Get Mystery Box with random crypto!

Fezekir _ فَذَكِّرْ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mdjemal — Fezekir _ فَذَكِّرْ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ mdjemal — Fezekir _ فَذَكِّرْ
የሰርጥ አድራሻ: @mdjemal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-12 16:25:25 #መጅሊስ
____

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከብዙ ፈተና  በኋላ  መጅሊ
ስን መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅትነቱ (NGO staus) አውጥተው በህግ የፀደቀ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች   ተቋም እንድሆን ብርቱ ጥረት አድርገዋል።   የመጅሊሱን  መተዳደሪያ ደንብም ሁሉንም ሙስሊም ማህበረሰብ ባማከለ መልኩ ከብዙ ውጣውረድ በኋላ  እንደፅድቅ አድርገዋል።

ነገር ግን ብዙ ፈተናና ችግር  ያሳለፈውን የመጅሊስ ተቋም  በየክልሉ  እየተደረገ ላለው ሪፎርሙ እንቅፋት እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ይገባል።

ሰሞኑን በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች  የመጅሊስ ሪፎርም በመካሄድ ላይ ይገኛናል። ሆኖም ግን  ደሴና ኮምቦልቻ ባለው የመጅሊስ ምርጫ  ሂደት ውስጥ  አንዳንድ ወንድሞች ለድን ካላቸው ጉጉት እኛ ከሌላው ለድኑ  የተሻልን ነን ብለው በማሰብ   ይሁን ግላዊ የስልጣን  ጥቅምን በማስቀደም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ኺላፍ  እየፈጠሩ  ይገኛሉ።

እስልምና ሀይማኖት በሙስሊሞች መካከል መለያየት (ኺላፍ)  እንዳይኖርና ከተፈጠረም  እንዳይሰፋ አበክሮ ያስተመረ ድን ነው። አላህ ሱወ የሙስሊሞችን አንድነት  ትልቅ ፀጋ (ኒዕማ) መሆኑን በቁርአን ውስጥ እንድህ ሲል ይገልፀዋል:


{ وَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ ۚ لَوْ أَنفَقْتَ مَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مَّا أَلَّفْتَ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ وَلَـٰكِنَّ اللَّهَ أَلَّفَ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ}


" በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው፡፡ በምድር ያለውን ሁሉ (ሀብት) በለገስክ ኖሮ በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር፡፡ ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ፡፡ እርሱ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡"
[ሱረቱ አል-አንፋል :63]
___

አዎ  በዚህ አንቀፅ እንደተገለፀው የኡማው አንድነትና የሙስሊሞች ልባዊ ግንኙነት ምድር ላይ ያለን ነገር ሁላ ቤዛ አድርገን የ
ማናገኘው ከአላህ የተቸረን ፀጋና ትሩፋት ነው።

ይህን ትልቅ የወንድማማችነት  ኒዕማ ከኺላፍ በመራቅና እርስ በርሳችን በመተጋገዝ እንጠብቀው!

አቡ አብድላህ
ጥር 5/ 2015 E.C

Join me

https://t.me/MdJemal
29 views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 20:39:04
30 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 16:39:29 #ፊትና



‏قال شيخ الإسلام ابن تيميةرحمه الله :
إنّنَا في زَمنٍ تَمُوجُ فِيه الفِتَن، وتَتَلاحَقُ فِيه النَوازِل والمِحَن، وعامَة الفِتَن سبَبُها أمرَان:
قلّة العِلم،
وضَعفُ الصَّبر.

ኢብኑ ተይሚየህ رحمه الله  እንድህ ይላሉ:
" እኛ ያለነው በፈተና ማዕበል ውስጥ ነው ፣ ፈተናዎችና አደጋዎች የሚፈራረቁበት ዘመን! የአብዛሀኛዎቹ ፈተናወች መነሻ ደግሞ  2 ምክንያቶች ናቸው:

የእውቀት ማነስና
ትእግስት (ሶብር) ማጣት!"

       مَجْمُوع الْفَتَاوَى ( 5/127 )

አላህ ከፈተና ይጠብቀን! ተፈትነውም ከሚያልፉት ያድርገን!

Follow me

https://t.me/MdJemal
17 viewsedited  13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 10:18:27 #ዚክር


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

"من قال: سبحان الله وبحمده. في يوم مائة مرة، حطت خطاياه، وإن كانت مثل زبد البحر ". 

{በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ ያለ ሰው ሃጢያቶቹ እንደ ባህር አረፋ ቢሆኑ እንኳ ይረግፉለታል።

[ቡኻሪ፡ 6405]
7 viewsedited  07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 17:45:15 #አብደላህኢብኑሰሉል እና መሰሎቹ በሁሉም ዘመን አሉ።
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅

ነብዩ ሶዐወ መካ ውስጥ እያሉ በደረሰባቸው ግፍና በደል ወደ መድና ተሰደዱ! መድናም ውስጥ የነበሩት ደጋግ አንሷሮች ስደተኞችን ተቀብለው አስተናገዱ።  ነብዩንም በገንዘባቸውና በህይወታቸውም ጭምር ረዱ።  ድነልኢስላምም በመድና ምድር ማበብ ጀመረ።

ነብዩ ሶዐወ  በበኒ ሙስጦሊቅ ዘመቻ ላይ እያሉ  በአንድ አንሷርንና ሙሀጅር መካከል ጠብ ተቀሰቀሰ። ሁሉም በየ ብሄሩ መጣራት ጀመረ፣ ይህን ሲመለከቱ  ነብዩ  ሶዐወ በጣም ተቀየሙና እኔ  በመካከላችሁ እያለሁ እንድህ የመሀይ ጥሪ ትጣራላችሁ አሉ። ዘረኝነትን ተዋት እሷ ጥንብ ነች አሉና የተጣሉትን አስታረቁ።

ይህን የሰማው  አብደላህኢብኑሰሉል የተባለው በመድና የሚኖር  ሙናፊቅ  "ጠንካሮቹ ደካሞቹን ከመድና ያስወጣሉ"  ሲል ዛተ።
ከመካ የተሰደዱትን ስደተኞች ለማለት ነው።በዚህ ጊዜ ለሱና መሰሎቹ  የሚከተለው የቁርአን አንቀፅ ወረደ:-

{ يَقُولُونَ لَئِن رَّجَعْنَا إِلَى الْمَدِينَةِ لَيُخْرِجَنَّ الْأَعَزُّ مِنْهَا الْأَذَلَّ ۚ وَلِلَّهِ الْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَـٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ}

«ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከእርሷ ያወጣል» ይላሉ፡፡ አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛውና ለምእምናን ነው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም፡፡
[ሱረቱ አል-ሙናፊቁን - 8]

የኢብኑ ሰሉል መሰሎች በየትኛውም ጊዜና ቦታ አሉና አላህ በፈጠረው ምድር፣ ጠፍ የሆነን መሬት አልምተው የሚኖሩን ማህበረሰቦች መሬታችንን  ካለቃቃችሁ በሚል የዘረኝነት ጭምብል ጭፍጨፋ እየፈፀሙባቸው ነው። ጌታየ እባክህ የተንኮል ኢብኑ ሰሉሎች  በዝተዋልና እጃቸውን ያዝልን! የስራቸውን ስጣቸው።

                كتبه أبو عبد الله
              ህዳር 29/ 2015
        
      
https://t.me/MdJemal
19 viewsedited  14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 19:58:34 {وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ}

"አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡" [ ሱረቱ ኢብራሂም: 42]

ጌታየ ሆይ በዳዮችን ብርቱ የሆነ መያዝን ያዛቸው። ግፈኞች ምድርህን በግድያ፣ በሙስናና በጭካኔ ሞሏት! ፍትህህን አታዘግይብን!
17 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 20:39:23
العبادة والأخلاق 
ስለ አምልኮና  መልካም ስነምግባር ቁርኝት የሚያሳይ መጠነኛ  ኦድዎ ነው! አድምጡት!
22 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 20:21:02 #እስልምና_الاسلام

አላህ ከዋለልን መልካም ፀጋ ሁሉ ትልቁ ውለታ ልባችንን ለኢስላም ክፍት ማድረጉ ነው!

{ فَمَن يُرِدِ اللَّهُ أَن يَهْدِيَهُ يَشْرَحْ صَدْرَهُ لِلْإِسْلَامِ }

[ አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለኢስላም ይከፍትለታል፡፡ ] ሱረቱ አል-አንዓም: 125

*****

ቀጥተኛውን #የኢስላም_መንገድ የያዘ አጓጊ ፍፃሜ ያገኛል። ምክንያቱም ትክክለኛውን የመጓዣ ፍኖት በእጁ ይዟልና። #ሰላም የሰፈነበት #ሐሴት የሞላበት ዘላለማዊ ህይወት። የአላህ ውደታና አጋርነት (ዊላየቱላህ) ሙሉ በሙሉ የሚንፀባረቅበትን ዓለም መውረስ የሚገኘው #በኢስላም ውስጥ ነው፣ በተለይ ኢስላምን ስንማረው፣ ስንተገብረውና ስንኖረውም ጭምር።


{ وَهَذَا صِرَاطُ رَبِّكَ مُسْتَقِيمًا ۗ قَدْ فَصَّلْنَا الْآيَاتِ
لِقَوْمٍيَذَّكَّرُونَ }

" ይህም (ያለህበት) ቀጥተኛ ሲኾን የጌታህ መንገድ ነው፡፡ ለሚያስታውሱ ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘርዝረናል፡፡ "

۞ لَهُمْ دَارُ السَّلَامِ عِندَ رَبِّهِمْ ۖ وَهُوَ وَلِيُّهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

" ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሰላም አገር አላቸው፡፡ እርሱም (ጌታህ) ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ረዳታቸው ነው፡፡ "

[ሱረቱ አል-አንዓም:126 & 127

ከ2 አመት በፊት ፌስቡክ ላይ የፃፍኩት ነው! ሳነበው ለራሴው የኢስላምን ኒዕማ ሳስታውስ ሸር በድጋሜ አደረግኩት!

https://t.me/MdJemal
26 views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 15:53:34 #ስነምግባርን ማሳመር



عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللهِ -صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- قَالَ: (إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ مكارم الْأَخْلَاقِ).

ነብዩ ሶዐወ " እኔ የተላኩት መልካም ስነምግባርን ለማሟላት ነው" ብለዋል።
ኢማሙ ማሊክ ዘግበውታል።

قَالَ رسول الله-صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : "يَا عَائِشَةُ إِنَّ شَرَّ النَّاسِ مَنْزِلَةً عِنْدَ اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ وَدَعَهُ أَوْ تَرَكَهُ النَّاسُ اتِّقَاءَ فُحْشِهِ "
(اتقاء فحشه) أي لأجل قبيح قوله وفعله
قال ابن حجر رحمه الله : "قَوْله : (اِتِّقَاء شَرّه) أَيْ قُبْح كَلَامه".
رواه البخاري ومسلم

የአላህ መልክተኛ ሶዐወ እንድህ አሉ : " ኣዒሻ ሆይ! አላህ ዘንዳ የትንሳኤ ቀን መጥፎ ደረጃ ያለው ሰው፣ ሰዎች መጥፎነቱን ለመጠንቀቅ ሲባል የተውት (የራቁት) ሰው ነው።" ብለዋል።

"ኢትቲቃኡ ፉህሺሂ" የተባለው ከንግግሩና ስራው መጥፎነት ለመራቅ ሲባል ለማለት ነው።

https://t.me/MdJemal
13 viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ