይገባኛልን?›› ብላ ጠይቃው ነበር፡፡ እሱም በሲዖል የሚሰቃዩትን ነፍሳት አሳይቷት ‹‹እናቴ እነዚህ በሲዖል የሚሰቃዩት ነፍሳት፣ የሚያገኙት እረፍት፣ ባንቺ ሞት ነው›› ሲላት የሞቷን መልካምነት፣ በሲዖል ለሚሰቃዩት ነፍሳት ነፃ መውጣት መሆኑን የተረዳችው እመቤታችን ‹‹ልጄ ሆይ ለእነዚህስ አይደለም አንዴ ሰባቴ ልሙትላቸው›› ብላ በፍቃዷ እዳረፈች ሊቃውንት ይተርካሉ፡፡

ወዳጆቼ እመቤታችን ለእኛ ለልጆችዋ ሰባቴ ለመሞት በነፍሷ የተወራረደች እናት ሆና ሳለ በዚህም እመቤታችንን በነፍስ ፍቅር አለመውደድ ማለት ከጣዕመ ፍቅሯ መሰደድ፣ በቁም ለሲዖል እሳት መማገድ ነው፡፡ ወለላይቱን እመቤት አለማመስገን ማለት በነፍስ በሥጋ ከጸጋ ፍቅሯ መራቆት፣ ለሰይጣንና ለሠራዊቱ ተላልፎ መሰጠት ነው፡፡ ከወለላይቱ፣ ከአዛኝቱ ጣዕመ ፍቅር መለየት ማለት ከሞቱት በላይ ከሚኖሩት በታች ሆኖ በቁም መሞት ነው፡፡

የከበረ ሥጋዋንም ቅዱሳን ሐዋርያት በክብር ገንዘው ጌቴሴማኒ ቀበሩ፡፡ በሦስተኛውም ቀን መላእክት ሥጋዋን ከጌቴሴማኒ መቃብር አውጥተው ወደ ገነት አሳርገው በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጡ፡፡ ምድራዊት ኪሩብ የክርስቶስ እናት ሞትን መቅመሷ ይደንቃል፡፡ ልጇ በሞት ፍርድ አያዳላምና ሞት ለማይገባት ለሥጋ እናቱ የደስታ ሞት አደላት፡፡

እንዲሁም በሌላ ታሪክ እመቤታችን ጥር 21 ቀን ልጇ የከበረ ሥጋዋን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው ይላል፡፡ በዚያም ሰንድሮስ በሚባል ነጭ ዕጣን እየታጠነ እስከ ነሐሴ 14 ቆይቷል፡፡ ይህም የሆነው አይሁድ የከበረ ሥጋዋን አውጥተው እንዳያቃጥሉት ነው፡፡ እመቤታችን በ49 ዓ.ም ገደማ ከሚያልፈው ከጨለማ ዓለም ወደ ማያልፈው ወደ ብርሃናዊው ዓለም በልጇ ፈቃድ ተሸጋግራለች፡፡

የከበረ ሥጋዋን ቅዱሳን ሐዋርያት ወደ ጌቴሴማኒ መካነ እረፍት ይዘው ሲሄዱ የነገር ሰደድ፣ ምቀኞች አይሁድ፣ በቅንዓት ተነሳስተው የሚያደርጉትን ተንል ያወቀ ተወዳጅ ልጇ በመብረቅ ሠረገላ ነጥቆ፣ በመላእክት አስጠብቆ፣ ከምድር ወደ ሰማይ አርቆ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር፣ ቅዱስ ዮሐንስን የዓይን ምስክር አድርጎ አስቀምጧታል፡፡ በወቅቱ በዚህም ምድራዊ ሥርዓተ ቀብሯ አልተፈጸመም፡፡

የእመቤታችን እና የዮሐንስ ከሐዋርያት መሰወር በቀሩት ሐዋርያት ላይ መንፈሳዊ ቅናት፣ ቁጭት፣ ጸጸት ስላሳደረባቸው ጉዳዩን ለማወቅ፣ ለህዝብና ለአህዛብ ለማሳወቅ፣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ታላቅ፣ የእመቤታችንን ምስጢር የሚያሳውቅ ሱባኤ በጾም በጸሎት በስግደት ያዙ፡፡

ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችንም ነሐሴ 14 ቀን በመለኮት ጸጋ የተከበበ፣ በመላእክት ዝማሬ የታጀበ፣ ክቡር ሥጋዋን አምጥቶ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በሚያስደንቅ ሁኔታ የከበረ ሥጋዋን በጌቴሴማኒ ቀበሩ፡፡ ወዳጆቼ ቅዱሳን ሐዋርያ በእመቤታችን በሕይወቷ ብቻ ሳይሆን በሞቷ ተባርከውባታል፡፡ በነፍሷ ብቻ ሳይሆን ነፍስ በተለየው ክቡር ሥጋዋ ተባርከውበታል፡፡ እሷም እንደ ልጇ ትንሳኤ በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ተነስታ በይባቤ መላእክት በልጇ ብርታት ወደ ሰማይ አርጋለች፡፡

በእረፍቷ ቀን የተከናወነውን ድንቅ ምጡቅ የመሰወር ምስጢር ያላየው ወንጌላዊው ቶማስ ነው፡፡ በነሐሴ 14 ቀነ በተገለጸው የእመቤታችን ሰማያዊ ምስጢር በቦታው ያልተገኘው ቅዱስ ቶማስ በተቀበረች በ3ኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ከልጇ ጎን ሆና፣ በደመና ተጭና፣ በመላእክት በዝማሬ ቃና፣ በእዝራ መሰንቆ በዳዊት በገና፣ ታጅባ ወደ ልጇ ሰማያዊ ርስት ልትገባ ስታርግ በሰማይ ላይ ያገኛታል፡፡

ትንሳኤዋንና እርገቷን ወንድሞች ሐዋርያት አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት በመንፈሳዊ ቅናት፣በብስጭት በማለት ‹‹በፊት የልጅሽን አስደናቂ ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ፣አሁን ደግሞ ያንቺን የእናቴን ትንሳኤ ሳላይ›› ብሎ ከማዘኑ የተነሳ ከደመናው ተወርውሮ፣ ሊወድቅ ሞክሮ ነበር፡፡

በዚህን ጊዜ ወለላይቱ አዛኝቱ እመቤታችን ከእሱ ሌላ ትንሳኤዋን ሐዋርያት እንደላዩ ነግራው አጽናናችው፡፡ ሄዶም ለወንድሞቹ ሐዋርያት የሆነውን እና ያየውን እንዲነግራቸው አዛው ምስክር እና ምልክት ይሆነው ዘንድ ሰበኗን /መቀነቷን/ ሰጥታው እሱ ወደ ምድር፣ እሷ ወደ ሰማያዊው ክብር አርጋለች፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም ወደ ወንድሞቹ ኢየሩሳሌም እንደደረሰ በመጀመሪያ የሰማው የእመቤታችንን ማረፍ እና በእነሱ እጅ መቀበሯን ነው፡፡

እሱም ሰምቶ እንዳልሰማ፣ አውቆ ምስጢሩን ደብቆ ‹‹የምትነግሩኝ ነገር እንዴት ሊሆን ይችላል? ደግሞስ ሞት በጥር፣ በነሐሴ መቃብር አይሆንም›› በማለት ይከራከራቸዋል፡፡ ሐዋርያትም ‹‹አንተ ደግሞ ቀድሞ የጌታን ትንሳኤ ተጠራጠርክ አሁን ደግሞ አላምንም ልትል ነው›› ብለው የፍቅር ቁጣ ተቆጥተው ተያይዘወ በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት ወደ መካነ ቀብሯ ሄደው ቢመለከቱ መቃብሯ ባዶ ሆኖ የከበረውን ሥጋዋን ስላጡ፣ እጅግ ደነገጡ፡፡
5.2K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:54:50

3.9K views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ