Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @memehirhenok
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 12.40K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2022-10-03 23:09:48

174 views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 23:02:08

455 views20:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 22:54:10

492 views19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 17:56:09
1.3K views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 17:55:49 #_ታላቅ_የንግሥ_በዓል_ጥሪ!

#_መስከረም_21_ቀን_ቅዳሜ_በወይን_አምባ_ማርያም!

ሼር በማድረግ ለእመቤታችን ልጆች አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል አንዱ መስከረም 21 ቀን የሚውለው በዓል ሲሆን ይህም ‹ብዙኃን ማርያም› በመባል ይታወቃል፡፡

መስከረም 21 ቀን ቅዳሜ በወይን አምባ ማርያም እመቤታችን ትነግሣለች፣ ልጆቿንም ትባርካለች። ስለዚህ በእለቱ መጥታችሁ እመቤታችንን አንግሡ፣ ከበዓሉ በረከት ተቋደሱ። ከንግሡ በኃላ ሰፊ የእመቤታችን ዝክር አለ ስለዚህ ከበዓሉ ረድኤት ከዝክሩ በረከት መጥታችሁ ተካፈሉ።

በነገራችን ላይ መስከረም 21 ቀን የእመቤታችን በዓል በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል። አንደኛው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አርዮስን በኒቂያ ለማውገዝ እና ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ዘንድሮ ግሸን ማርያም ያልሄዳችሁ ወይን አምባ መጥታችሁ እመቤታችንን አክብሩ አንግሡ።

#_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ቤተ ኮርስቲያኑ በር ላይ ያወርዷቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

መስከረም 16-1-2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2.0K viewsedited  14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 22:23:40

692 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 21:14:24
1.8K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 21:14:17 #_የአዲሱ_ዓመት_የንስሐ_እና_የቄደር_ጥምቀት_ጥሪ!

#_አዲሱን_ዓመት_በንስሐ_ሕይወት_እንጀምር!

#_እሑድ_መስከረም_15_ጠዋት_2_ሰዓት

#_በወይን_አምባ_ቅድስት_ማርያም_ቤተ_ክርስትያን!

"የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም"

#_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

#_ቄደር_ለምን_እንጠመቃለን?

#_ቄደር_በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

የነፍስ ጉዳይ ነውና ሳትቸኩሉ በደንብ አንብቡት!

"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት ለጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።" 1ኛ ጴጥ 4፥3

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_ሼር_በማድረግ_የነፍስ_ግዴታዎትን_ይወጡ!

እግዚአብሔር "ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ" ስላለን ጾሙን በንስሐ፣ በቄደር እንቀድሰው። /ት.ኢዮ 1፥14/

ተወዳጆች ሆይ አዲሱን ዓመት ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ሰጥቶናል እኛም ጀምረናል። ነገር ግን እግዚአብሔር ዓመታትን የሚሰጠን ንስሐ እንድንገባ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ነው። አዲስ ዓመት ተሰጠን ማለት አዲስ የንስሐ ዕድል ተሰጠን ማለት ነው።

እግዚአብሔር አዲሱን ዓመት እንዲባርክልን፣ ዘመናችንን የበረከት የረድኤት የስኬት የአምልኮት ሕይወት እንዲያደርግልን እሑድ መስከረም 15 ጠዋት 2 ሰዓት በወይን አምባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን የቄደር ጥምቀት እና ንስሐ የመስጠት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። እባካችሁ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ኑ። በተቻለ መጠን ደጇ ሁለት ሰዓት ድረሱ!

በምትወዷት በእመቤታችን እማጸናቹኃለሁ በ 2014 ዓ.ም የሠራነውን ኃጢአት ወደ አዲሱ ዓመት ይዘነው ከተሻገርን እንዲሁም በአዲሱ ዓመት ከበደልን ንስሐ እንግባ።

የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር።

#_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣

ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣

ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን።

ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል።

በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል።

ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ እሑድ መስከረም 15 ቀን ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ።

የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ።

የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም።

የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ።

ስለዚህ እሑድ መስከረም 15 ቀን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ወይን አምባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ።

#_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ቤተ ኮርስቲያኑ በር ላይ ያወርዷቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ሐሙስ መስከረም- 12-15 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2.2K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 22:21:55

2.3K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 19:30:25

3.4K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ