Get Mystery Box with random crypto!

#_ታላቅ_የንግሥ_በዓል_ጥሪ! #_መስከረም_21_ቀን_ቅዳሜ_በወይን_አምባ_ማርያም! ሼር በማድ | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_ታላቅ_የንግሥ_በዓል_ጥሪ!

#_መስከረም_21_ቀን_ቅዳሜ_በወይን_አምባ_ማርያም!

ሼር በማድረግ ለእመቤታችን ልጆች አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል አንዱ መስከረም 21 ቀን የሚውለው በዓል ሲሆን ይህም ‹ብዙኃን ማርያም› በመባል ይታወቃል፡፡

መስከረም 21 ቀን ቅዳሜ በወይን አምባ ማርያም እመቤታችን ትነግሣለች፣ ልጆቿንም ትባርካለች። ስለዚህ በእለቱ መጥታችሁ እመቤታችንን አንግሡ፣ ከበዓሉ በረከት ተቋደሱ። ከንግሡ በኃላ ሰፊ የእመቤታችን ዝክር አለ ስለዚህ ከበዓሉ ረድኤት ከዝክሩ በረከት መጥታችሁ ተካፈሉ።

በነገራችን ላይ መስከረም 21 ቀን የእመቤታችን በዓል በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል። አንደኛው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አርዮስን በኒቂያ ለማውገዝ እና ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ዘንድሮ ግሸን ማርያም ያልሄዳችሁ ወይን አምባ መጥታችሁ እመቤታችንን አክብሩ አንግሡ።

#_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ቤተ ኮርስቲያኑ በር ላይ ያወርዷቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

መስከረም 16-1-2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ