Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @memehirhenok
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 12.40K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 28

2022-10-14 21:23:35

5.2K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 21:27:39
5.5K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 21:27:27 #_የንስሐ_እና_የቄደር_ጥምቀት_ጥሪ!

#_እሑድ_ጥቅምት_6_ጠዋት_2_ሰዓት

#_በወይን_አምባ_ቅድስት_ማርያም_ቤተ_ክርስትያን!

"ጥሩ ውኃንም እረጭባችኃለሁ እናንተም ትጠራላችሁ" ሕዝቅ 36፥25

"የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም"

#_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

#_ቄደር_ለምን_እንጠመቃለን?

#_ቄደር_በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

የነፍስ ጉዳይ ነውና ሳትቸኩሉ በደንብ አንብቡት!

"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት ለጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።" 1ኛ ጴጥ 4፥3

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_ሼር_በማድረግ_የነፍስ_ግዴታዎትን_ይወጡ!

ተወዳጆች ሆይ እሑድ ጥቅምት 6 ጠዋት 2 ሰዓት በወይን አምባ ማርያም ቤተ ክርስትያን የቄደር ጥምቀት እና ንስሐ የመስጠት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። እባካችሁ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ኑ። በተቻለ መጠን ደጇ ሁለት ሰዓት ድረሱ!

የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር።

#_ቄደር_ለመጠመቅ_የሚያበቁን_ኃጢአቶች_የትኞቹ_ናቸው?

ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣

ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣

ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን።

ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል።

በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል።

ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ እሑድ ጥቅምት 6 ቀን ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ።

የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ።

የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም።

የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ።

ስለዚህ እሑድ ጥቅምት 6 ቀን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ወይን አምባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ።

#_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ቤተ ኮርስቲያኑ በር ላይ ያወርዷቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ሐሙስ ጥቅምት 3-1-15 ዓ.ም
አዲስ አበባ
5.3K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 18:29:47

5.1K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 17:26:19

1.9K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:49:45
1.1K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:49:34 ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይድረሰውና ጌታችን ምድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማዕቷ ለትውልድ የሚተላለፍ የዘላለም ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ መታሰብያዋን ያደረገ ስሟን የጠራ በስሟ ቤተ ክርስትያን የሠራ፣የተራበውን በስሟ ያበላ፣የተጠማውን በስሟ ያጠጣ፣የገድሏን መጽሐፍ የጻፈውን፣ያጻፈውን፣ያነበበውን፣የተረጎመውን፣ሰምቶም በልቡ ያኖረውን፣የልቡን መሻት እንደሚፈጽምለት እና በመንግስተ ሰማያት እንደ እርሷ የክብር አክሊል እንደሚያቀዳጀው፤ሥዕሏን አሥሎ በክብር በቤቱ አስቀምጦ ሽቶ እየረጨ ቢጸልይበት ጸሎቱ እንደሚሰማና ልብን የሚመስጥ ጣፋጭ የሆነ መዓዛ እንደሚያሸተው፣ወንድ ልጁንና ሴት ልጁን በስሟ የሰየመ በመንግስተ ሰማያት የበለጠና የከበረ ስም እንደሚሰጣቸው፣ዕጣን፣ስንዴና መብራትን፣ልብሰ ተክህኖ፣መጋረጃ ቢሰጥ በሞቱ ቀን የብርሃን ልብስ እንደሚለብስ፣ያለ ወቀሳ ያለከሳ ባህረ ሲኦልን ተሻግሮ መንግስቱን እንደሚወርስ ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡

ሰማዕቷን ከሌሎች ቅዱሳን ልዩ የሚያደርጋት ታሪክ

በግብጽ አገር አርባ ዓመታት የነገሠ ባለ 12 ክንፉ ብጹአዊ አቡነ ሙሴ የሚባሉ ታላቅ ጻድቅ አሉ፡፡ እኝህ ጻድቅ ከንግስና ወደ ምንኩስና የተሸጋገሩ መንፈሳዊ አርበኛ ናቸው፡፡

ታድያ እኝህ ጻድቅ የቅዱሳን፣የሰማዕታትን ዓጽም እሰበሰቡ ደግላቸውን እያጻፉ፣ቤተ ክርስትያን በመስራት፣ታቦታቸውን በማክበር፣በበዓላቸውም ቀን ይቀድሱ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን ታቦት ለማሰናዳት፣ሜሮን ለመቀባት ወደ ቤተ መቅደስ በገቡ ጊዜ በወርቅ የተለበጠ እና በላዩ በሮማይስጥና በጽርዕ ቋንቋ የብጽዕት ቅድስት አርሴማ ስም የተጻፈበት አንድ ጽላት ያገኛሉ፡፡ ያን ጊዜ የቅዱሳንን ስማቸውን አሰቡ፡፡ የገድላቸውንም ዜና መረመሩ፡፡ ግን የቅድስት አርሴማን ግድልና የሞቷን ዜና አላገኙም፡፡ ስለዚህም ነገር በምን ዘመን ሰማዕት እንደሆነች እና የሰማዕትነቷን ሥራ ያስረዳቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አመለከቱ፡፡

ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለአቡነ ሙሴ ተገልጦ ‹‹ብጽአዊ ሙሴ ሆይ የብጽእት አርሴማን ሥራ እነግርህ ዘንድ ስማ፡፡ ይህቺ ሰማዕት ገና አልተጸነሰችም፣አልተወለደችም፤በወርቅ ዓምድ በሕይወት መጽሐፍ ስሟ ተጽፏል እንጂ፡፡ ነብዩ በመጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይጻፋል እንዳለ እርሷም በኋለኛው ዘመን ሰማዕት ትሆናለች፤በዓለም ዳርቻ ሁሉ የገድሏ ዜና ይታወቃል፡፡

ተአምሯ የሚነገረው በኢትዮጲያ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብጽዕት ቅድስት አርሴማን የስም መታሰብያ መጥራት አትተው፡፡ ጽላትዋም ከአንተ ጋር ይኑር፡፡ የመቅደስዋም ህንጻ በህንጻህ ቦታ ጎን ይኑር፡፡ ስምህ በተጠራበትም የስሟ መታሰብያ ይጠራል›› ብሎ መልአኩ ወደ ላከው እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡

አቡነ ሙሴም የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ ሰማዕቷም ገና ሳትወለድ በፊት እንደ እመቤታችን በእግዚአብሔር ህሌና ታስባ ትኖር ነበር፡፡ እኛም እንደ እንደ ጻድቁ አቡነ ሙሴ በሰማዕቷ ጸሎት እና ቃል ኪዳን ልንጠቀምባት ይገባል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዮንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶም ስለ ዮፍታሔ ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነብያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና›› ነው ያለው፡፡ /ዕብ 11÷32/ እኔም ስለ እዚች ድንቅ ብርቅ እና ከወርቅ በላይ የከበረች ከአልማዝም በላይ የተወደደች ስለ ሰማዕቷ ለመተረክ ጊዜ ስለማይበቃን እዚህ ላይ ይብቃን፡፡

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ ጸሎት፣በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

በድጋሚ የተለጠፈ

መስከረም 29/1/15 ዓ.ም
አዲስ አበባ
2.0K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 20:49:33 #_አርሴማ_ቅድስት_ሰማዕት

#_አጠር_በጠር_ያለ_ታረኳ

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ- ማርያም

ሼር በማድረግ ለሰማዕቷ ለወዳጆችዋ አድርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከሚያከብሩ ብሩካን ከሆኑ፤በጾም በጸሎት በስግደት በትጋት ከሚኖሩ ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስ ከእናቷ ከቅድስት አትናስያና በጥር 6 ቀን የተወለደች ደገኛ የገድል አርበኛ ናት፡፡

በተለይ ስትወለድ ይህ ቀረሽ የማትባል እጅግ መልከኛ እና ግርማዋ የሚያስፈራ ነበር፡፡ እናት እና አባቷም በጾም በጸሎት በስዕለት ስላገኟት እስከ 3 ዓመት ካሳደግዋት በኃላ በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም በተሰራች ቤተ ክርስትያን ታገለግል ዘንድ ሰጧት፡፡ እመቤታችንን 12 ዓመት አገልግላ ያለፈቃድዋ በቤተሰቦችዋ ግፊት በ15 ዓመቷ ዳሯት፡፡ ሰማዕቷ ግን ዓለማዊ ሕይወት ባለመፈለግዋ ወደ ገዳማዊ ምናኔ ህይወት ገብታለች፡፡

በዚያን ዘመን ብዙ ሰማዕታት ያስፈጀ ጨካኙ የሰው አውሬ ካሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ መላኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሴት ሊያገባ ሽቶ በየአገሩ ሁሉ ፈልገው መርጠው ያመጡለት አንድ አሽከሮቹን አዘዘ፡፡

እንግዲህ የሰማቷ አሳዘኝ የመከራ ሕይወት ከዚህ ነው የሚጀምረው፡፡

የዲዮቅልጥያኖስ ሠራዊቶች አርሴማ የምትባል ውብ ሴት በሮሜ በአንድ ገዳም እንዳለች ሰሙ፡፡ አዋቂዎችም የሰማዕቷን ውብ መልኳን ስለው ለንገሡ ለዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት፡፡ ንጉሡም ስዕሏን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና በሥጋዊ ጋብቻ አብሯት ሊኖር እንዳሰበ ለመኳንንቱ ነግሮ ለሠርግ እንዲመጡ አዘዘ፡፡

ቅድስት አርሴማ ይህንን በሰማች ባወቀች ጊዜ ከደናግሉ ጋር የንጉስ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነው አርመንያ አገር ሸሸች፡፡ ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ የከበረች አርሴማን አስፈልጎ ባጣት ጊዜ በአርመንያ እዳለች ሰማ፡፡

ዲዮቅልጥያኖስም ለአርመንያው ንጉሥ ለድርጣድስ ከእሱ ሸሽታ እንደሄደች እና ባስቸኳይ አስጠብቆ እንዲልክላት አዘዘው፡፡ ደናግሉ ይንን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሰወሩ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን በክብር ያመጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ሰማዕቷም ወደ እርሱ መምጣትን እንቢ ባለች ጊዜ በመሬት እየጎተቱ ወደ ንጉሡ አቀረቧት፡፡

ድርጣድስ የቅድስት አርሴማን ደም ግባት እና ውበት ባየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ የመንፈስ እናቷን አጋታን አባብላ እሺ ታሰኛት ዘንድ አዘዛት፡፡ አጋታም ወደ ሰማዕቷ ሄዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት ‹‹እወቂ ይህ ርኩስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ምሽራሽን ክርስቶስን እንዳትተይ›› ብላ አጸናቻት፡፡

ንጉሥ ድርጣድስም ሰማዕቷን ይዞ ወደ እልፍኝ ሊያስገባት ከአደባባይ መካከል ተነስቶ ድንግል አርሴማ በእጁ ያዛት፡፡ በዚያን ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው፡፡ ድርጣድስም በጦትነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለነበር በታናሽ ብላቴና ስለተሸነፈ መኳንንቱ ፊት ስለተዋረደ አፈረ፡፡

ከዚህ በኃላ በሰው አንደበት ለመናገር የሚከብድ መከራና ስቃይ አጸናባት፡፡ ሰማዕቷም ከንጉሡና ከጋሻ ጃግሬዎቹ የሚደርስባትን መከራ በመታገስ በረታች፡፡ ንጉሥ ድጣድስ በሰማዕቷ ላይ የሚያደርሰውን ሥጋዊ መከራ የልቡ ስላልደረሰለት ጡቷን በማስቆረጥ ዓይኗን በወረንጦ በማስወጣት ቢያሰቃያትም ሰማዕቷ ይበልጥ በክርስቶስ ፍቅር ጸናች፡፡ በሚደርስባትም ነገር ደስ ተሰኘች፡፡

ወዳጆቼ እኛ በሚደረስብን ሥጋዊ ህመም ስቃይ መከራ ፈተና እንደሰታለን? አንደሰትም ይልቁንም እናማርራለን፡፡ ምንያቱም የክርስቶስ የመከራ ሕይወት ውስጣችን ስላልገባ ነው፡፡ ክርስቶስ ጋር ለመድረስ መንገዱ፣በአጋንንት እና በሥጋ እየተጎዱ መሆኑን ስለማንረዳ ነው፡፡ ብንረዳም የደስታ እንጂ የመከራ ትከሻ ስለሌለን ነው፡፡ የመከራ ትከሻ ቢኖረንም ትዕግስት ስለሌለን በመከራችን አንጸናም፡፡

በመጨረሻም ንጉሥ ድርጣድስ የሚያደርገውን ሲያጣ አንገቷን በሰይፍ ሊያስቆርጥ ወሰነ፡፡ ከዚህ በኃላ ንጉሥ ድርጣድስ ቡርክት ቅድስት አርሴማን ወደ መገደያ ወንዝ እንዲወስዷትና በዚያም የከበረ ራሷን ይቆርጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን ወታደሮች አንገቷን ሲቆርጧት ያይ ዘንድ ከእርሷ ጋር ወጣ፡፡ ሰማዕቷ በምትገደልበት ትይዩ ከሠራዊቱ ጋር ተቀመጠ፡፡

የእጃቸው ክንድ የበረታ ልባቸው ግን የጨከነ ሮማውያን ወታደሮች ሰይፍ ይዘው ወደ ሰማዕቷ ቀረቡ፡፡ ሰማዕቷ ሞቷ ሰማያዊ እረፍቷ ስለሆነ በደስታ ትመለከታቸው ነበር፡፡ ቅድስት አርሴማም ወታደሮቹን የጸሎት ጊዜ እንዲሰጧት ጠይቃቸው ፈጣሪዋን ካመሰገነች በኃላ ፊቷን ወደ ምስራቅ መልሳ ወገቧን ታጥቃ አንገቷን ከፍ አድርጋ ለሚቆርጧት ታመቻችላቸው ነበር፡፡

ቆራጮች ወታደሮች ከቅድስት አርሴማ ግርማ የተነሳ ደንግጠው ሰይፋቸውን እንደያዙ በምድር ላይ ወደቁ ሰይፋቸውንም ጣሉ፡፡ ሰማዕቷም እያበረታታች ‹‹የታዘዛችሁትን ፈጽሙ›› ትላቸው ነበር፡፡ ወታደሮቹም ‹‹እኛስ ወዳንቺ መቅረብ እና አንገትሽን መቁረጥ አልቻልንም በግንባርሽ ላይ ያለው ትዕምርተ መስቀል አስፈርቶና፤ግንባርሽን ካልሸፈንሽልን አንገትሽን ፈጽሞ ልንቆርጥ አንችልም›› አሏት፡፡

ሰማዕቷም ለወታደሮቹ ፊቴን የምሸፍንበት ቁራጭ ልብስ ወይም ቁራጭ ጨርቅ ስጡኝ አለቻቸው፡፡ እነሱም ቁራጭ ጨርቅ ጣሉላት እሷም ፊቷን ሸፈነች፡፡

ቅድስት አርሴማም ንጉሥ ድርጣድስ እና ሠራዊቱ ሕዝቡም እየተመለከቱ ምስከረም 29 ቀን አንገቷን በሰይፍ ቆረጡ፡፡ ወዳጆቼ እኛን ጌታችን እንደ እነ ቅድስት አርሴማ፣ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ፣ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ወዘተ አንገታችሁን ተቆረጡልኝ ሰማዕት ሁኑልኝ አላለንም፡፡ ኃጢአትን ከእናንተ ሰውነት ቆርጣችሁ ጣሉት ነው ያለን፡፡

የዝሙትን ፍላጎት ከሰውነታችሁ ቁረጡና ደም አላባ ሰማዕት ሁኑ ነው የተባልነው፡፡ የኃጢአቶችን ተቀጽላ ከሥጋችሁ ላይ ቁረጡና በንስሐ ጻድቅ ሁኑ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት በደማችሁ ዋጋ ገነት ግቡ ሳይሆን በደሜ ፈሳሽት መንግስቴን ውረሱ ነው ያለን፡፡ እንደ ሰማዕታት ጽኑ መከራን በሥጋችሁ ተቀበሉ ሳይሆን ቅዱስ ሥጋዬን ብሉና የርስቴ ተካፋይ ሁኑ ነው ያለን፡፡ ሰማዕት ሁኑ ሳይሆን በእኔ መስዋዕትነት ዳኑ ወደ መንግስቴ ጎዳና አቅኑ ነው ያለን፡፡ አወይ አለመጠቀማችን እንደ እኛ ያደለው ማን አለ?

ቅድስት አርሴማም በሰይፍ ስትሰየፍ ከአንገቷም ደም፣ ውኃ፣ ወተትና ማር እንደ ክረምት ነጠብጣብ እየተንጠባጠበ መነጨ፡፡

ደም ከአንገቷ የመነጨው ስለ ሃይማኖትዋ ቆራጥነት ስለ ሞት አለመፍራት እና የጌታችንን መከራ ተሸክማ ሰማዕት ስለሆነች ነው፡፡

ውኃ የፈሰሰው ስለ ብዙ ጸሎትዋ፤ስለልመናዋና የቤተ ክርስትያን መጻሕፍትንና ምስጢራትን ሁሉ ልብ ስለምታደርግ ነው፡፡

ወተት የመነጨላት ስለ ክብሯ ስለ ከፍታዋ እና ንጽሃ ድግልናዋን ስለጠበቀች ነው፡፡

ማር የወረደው ስለሚያስደንቅ የፊቷ ወዝ፣ደም ግባቷ፣ስለ ጣፋጭ የከንፈሯ ቃልና የሰማዕታት ሁሉ እህት ስለሆነች ነው፡፡

ከዚህ በኃላ ብሩህ የሆነ የደመና አምድ ወረደና በላይዋ ጋረዳት፡፡ ወደ ሰማይም እንደ መብረቅ ሳባት፡፡ የቅዱሳን መላእክትም ማህበር ነፍሷን አሳረጓት፡፡ በክብር በእልልታ በዝማሬና በማህሌት ሃሌ ሉያ እያሉ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አስገቧት፡፡

እርሷ እንደ ሞተች ባወቁ ጊዜ ወታደሮቹ ደናግሉን ሁሉ ጫማቸውን እየበሱ እራሳቸውን ቆረጡ፡፡ ቁጥራቸውም ሰባ ሁለት ነፍሳት ነበሩ፡፡

ቃል ኪዳንዋ
1.7K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 15:50:28

2.0K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 21:26:05
2.7K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ