Get Mystery Box with random crypto!

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehirhenok — ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @memehirhenok
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 12.40K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2022-09-19 09:15:02

3.4K views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 17:31:13
3.8K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 17:31:04 አንዳንዴ ሊወልዱ ጥቂት ወራት እና ጥቂት ቀናት ብሎም ዕለቱን ለፅንስ ክትትል ምርመራና ለመውለድ ሆስፒታል ሲሄዱ በሐኪሞች ‹‹ፅንሱ ልክ አይደለም፣ ጠፍቷል›› ተብሎ ጆሮ ጭው፣ ልብ ክው የሚያደርግ መርዶ የሚሰሙት በዛር፣ በዓይነ ጥላና በመተት ድግምት በሚፈጠር አሳዛኝ ክሥተት ነው፡፡

ልብ ካላችሁ እህቶቼ ብዙ ፅንሱ ከመጨናገፉ በፊት አንዳንዶች ሕልም ያያሉ፡፡ የሆነ ጥቁር ሰው ሲታገላችሁ፣ ማኅፀናችሁን ሲረግጣችሁ፣ ሲመታችሁ፣ የምትወዱትን ነገር ታግሎ ሲነጥቃችሁ፣ የሆነ ሰው እላያችሁ ላይ ሲከመርባችሁ፣ ሲያንቃችሁ እና ሲተናነቃችሁ ወዘተ ታልማላችሁ፡፡

ይህ የሚሆነው ከእርግዝናችሁ የቀና የቤተሰብ ዛር፣ ዓይነ ጥላ እና በተለይ በትዳራችሁ፣ በእርግዝናችሁ የሚቀናባችሁ ሰው የመተት አጋንንት ሲያስልክባችሁ እና ክፉ መናፍስቱ ሲዋጋችሁ ነው፡፡ ይህን ሕልም ስታዩ የዛኑ ቀን አልያም በጥቂት ቀናት ውስጥ ምንም ሳትሆኑ በድንገት ደም ይፈሳቹኃል ከዛም ፅንሱ ይቋረጣል፡፡

5ኛ/ መስተፋቅር ፦

መስተፋቅር ማለት አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ያለ ፍላጐትዋ በአጋንንት ጥበብ እንድትወደው ማድረግ ነው፡፡ መስተፋቅር የተደረገበት ሰው ከፍተኛ ፍቅር ውስጥ በመግባት በቤተሰብ እንኳን ተው/ተይ ቢባሉ ከቤተሰብ እስከ መለያየት ተወራርደው እንቢኝ ይላሉ፡፡

በመስተፋቅር የተጀመረ ትዳር ትልቁ ችግር እግዚአብሔር የመሠረተው ሳይሆን በሰይጣን ጥበብ የተመሠረተ ስለሆነ አይጸናም፡፡ በጊዜ ሂደት ምስጢሩ ይወጣል አልያም መስተፋቀሩ ይከሽፋል፡፡ ያኔ በመናፍስት ጥበብ ያዋረሱት ፍቅር እንደ ጉም ይተንና የተደረገበት ሰው እንደ ሰመመን መርፌ ከነቃ ሁሉም ነገር ይበላሻል፡፡

በመስተፋቅር በተመሠረተ ትዳር የሚወለዱትም ልጆች የመናፍስቱ ሰለባ ይሆናሉ፡፡ ጤና ከማጣት እስከ መደንዘዝ ይደርሳሉ፡፡ በመስተፋቅር በተመሠረተ ትዳር የሚወለዱት ልጆች የአጋንንቱ ግብር ናቸው፡፡

ትዳሩ የተመሠረተው እና ልጆቹም የሚመጡበት መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለማይወደድና ብሎም ስለማይባረኩ የእናት ወይም የአባታቸው አጋንንት እየተጠናወታቸው ለሀገር እና ለወገን በተለይም ለቤተ ክርስቲያን የማይጠቅሙ፣ ከጥቅማቸው ጥፋታቸው ያመዘነ ልጆች ይሆናሉ፡፡

6ኛ/ ቡዳ ፦

ወዳጆቼ እንደ ቀልድ የምንሰማውና የምናየው የቡዳ መንፈስ ጣጣው ብዙ ነው፡፡ አንዲት ሴት በውበቷ፣ በጸጉሯ፣ በቁመናዋ የአጋንንት ጥርስ ውስጥ ገብታ፤ በቡዳ መንፈስ ተበልታ ከሆነ በትዳር ሕይወቷ እጅጉን ልትቸገር ትችላለች፡፡

በተለይ በጸባይ እና በልጅ ማጣት ትቸገራለች፡፡ የቡዳ መንፈስ ያለባት ሴት አመሏ ንጭንጭ ይላል፣ ሆድ የሚብሳት እና ለቅሶ የሚቀድማት ናት፡፡ በተለይ መልከኛ ከሆነች ራስዋን የምትጥል፣ ለውበቷ ግድ የሌላት ዝርክርክ ትሆናለች፡፡

እንዲሁም የቡዳ መንፈሱ በማኅፀኗ ውስጥ አሸምቆ በመደበቅ ፅንስ ሊያጨናግፍባት እና ሊያጠፋባት ይችላል፡፡ በቡዳ ዓይኗን ከተበላች ዓይኗን ያቃጥላታል፣ አጥርቶ የማየት ችግር ይገጥማታል፣ ውበቷ ይበላሻል ለምሳሌ ፊቷ እንደ ማድያት ባለ ሁኔታ ይበልዛል፣ በወጣትነቷ ፊቷ የአሮጊት ፊት ይመስላል፣ ያለ እድሜዋ ፊቷ ይሸበሸባል፡፡ ማኅፀኗን ይቆርጣታል የሚገላበጥ እና ውስጡ የሆነ ነገር ያለ መስሎ ይሰማታል፡፡

ወዳጆቼ ስለ ቡዳ ካነሳን እንደው እርግዝና በቡዳ እንደሚበላ ታውቃላችሁ? ብዙዎቻችን የቡዳ መንፈስ በውበት በደም ግባት ወዘተ የሚገባ ብቻ ይመስለናል፡፡ ግን እርግዝናም በቡዳ ይበላል፡፡ እናቶቻችን ሲያረግዙ ማርገዛቸውን ለሰው የማያሳውቁት፣ እርግዝናቸውን በልብስ ደረብረብ አድርገው የሚሸፍኑት ከዓይነ ወግ ቡዳ ራሳቸውን ለመጠበቅ ብለው ነው፡፡ ልብ ካላችሁ አንዳንድ ሴቶች እርግዝናቸው ያምራል፡፡ ከቁመናቸው ጀምሮ እስከ ፅንሱ አቀማመጥ ላያቸው ለዓይን ደስ ይላሉ፡፡

የቡዳ መንፈስ ደግሞ ከዓይን ተነስቶ ወደ ሰው የሚገባ መንፈስ ስለሆነ እርግዝናቸውን በቡዳ ይበላል፡፡ ከዛማ ብዙም ሳይቆዩ አቅለሸለሸኝ፣ አመመኝ፣ ማኅፀኔን ቆረጠኝ ወዘተ በማለት ደም ሊመታቸውና ፅንሱ ሊጨናገፍ ብሎም ሊጠፋ ይችላል፡፡

ስለዚህ እባካችሁ እርጉዝ ስትሆኑ ፅንሱን ሰው ይይልኝ፣ ማርገዜን ምቀኞቼ ይወቁልኝ፣ ዓይናቸው ደም ይልበስ እያላችሁ ስስ ልብስ በመልበስ አትታዩ፡፡ በተለይ የመውለጃ ጊዜያችሁ ሲደርስ ሰው የሚበዛበት ቦታ በመታየት እና በመዝናናት ስም ዞር ዞር ከማለት ታቀቡ፡፡

ቤቢ ሻወር እያላችሁ እርግዝናችሁን በቡዳ አታስበሉ፡፡ ቤቢ ሻወር ብላችሁ እዩልኝ እንዳላችሁ በቡዳ የተበላ፣ ጤና ያጣ ልጅ ወልዳችሁ ልጄን አትዩብኝ፣ ደብቁልኝ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፡፡

ወዳጆቼ ከላይ ያየናቸው ርኩሳን መናፍስት፣ በትዳራችን ላይ ጣልቃ በመግባት፣ ካለመግባባት እስከ መለያየት ሊያደርሱን ስለሚችሉ በትዳራችን ውስጥ የሚፈጠሩትን ነገሮች ረጋ ብሎ፣ አስተውሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡

በተረፈ ትዳራችሁ በክፉ መናፍስትም ይሁን በሰው ተንኮል ችግር ውስጥ ከገባ፣ የወለድናቸውም ልጆች እክል ከገጠማቸው ንስሐ ገብተን፣ በጸሎት በርትተን በአምልኮት ሕይወት ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር ከመለስን ምህረቱን፣ ቸርነቱን ወደ እኛ ይመልሳል፣ መፍትሔም ይሰጠናል፡፡

ቀናችሁን በጸሎት ጀምሩ፣ ማታ በጸሎት እደሩ!

መስከረም 8-1-15 ዓ.ም

አዲስ አበባ
4.3K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 17:31:04 እንዲሁም የፅንሱን ደም በመጠጣት ልጁን ለራሳቸው ይገብራሉ፡፡ በተለይ የቤተሰባችን ባዕድ አምልኮ ካለ እንደ ዛርና ዓይነ ጥላ ያሉ መናፍስት ዘራችንን በማምከን ሴቷን ማኅፀኗን በመዝጋት፤ ብታረግዝም ፅንሱን በማጨናገፍ፤ ቢወለድም ጤናማ ያልሆነ ልጅ ለምሳሌ ንቃተ ኅሊናው የቀነሰ፣ የአእምሮ እድገት ውሱንነትና የአካል እድገት መዘግየት ያለበት፣ በተለይ ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ ልጆች እንዲወለዱ በማድረግ ከፍተኛውን ሚና ይጫወታሉ፡፡

እኛም እነዚህን ክሥተቶች በሳይንሱ መንገድ በመረዳት ፈታኛችንን እንዳንዋጋ ቀድመን በሥጋ እውቀት ተመልተናል፡፡ ብናውቅም ከመረዳት ውጪ በጸሎት መዋጋትን ስለማንሻ የጨለማው ዓለም ገዢ ሰለባዎች እንሆናለን፡፡

እነዚህ የአጋንንት ፍላጻዎች እንዳይወጉን ስለ ትዳራችን ጤናማነት፣ ጽነስ ከመፈጠሩ በፊት በቡራኬ እንዲመጡ አብዝቶ መጸለይን ስላልቻልን፣ ልጀቻችንን መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ሳይሆን ርኩስ መንፈስ የተጠናወታቸው እንዲሆኑ እናደርጋለን፡፡

እኛ ወላጆች በመንፈሳዊ ሕይወት ዝለት፣ በጸሎት ድክመት ምክንያት በልጆቻችን ላይ የሕይወት ዘመን የመከራና የፈተና ጦስን እናወርሳቸዋለን፡፡

የዛር መንፈስ እየባሰ ሲመጣ በተለይ ደም የለመደ ከሆነ አባትና ልጅን፣ ልጅንና እናትን፣ ወንድምና እህትን፣ በማጣላት ደም ሊያፋስስ ይችላል፡፡ ደሙን እንደ በዓል ግብር ይጠቀምበታል፡፡ ስለዚህ ፅንስ ከአንድም ሁለቴ ሲጨናገፍ፣ በማሕፀን ውስጥ ሲጠፋ ዝም ብለን በየሕክምናው ከምንሮጥ ቆም ብለን ወደ ኋላ እናስብ፡፡

ብዙ ጊዜ የቤተሰቦቻችንን ጣጣ ችግሮቻችንና የችግሮቻችን መንስኤ ሆነው እናገኛለን፡፡ ስለዚህ ወደ ጠበሉ ወደ ጸሎቱ ፊታችንን መልሰን ወደ ፈጣሪ ብንማጸን መፍትሔ እናገኛለን ጤናማ ልጅ እንወልዳለን፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በሳይንሱ ስም የተሰጣቸው፣ ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በማኅፀን በአጋንንት ከመጨናገፍ ተርፈው ግን የአጋንንት ሰለባ ሆነው የተወለዱትን ልጆችን አጋንንት እንዴት ለከፋ ሕይወት እንደዳረጋቸው እግረ ብዕራችንን እንይ፡፡

ለምሳሌ በሕክምናው ‹‹ዳውን ሲንድረም›› የሚባልም ሕመም አለ፡፡ ይህም የእድገትና የአእምሮአዊ መዘግየትን የሚያስከትለው የዘረ መል ክሮሞዞም 21 ችግር ነው፡፡ ይህ ያልተለመደ የሕዋስ ክፍፍል ከክሮሞዞም 21 ተጨማሪ የዘረ መል (ንጥረ ነገር) ውጤት ሲመጣ የተከሠተ የዘር ቀውስ ነው፡፡

ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች ከውልደታቸው ጀምሮ የተለያዩ ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡ እነርሱም ፡- የሰውነት ጡንቻ መልፈስፈስና አቅም ማጣት፣ ትንሽ ጭንቅላት፣ ትንሽ ጆሮ፣ ትንሽ አፍ፣ አጭር አንገትና ከአንገት ጀርባ ደግሞ ከመጠን ያለፈ የተረፈ ቆዳ፣ ሰፋፊ አፍንጫ ናቸው፡፡

የሕመሙ ምልክት ከዚህም ከፍ ሲል በቋሚነት የሚገለጥባቸው መንገዶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ፡- የዕውቀት ጉድለት፣ ከሌሎች ሰዎች ያነሰና ሾጠጥ ያለ ራስ ቅል፣ የልብ ሕመም፣ ጆሮአቸው ድምጽ መሰብሰብ አቅሙ አናሳ የሆነና የመስማት ችግር ያለበት፣ በሽታ የመከላከል አቅም ማጣት፣ በአፍ መተንፈስ፣ ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት፣ የእንቅልፍ ችግር ፣ የእይታ ችግር ወዘተ …ናቸው፡፡

እንዲሁም ኦቲዝም (Autism) የተባለውን ብንመለከት ኦቲዝም በማኅበራዊ መስተጋብር እና ግንኙነት ፣ እንዲሁም በተገደበ እና ተደጋጋሚ በሆነ ባሕርይ ተለይቶ የሚታወቅ የእድገት በሽታ ነው፡፡ ኦቲዝም ያለባቸው ወላጆች በልጆቻቸው ሕይወት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ምልክቶችን ያስተውላሉ፡፡

ሌላው አልዛይመርን ብንመለከት አብዛኞቹ የሳይንስ ሊቃውንት በሰዎች ላይ አልዛይመር የሚከሠተው በአንጎል ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ የዘረ መላዊ ፣ የአኗኗር ዘይቤዎች እና አካበቢያዊ ምክንያቶች ውሕደት በመፍጠር እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ከአንድ በመቶ በታች የሆነው የአልዛይመር በሽታ የሚከሠተው በተወሰኑ ሰዎች ላይ በዘር ለውጦች ምክንያት ነው፡፡

ግን ዋና ዋና ምልክቶቹ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ፣ ግራ መጋባት ፣ የአእምሮ ማሽቆልቆል፣ የመረዳት ችግር፣ በምሽት ሰዓታት ግራ መጋባት፣ መገለል፣ መርሳት፣ የትኩረት ማነስ፣ ትውስታዎችን አለመፍጠር፣ የተለመዱ ነገሮችን ለይቶ አለማወቅ፣ ጠብ መፍጠር፣ ብስጭት፣ ራስን በተገቢው መልኩ አለመንከባከብ፣ ትርጉም የለሽ ቃላትን መደጋገም፣ እረፍት ማጣት፣ እየተንከራተቱና ሲጠፉ መዋል፣ ሥነ ልቦናዊ ድብርት ወዘተ ናቸው፡፡

እነዚህ ከላይ ያየናቸው የሾተላይ የዳውን ሲንድረም፣ የኦቲዝም፣ የአልዛይመር ምልክቶች ተብለው የተጠቀሱት በሙሉ ክፉ መናፍስት/አጋንንት፣ ዛር፣ ዓይነ ጥላ፣ ብዳ ወዘተ/ በሕፃናት እና በልጆች እንዲሁም በአዋቂዎች ላይ ሲያድሩ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡ አንዳንዱ ላይ መልክአ አጋንንት ተሥሎባቸው የሚወለዱ አሉ፡፡ ያ ማለት አስፈሪ ገጽታን ተላብሰው የሚታዩ፤ ሲያዩዋቸው የሚያሳዝኑ ሳይሆን የሚያስፈሩ ልጆች ሆነው ይታያሉ፡፡

አጋንንት ከሥጋቸው ሲዋሐዱ ራሱን በሰው ገጽታ ሲገልጽ ልጆቹ አስፈሪ ገጽታን እንዲላበሱ ያደርጋል፡፡ ዛር እና ዓይነ ጥላ የልጆች ፊት ላይ ሲቀመጥ እራሱን በመሳል እራሱን በመምሰል ከተፈጥሮ ወጣ ያለ ገጽታ እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡

እነዚህ ችግሮች በጊዜ ከታወቁ በጸሎት፣ በጸበል በእምነት እና በቅብዓ ቅዱስ መፍትሔ እና ድህነት የሚገኝባቸው ናቸው እምነት ትእግስት ፅናት ላላቸው፡፡ ካልሆነ ግን ችግሩን እና በዚህ የተቸገሩትን ልጆች ይዞ መኖር ነው፡፡

4ኛ/ መተት ፦

አንድ ሰው በአንድ ሰው በመቅናት የሚያደርገው የምቀኝነት የአጋንንት ሥራ ነው፡፡ መተት በትዳር ዕድል በልጅ በባል/በሚስት በመቅናት የሚደረግ ክፉ አሠራር ነው፡፡ በትዳር ላይ መተት ከተደረገ ፈጣን የባሕርይ ለውጥ ማምጣትና ሰላም ማጣት ከዛም እስከ መለያየት የሚደርስ መጠላላት በመሃላቸው ሊፈጥር ይችላል፡፡ ታዲያ ሁለቱም በተለይም የተጋቢዎች ወገን የአጋንንቱን አሠራር ባለመረዳት ፍቺን እንደ አማራጭ በማየት በችኮላ፣ ትዕግሥት በማጣት አጋንንቱን ይተባበራሉ፡፡

የቤተሰብ ጣልቃ መግባት ለአጋንንቱ ጥሩ ከለላ ስለሚሆንና ቤተሰብን በጐ በመሰለ ሐሳብ በመደገፍ ይገባባቸውና በእነርሱ አድሮ የመለያየትን ሥራ ይሠራል፡፡ የሚያሳዝነው ሁለቱ ተፋቺዎች ምክንያት ያለው በሚመስል ባልታወቀ ምክንያት ተለያይተው ሌላ ቢያገቡ ትዳራቸው ከድጡ ወደ ማጡ ነው የሚሆንባቸው፡፡ ቀድሞ አጋንንት ስላፋታቸው ሁለተኛው ትዳር ውስጥ ጣልቃ በመግባት ማበጣበጥ ሰላም መንሳት ይጀምርና ያለያያል፡፡

በዚህም ተፋቺው ‹ትዳር› የሚባለው ነገር ሲነሳ ግፍግፍ በማለት ለልጆቻቸውና ለወዳጆቻቸው የትዳርን መጥፎ ገጽታ ብቻ በመናገር ቤተሰብን ተጽዕኖ ውስጥ በመክተት ታናናሾችንና ልጆችን ‹ትዳር ከእርሷ ወዲያ ላሳር› በማለት ትዳርን እንዲፈሩ ፈርተውም እንዳያገቡ በማድረግ ቆሞ ያስቀራል፡፡

ለዚህ መፍትሔው በትዳር ያልተጠበቀ ክሥተት ሲፈጠር መጸለይና አባቶችን በጸሎት እንዲረዱ ማድረግ፣ በተቻለ አቅም ጠበል መጠመቅ፣ ችግሩን ማወቅና ለችግሩ መፍትሔ ማግኘት ይቻላል፡፡

ወዳጆቼ በትዳር በመቅናት የሚመተት መተት ልክ እንደ ዛር እና ዓይነ ጥላ ፅንስ ሊያጨናግፍ እና ፅንስን በማኅፀን ውስጥ ሊያጠፋ ይችላል፡፡ በተለይ እርጉዝ ሴት ሆና የመተት አጋንንት ከተላከባት በማሕፀኗ ውስጥ ያለውን ፅንስ ስለሚመታውና ስለሚያድርበት ፅንሱ ሊጨናገፍ እና ሊጠፋ ይችላል፡፡
2.3K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 17:31:04 #_የርኩሳን_መናፍስት_ፈተና_በትዳር_ሕይወት

#_ክፉ_መናፍስት_በትዳር_እና_በሩካቤ_ሥጋ_ጣልቃ_መግባት

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!

ተወዳጆች ሆይ ክፉ መናፍተስ በትዳር ሕይወታችን፣ በሩካቤ ሥጋ ደስታችን እንዴት ጣልቃ እየገቡ እንደሚበጠብጡ እና እንደሚያናውጡ በዝርዝር እናያለን። እኔ ሳልሰለች የጻፍኩትን እናተ ሳትሰለቹ አንብቡት።

1ኛ/ ዓይነ ጥላ

ዓይነ ጥላ ገርጋሪ ምቀኛ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ ይህ ክፉ መንፈስ አድብቶ በመተናኮል ዕድላችንን በመዝጋት እጃችን ገባ ያልነውን ነገር በማሳጣት ይተናኮላል፡፡ ዓይነ ጥላ አብረውን ከሚወለዱና ተወልደን ከጊዜ በኋላ ከሚጠናወቱን ክፉ መንፈስ አንዱ ነው፡፡

ዓይነ ጥላ ያለባቸው ባል ወይም ሚስት በትዳራቸው ሰላም፣ ፍቅር፣ መግባባት በመሃላቸው በፍጹም አይኖርም፡፡ በተለይ በሩካቤ ሥጋ አይስማሙም፣ አይጣጣሙም፣ አይግባቡም፡፡

የዓይነ ጥላ መንፈስ ተጠቂ ከሆኑ እንኳን ሩካቤ ሥጋን በመፈቃቀድ ሊፈጽሙ ቀርቶ አብሮ መተኛት መተቃቀፍ አይወዱም፡፡ መንፈሱ የባልን ሰውነት ወይም የሚስትን ሰውነት እንደ ባዕድ አካል በማሳየት እንዲቀፈው/እንዲቀፋት በማድረግ ምክንያት የሌለውን ጥላቻ በመሃላቸው ይዘራል፡፡ በሩካቤ ሥጋም ደስታ የሚባል ያሳጣቸዋል፡፡ ሩካቤ ሥጋን የሚፈጽሙት ስለተጋቡ ብቻ እንጂ ወደውና ፈቅደው አይደለም፡፡ ደመ ቀዝቃዛ ያደርጋቸዋል፡፡

ከትዳር በፊት ወደ ሕይወታቸው ሰተት ብሎ የገባው መንፈስ በትዳራቸው ውስጥ ራሱን በተለያየ ጠባይና መልክ በመግለጥ፣ ለትዳራቸው መበጣበጥ እና መናወጥ ምክንያት ይሆናል፡፡ በማግባታቸው የተበሳጨው ዓይነ ጥላ በትዳር ኑሮአቸው ውስጥ የበቀል መርዙን እየረጨ፣ ትዳሩን እያቀጨጨ ለፍቺ ይዳርጋል፡፡

ዓይነ ጥላ በትዳር ሕይወት ሰላም በመንሳት እና በሩካቤ ሥጋ ጊዜ ስሜት በማጥፋት፣ የሩካቤ ሥጋ ደስታን በማበላሸት የተካነ ስለሆነ የመንፈሱን ጠባይ አውቃችሁ ልትነቁበት እና በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ልትዋጉት እንዲሁም በቅዱስ ቁርባን ጸጋ ከሕይወታችሁ ልታርቁት ይገባል፡፡ ምክንያቱም መንፈሱ ሸፍጠኛና ከጠባይ ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ የብዙዎችን ትዳር ለፍቺ አብቅቷል፡፡

2ኛ/ ዛሮች፦

ከሁለት አንዳቸው ዛር እና የዛር ውላጅ፣ ወንድ ወይም ሴት ዛር ካለባቸው ትዳራቸው አደገኛ ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ ዛሩ ስለሚቀና ባልና ሚስትን ለማተራመስ ኩርፊያን፣ ንትርክን ጭቅጭቅን፣ ብስጭትን፣ አለመግባባትን፣ አለመተዛዘንን፣ ጥላቻን እንደ ግብዓት በመጠቀም ፍቅርን በማቀዝቀዝ ትዳሩን በፍቺ መንገድ እንዲጓዝ ይዳርጋል፡፡

ባስ ሲልም ደም የለመደ ዛር ከሆነ ጸብ በማንሳት ደም ያፋስሳል ከተቻለም ነፍስ ያዋድቃል፡፡ ዛሩ በአባትና በእናት ላይ ካለ በግንኙነት ወቅት ከዘር ጋር በመዋሐድ በማኅፀን ከፅንሱ ጋር አድጐ በመወለድ ደባል ሆኖ ያድጋል፡፡ ዛር እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ በመውረድ ቤተሰብን በማፈራረስ ሰላማቸውን በመደምሰስ ቤተሰብን ይዘበራርቃል፡፡

ዛር ልጆች ከተወለዱ በኋላ በልጆች እእምሮ በማደር አእምሮአቸውን በመዝጋት ትምህርት እንዳይገባቸው በማድረግ ቤተሰብንና ተማሪውን ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ በዚህም ልጁ በቤተሰብ እንዲጠላ ያደርገዋል፡፡ ፍራቻን እያስተማረ ያሳድገውና በራስ መተማመኑን በማጥፋት ለቤተሰቡ ለሀገሩ ደንታ ቢስ በማድረግ ውድ ሕይወቱን በመውረስ ለራሱ ለጥፋት ዓላማ ይጠቀምበታል፡፡

ሌብነትን፣ ወንጀልን፣ ክፉ ሱስን፣ መጠጥን፣ ዝሙትን፣ ጠበኛነትን እና ነውጠኝነትን በማስለመድ ምግባረ ቢስነትን በማላበስ የእርግማን ትውልድ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ወላጆች ሆይ ልጆች የሚታነጹት በእናንተ መልካምና እኩይ መሠረት ላይ ስለሆነ ዛሬ እንደ ቀልድ የዘራችሁትን ነገ መከመር እስኪያቅታችሁ ድረስ ስለምታጭዱ ልትጠነቁና በእውነተኛው መንገድ ልትሄዱ ይገባል፡፡ ዛሬ ‹‹የተረገመ ያልተባረከ›› እያላችሁ የምትረግሙት ልጅ ትላንት የናንተ ወይም የቤተሰባችሁ ጠንቅ ተርፎት ነውና ልታዝኑላቸው ይገባል፡፡

የዛር መንፈስ አንዱ መጥፎ መገለጫው በዓል በመጣ ቁጥር ለምሳሌ በዘመን መለወጫ፣ በገና እና በትንሣኤ በዓላት የቤተሰቡን ደስታ ለማጥፋት እና ሰላም ለመንሳት የማይረባ እና ውኃ የማያነሳ አለመግባባትንና ጠብን ተጠቅሞ ቤተሰቡን በማተራመስ፣ የበዓሉን ዐውድ ያጠፋባቸዋል፡፡

ወዳጆቼ በባል ወይም በሚስት ላይ የራሳቸው አልያም የዛር መንፈስ ካለ ካላወቁበት እና ካልነቁበት መቼም ቢሆን በዓል በመጣ ቁጥር መጣላታቸው፣ በዓልን በኩርፊያ ማሳለፋቸው አይቀርም፡፡ እንዲሁም ከሁለት አንዳቸው ላይ በሕመም ተመስሎ በመቀመጥ ለበዓል የደስታ መዋያ ያሰቡት ገንዘብ የሐኪም ቀለብ ያደርጋል፡፡

ከላይ እንደጠቀስኩላችሁ በተለይ የወንድ ዛር በሴቷ ላይ ካለ ከባሏ ጋር ሩካቤ ሥጋ መፈጸም ቀርቶ አብሮ መተኛት እና ማውራት ያስጠላታል፡፡ ሌሊት ከባሏ አጠገብ ተኝታ በእንቅልፍ ልቧ የወንድ ዛሩ ይገናኛታል፡፡ በደመ ነፍስም በተኛችበት የሚጫናት፣ የሚነካት፣ ሰውነቷን የሚዳስሳት ሰው መሰል ነገር ይሰማታል፡፡

እንዲሁም ሴት ዛር በወንዱ ላይ ካለች በተለይ በስንፈተ ሩካቤ ይጠቃል፡፡ በሕልመ ሌሊትም እጅጉን ይመታል፡፡ ጠባዩ እየተቀያየረ በውኃ ቀጠነ ይጨቃጨቃል፣ እንደ ሕፃን ይነጫነጫል፡፡ ሚስቱ ታስጠላዋለች፡፡ አብሯት ቢተኛም ሩካቤ ሥጋ ለመፈጸም እጅጉን ይቸገራል፡፡ በባል ላይም ሴት ዛር ካለች በሚያውቃት እና በማያውቃት፣ በቤተሰብ እየተመሰለች ሌሊት በተኛበት ትገናኘዋለች፡፡

3ኛ/ ፅንስን የሚያጨናግፉ እና በማሕፀን የሚገድሉ ክፉ መናፍስት/ሾተላይ ፦

ብዙዎች በተደጋጋሚ የፅንስ መጨናገፍ እና በማኅፀን ውስጥ የፅንስ መጥፋት ያጋጥማቸዋል፡፡ በተለይ በማኅፀን ውስጥ ፅንስ ሲጠፋ በሕክምናው ሾተላይ ተብሎ ስም ይሰጠዋል፡፡

ሕክምናው የሕክምናውን ጥበብ እንጂ የክፉ መናፍስቱን ተንኮል ስለማያውቅ ከቤተሰቦቻችን በወረስናቸው፣ በራሳችንም ባመጣናቸው የዛር መንፈስ እንዲሁም በዓይነ ጥላና እና በመተት በድግምት ፅንስ እንደሚጨናገፍ እና በማኅፀን እያሉ እንደሚጠፋ አያውቅም፡፡ ስለዚህ የተጨናገፈውና በማኅፀን የሚጠፋው ፅንስ ሁሉ ሾተላይ ይባላል፡፡
አጅሬም በሾተላይ ስም ራሱን ሰውሮ ሥራውን በገሃድ ይሠራል፡፡

በነገራችን ላይ ሕክምናው በተደጋጋሚ ፅንስ የመጨናገፍ ችግር የሚገጥማቸውንና የፅንሱን የመጨናገፍ ምክንያት በውል የማያውቃቸውን ‹‹መንስኤው የማይታወቅ›› ወይም በሕክምናው ቋንቋ ‘አይድዮ ፓቲክ’ ይለዋል፡፡

በሕክምናው ሾተላይ የሚባለው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጌቲቭ /Rh-/ ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ /Rh +/ የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ አር ኤች ፓዘቲቭ የሆኑ የደም ሕዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል፡፡ ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ሕይወት ፍጻሜ ድረስ ይኖራል፡፡

በዚህም በማኅፀንዋ ውስጥ የያዘችውን ፅንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ፅንሱን እንደ ባዕድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል ፅንሱም ይጠፋል በማለት ይገልጻል፡፡

ወዳጆቼ ከላይ እንዳየነው ሾተላይን ወደ መንፈሳዊው ዓለም ስናመጣው ፅንስን የሚያጨናግፍ እና በማኅፀን እንዳለ የሚያጠፋው የቅድመ አያቶቻችን፣ የአያቶቻችን፣ የእናት አባታችን ዛር እንዲሁም ዓይነ ጥላና እና መተት ድግምት ነው፡፡ አጋንንት፣ ሰይጣን፣ ዛር፣ ዓይነ ጥላ ፅንስን ተዋሕደው በማጨናገፍ ይታወቃሉ፡፡
2.8K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 07:22:48

3.5K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 19:55:33
4.9K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 19:55:19 ይሄ ሲሆን ነው በመንፈሳዊ ሕይወታችን በሁለት እግራችን የምንቆመው፡፡ ካልሆነ ግን መንፈሳዊ ሐንካሳ ሆነን መንፈሳዊ ሕይወታችን መውደቅ መነሳት ያለበት፣ የክፉ መናፍስት ውጊያ የበረታበት፣ ጸጋ፣ በረከት፣ መለኮታዊ ቡራኬ የሌለበትን ሕይወት እንኖራለን፡፡

ጨለማውን የሚያርቅ ብርሃንን ይዘን የሚጨልምብን፣ መድኃኒቱን ይዘን ሕመም የሚበረታብን፣ ምግቡን በእጃችን ይዘን የሚርበን፣ መፍትሔውን ይዘን የምንቸገር፣ በረከቱን ይዘን አመድ አፋሽ የምንሆን፣ ዘላለማዊ የመንግሥተ ሰማያት ክብር ይዘን ጊዜያዊ እና ኃላፊ ነገር ሰቅዞ የሚይዘን እንዳንሆን በየእለቱ የአምልኮት ሕይወትን ልንለማመድ እና ልንለምድ ይገባናል፡፡

ከባለፈው ስህተታችን ታርመን፣ በአዲሱ ዓመት አዲስ በረከት እና ብርቱ የአምልኮት ሕይወት ይዘን እንድንበረታ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ ወለላይቱ እመቤት በተቀደሰው ጸሎቷ ታግዘን።

በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት!

መስከረም 3-1-15 ዓ.ም

አዲስ አበባ
4.5K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 19:55:18 ብርቱ መንፈሳዊነት ይልቁንም የአምልኮት ሕይወት በመወለድ ሳይሆን በመለማመድ የምናገኘው በረከት ነው፡፡

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!

ተወዳጆች ሆይ ብዙዎቻችን ብርቱ መንፈሳዊነት ይልቁንም ጥሩ የአምልኮት ሕይወት ጸጋው የምናገኘው አብሮን በመወለድ ሳይሆን በመለማመድ ነው፡፡ በእርግጥ ጸጋ እግዚአብሔርን፣ የተጋድሎ እና የአምልኮት ሕይወትን በመለማመድ ሳይሆን በመወለድ ያገኙ ብዙ አሉ፡፡ እነሱም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቅዱሳን ናቸው፡፡

ለምሳሌ ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርሚያስ የነብይነት ጸጋ ያገኘው ተጋድሎ ሳይሆን ነና በእናቱ ማኅፀን ሳለ እግዚአብሔር ቀድሶት መርጦት ነው፡፡ ለዚህም ነው እግዚአብሔር ‹‹በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፣ ከማኅፀን ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፣ ለአሕዛብም ነብይ አድርጌሃለሁ›› ያለው፡፡ /ኤር 1÷5/

እንደ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገገ፣ አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ሊባኖስ፣ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ወዘተ ያሉት ቅዱሳን ተወልደው ከማገደላቸው በፊት ለአምልኮት እና ለተጋድሎ ሕይወት በመወለድ አግኝተዋል፡፡ ነገር ግን በመወለድ ያገኙትን ጸጋ እግዚአብሔር የተጋድሎ ሕይወትን በመለማመድ እና በመልመድ ጸጋቸው አሳድገዋል ከትልቅ ማዕረግ ደርሰዋል፡፡

መለማመድ ወይም መልመድ የምንለው የእለት ተእለት የአምልኮት እና የተጋድሎ ሕይወት ነው፡፡ የተጋድሎ እና የአምልኮት ሕይወት የምንለው ጾም፣ የጸሎት፣ የስግደት፣ የትጋት፣ የትእግስት፣ የመንፈሳዊ ቆራጥነት እና ለፈጣሪ ያለን ታማኝነት ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች እኛ ምዕመናን አስቀድመን እንደ ቅዱሳን በመወለድ ሳይሆን በየእለቱ በመለማመድ የምናመጣቸው፣ የምናሳድጋቸው፣ እና ጸጋ እግዚአብሔርን የምናገኝባቸው ናቸው፡፡

ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ ምዕዋት፣ ትእግስት፣ ቸርነት፣ ትህትና፣ መልካም ሥነ-ምግባር የምናገኛቸው እና የምናዳብራቸው በየእለቱ በመለማመድ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው 20 ደቂቃ የማይሞላውን የእለት ውዳሴ ማርያም አዘውትሮ መጸለይ ካለመደ ታላቁን የእመቤታችን ምስጋና የሆነውን ለጥሩ አንባቢ 40 ደቂቃ ለእንደእኔ ላለው አንድ ሰዓት የሚፈጀውን አርጋኖንን በፍጹም መጸለይ አይችልም፡፡ ምናልባት ቢጸልይ የጸሎት ልምድ ስለሌለው ይሰለቸዋል ከዛም ይተዋል፡፡

አንድ ሰው በየቁኑ የአምልኮት ስግት እየሰገደ ስግደትን ካልተለማመድ በቀን በመቶዎች የሚቆጠር ስግደት መስገድ አይችልም፡፡ የስግደት ሕይወት በመወለድ ሳይሆን በመለማመድ ሂደት የምናገኘው ጸጋ ነው፡፡ በቀን ሦስት መቶ ለመስገድ አስቀድሞ በየነቁ ሠላሳ መስገድን መለማመድ እና መልመድ አለብን፡፡ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩትን የተጋድሎ ስግደትን ለመስገድ በመጀመሪያ የየቀኑን የአምልኮት እና ሌሎችንም ስግደቶች መለማመድ እና መልመድ ይጠበቅብናል፡፡

ስግደትን ካለመድን እና ካልተለማመድን ‹‹አንድ ቀን እሰግዳለሁ፣ እሱ ሲፈቅድ እሰግዳለሁ፣ ሲሞላልኝ እሰግዳለሁ›› እያልን የስግደት ጸጋ ጎድሎብን ብዙ ነገር አጉድሎን ዘመናችን ያልፋል፡፡ ወዛችንን፣ ጉልበታችንን፣ ድካማችንን በስግደት ለእግዚአብሔር መስዋእት አድርገን ማቅረብ ሳንችል በከንቱ እንኖራለን፡፡

አብዛኞቻችን ማለት በሚቻል ደረጃ በሥራ፣ በድካም ወዘተ እያሳሰብን ሌሊት 9 ሰዓት ተነስቶ የመጸለይ ልምድ የለንም፡፡ የጠዋቱን ጸሎት እንኳን በመከራ ነው የምንጸልየው የማንጸልይ እንዳለን ሆኖ፡፡ ወዳጄ ሌሊት 9 ሰዓት ተነስቶ ለመጸለይ አስቀድመን ጠዋት 12 ሰዓት ተነስቶ መጸለይን መልመድ አለበን፡፡ ይህንን ካደበርን በኋላ ሊሊት 11 ሰዓት መጸለይም መልመድ እና መለማመድ ከዛ በኋላ በሂደት ሌሊት 9 ሰዓት ተነስቶ መጸለይን እንለምዳለን፡፡

አጅግ የሚገርመው በቤተ ክርስቲያናችን ያሉትን ሰባቱን የአዋጅ አጽዋማት አብዛኞቻችን በተቀመጠላቸው እና በታዘዝነው ሰዓት አንጾምም፡፡ ይልቁንም እስከ 9 ሰዓት ጹሙ ተብለን ‹‹እግዚአብሔር የማያውቀው የለም፣ እስካሁን የጾምኩትን ይቁጠርልን፣ ለበረከት ያድርግኝ›› እያልን የጾም የስንፍና ካባ ለብሰን አሐዱ አብ ሳይባል 6 ሰዓት የምንበላ፣ የባሰብን ደግሞ በጠዋት የምንበላ ሚሊዮኖች ነኝ፡፡

ሰውን ከእግዚአብሔር የምታስታርቀው፣ ለሀገር ምህረት የምታሰጠው፣ ሥጋን ለነፍስ የምታስገዛው፣ ነፍስን የምትቀድሰው፣ ክፉ መናፍስትን ከውስጣችን ነቅላ የምትጥለው፣ የነፍስን ቁስል የምትፈውሰውን፣ ቅዱሳንን እስከ ብቃት የምታደርሰውን ጾም በአግባቡ እና በሥርዓቱ የማንጾመው ጾምን መልመድ እና መለማመድ ስላልቻልን ነው፡፡

በአዋጅ የታዘዝነውን ጾም በራሳችን አዋጅ የምንበላው የጾም ልምምድ እና ልምድ ስለሌን ጭምር ነው፡፡ የጾም ልምድ እና ልምምድ ከሌለን ገና በጠዋቱ ጨጓራችን ይጮሃል፣ አንጀታችን በረሃብ ይላወሳል፣ ሰውነታችን ይደክማል፣ ልባችንን ፍስስ ይላል፡፡

ይህ የሚሆነው የመብላት እና የጾም ልምድ ስለሌለን ነው፡፡ ታውቃላችሁ በዓመት አንዴ ከስቅለት እስከ ጌታ ትንሳኤ ሌሊት ሦስት ቀን እንኳን ልናከፍል/ልንጾም/ ቀርቶ የስቅለት ቀን ጾመን ከዋልን አንጀታችን በአፋችን ሊወጣ የሚደርሰው የጾም ልምድ እና ልምምድ ስለሌለን ነው፡፡

እግዚአብሔር ልጆቹን ይልቁንም ያቀረባቸውን ወዳጆቹን በአምልኮት ሕይወት እና በመከራ ሕይወት መጽናት ያለማምዳቸዋል፡፡ የአምልኮት ሕይወት የለመዱት እና የተለማመዱት ደግሞ በየትኛውም መንፈሳዊ ሕይወት ስኬታማ እና ጽኑአን ናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል›› ያለው የአምልኮት ሕይወትን በመንፈሳዊ እልህ ለሚተገብረው ነው፡፡ /ሮሜ 9÷18/

የሚለምድ ካለ እግዚአብሔር ልጆቹን በአምልኮት ሕይወት፣ በተጋድሎ ሕይወት፣ በመከራ ሕይወት፣ በፈተና ሕይወት ወዘተ ያለማምዳል፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን እንደሚከፍል አውቆ እንደተወደ ባሕረ ኤርትራ ላይ እንዲጣል አደረገው፡፡

ፈርዖን ሙሴን ለመግደት ባሕረ ኤርትራ ላይ ቢጥለውም እግዚአብሔር ግን ሙሴ ወደፊት ባሕረ ኤርትራን በስሙ እንዴት ለሁለት እንደሚከፍለው፣ ሕዝቡን እንዴት እንደሚያሻግርለት ያለማምደው ነበር፡፡

አብዛኞቻችን ‹‹ለምን አትጸልዩም፣ ለምን አትጾሙም፣ ለምን አትሰግዱም›› ስንባል ‹‹እግዚአብሔር የፈቀደ ቀን›› እያልን ስንፍናችንን በእግዚአብሔር ፈቃድ ስም እንሸፍናለን፡፡ አንዳንዶቻችን ጥሩ መንፈሳዊ ሰው ለመሆን፣ ወጥ የሆነ በጽናት እና በትእግስት በትጋት እንዲሁም በብርታት የታጀበ የአምልኮት ሕይወት እንዲኖረን በእየለቱ እየተገበርን እውነተኛ አምልኮን ከመለማመድ እና ከመልመድ ይልቅ የአምልኮት ሕይወትን የሚያስፈጽመን፣ የሚያስተገብረን ልዩ መለኮታዊ ኃይልን ከአርያም የምንጠብቅ ብዙ የዋሆች እና ሞኞች አለን፡፡

በጸሎት ቤታችን ያስቀመጥነውን የጸሎት መጽሐፍ ይዘን በጸሎት ሰዓታችን መጸለዩን ትተን እግዚአብሔር አንዳች ኃይል ልኮልን እንዲያጸልየን የምንፈልግ አለን፡፡ ባለን ጉልበት የአምልኮት እና የተጋድሎ ስግደትን መስገድ እየቻልን እግዚአብሔር ልዩ የስግደት ጸጋ ሰጥቶን እንደ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ እንደ መንኮራኩ የሆነ ተአምራዊ ስግደት መስገድ የምንፈልግ የቀን ሕልመኞች አለን፡፡ ባለን ሳንጠቀም የሌለንን ከእግዚአብሔር የምንጠብቅ ድርቅ ያለን አለን፡፡

ወዳጆቼ ወደድም ጠላንም ቀደምት አባቶቻችን በሄዱበት፣ በተጓዙበት የአምልኮት ሕይወት ተጉዘን ከእግዚአብሔር ለመገናኘት፣ ብሎም ዘላለማዊ መንግሥቱን ለመውረስ በየእለቱ የአምልኮት ሕይወትን ለመተግበር እንዳቅማችን መለማመድ እና መልመድ አለብን፡፡
4.3K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 22:23:07

3.7K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ