Get Mystery Box with random crypto!

#መጅሊስ ____ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከብዙ ፈተና  በኋላ  መጅሊስን መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅትነ | Fezekir _ فَذَكِّرْ

#መጅሊስ
____

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከብዙ ፈተና  በኋላ  መጅሊ
ስን መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅትነቱ (NGO staus) አውጥተው በህግ የፀደቀ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች   ተቋም እንድሆን ብርቱ ጥረት አድርገዋል።   የመጅሊሱን  መተዳደሪያ ደንብም ሁሉንም ሙስሊም ማህበረሰብ ባማከለ መልኩ ከብዙ ውጣውረድ በኋላ  እንደፅድቅ አድርገዋል።

ነገር ግን ብዙ ፈተናና ችግር  ያሳለፈውን የመጅሊስ ተቋም  በየክልሉ  እየተደረገ ላለው ሪፎርሙ እንቅፋት እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ይገባል።

ሰሞኑን በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች  የመጅሊስ ሪፎርም በመካሄድ ላይ ይገኛናል። ሆኖም ግን  ደሴና ኮምቦልቻ ባለው የመጅሊስ ምርጫ  ሂደት ውስጥ  አንዳንድ ወንድሞች ለድን ካላቸው ጉጉት እኛ ከሌላው ለድኑ  የተሻልን ነን ብለው በማሰብ   ይሁን ግላዊ የስልጣን  ጥቅምን በማስቀደም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ኺላፍ  እየፈጠሩ  ይገኛሉ።

እስልምና ሀይማኖት በሙስሊሞች መካከል መለያየት (ኺላፍ)  እንዳይኖርና ከተፈጠረም  እንዳይሰፋ አበክሮ ያስተመረ ድን ነው። አላህ ሱወ የሙስሊሞችን አንድነት  ትልቅ ፀጋ (ኒዕማ) መሆኑን በቁርአን ውስጥ እንድህ ሲል ይገልፀዋል:


{ وَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ ۚ لَوْ أَنفَقْتَ مَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مَّا أَلَّفْتَ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ وَلَـٰكِنَّ اللَّهَ أَلَّفَ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ}


" በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው፡፡ በምድር ያለውን ሁሉ (ሀብት) በለገስክ ኖሮ በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር፡፡ ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ፡፡ እርሱ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡"
[ሱረቱ አል-አንፋል :63]
___

አዎ  በዚህ አንቀፅ እንደተገለፀው የኡማው አንድነትና የሙስሊሞች ልባዊ ግንኙነት ምድር ላይ ያለን ነገር ሁላ ቤዛ አድርገን የ
ማናገኘው ከአላህ የተቸረን ፀጋና ትሩፋት ነው።

ይህን ትልቅ የወንድማማችነት  ኒዕማ ከኺላፍ በመራቅና እርስ በርሳችን በመተጋገዝ እንጠብቀው!

አቡ አብድላህ
ጥር 5/ 2015 E.C

Join me

https://t.me/MdJemal