Get Mystery Box with random crypto!

Fezekir _ فَذَكِّرْ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mdjemal — Fezekir _ فَذَكِّرْ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ mdjemal — Fezekir _ فَذَكِّرْ
የሰርጥ አድራሻ: @mdjemal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-21 23:40:51
4 views20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 23:39:02
4 views20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 21:35:29 #ቁርአን
#መስጅድ_ፈረሳ

هذه إهانة #القرآن الكريم في ولاية أورمية, حول العاصمة أدس أببا إتيبيا، بعد هدم المساجد بقوة عقلم أورمية.

ይህ ከታች በፎቶ የምታዩት በአዲስ አበባ ዙሪያ ሸገር ሲቲን ለመገንባት ሲባል በፈረሰ መስጅድ ፍርስራሽ ውስጥ የተገኘ የተቀዳደደ #ቁርአን ነው። አፍራሽ ግብረ ሀይሉ የተከበረውን ቁርአንና ኪታቦች እንኳ ለማንሳት ያልፈቀደ አጥፊ ሀይል ነው።ይህን የተከበረ የአላህ ቃልና የተከበረውን መስጅድ ጭምር በማፍረስ እንዳዋረዳችሁን እናንተንም አላህ ያዋርዳችሁ።

This desecration of #Qura'n is in Addis Abeba, Ethiopia.This happend after Government led forces abolished mosques in mass to creat the so called Sheger city. The task force didn't even allow the muslim community to collect religious books including Qur'an.

It is very heart touching news, we have never seen such heinous crime perpetrated on its own people by their own authorities in any country.

#የግፍከተማ #ሸገርሲቲ

           كتبه أبو عبد الله
                                   May 21/ 2015  
          ذول قعدة 01/1444
10 viewsedited  18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 17:25:57
28 views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 17:25:56 #መስጅድ_ፈረሳ

ማቆሚያ የሌለው የኦሮሚያ ክልል መስጅድ ፈረሳ ተጧጡፎ ቀጥሏል።

መስጅድ ለሙስሊሞች ከመኖሪያ ቤትም በላይ የሚያስፈልጋቸው ተቋም ለመሆኑ ነብዩ ሶዐወ መድና እንደገቡ መጀመሪያ የሰሩት ተቋም መስጅድ ነው። አዎ መስጅድ አላህን የምናመልክበት፣ ልጆቻችንን በተርቢያ የምናሳድግበት፣ ብሶታችንን ለአላህ የምናሰማበት፣ የምንማርበት ...ወሳኝ ቦታ ነው።

ለዚህ ሲባል በአለም ላይ ያሉ ሙስሊም ጠል አካላት ጉልበት ሲያገኙ የመጀመሪያ የጥፋት ብትራቸውን የሚያሳርፉት በዚህ ወሳኝ ቦታ ማለትም #መስጅድ ላይ ነው። አዎ ተቋምን ማፍረስ ማህበረሰብን ማፍረስ መሆኑን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ።

አሁንም የኦሮሚያው ክልል መንግስት ይህንን ተግባር ስራየ ብሎ ተያይዞታል። የኦረሚያ ክልልና የፌደራል እስልምና ጉዳዮችን ተማፅኖም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎታል። የፌደራል እስልምና ጉዳዮች ቢጨንቀው ለጠቅላይ ሚኒስተሩ መስጅድ ፈረሳው እንድቆም ደብዳቤ ፅፏል።

ጠቅላይ ሚኒስተሩ መስጅድ ፈረሳውን ያስቆሙት ይሆን? እስከ አሁንስ አልሰሙ ይሆን?

በፈረሳው ምክንያት ከእቃና ፍርስራሽ እንጨት ጋር እየተጫነ ለእንግልት የተዳረገው ቁርአንና ሀድስ አላህ ፊት አያስጠይቀን ይሆን?
እንደ ኡማ በአንድ ላይ ተነስተን ፈረሳውን ማስቆምስ እንደት ተሳነን?

ስልጣንን መከታ በማድረግ ለማህበረሰቡ ምንም አይነት ተለዋጭ ማረፊያ ሳታዘጋጁ በጥላቻ መስጅና የድሀ ቤት የምታፈርሱና የምታስፈርሱ ወቅትዮች አላህ እናንተንም ስልጣናችሁንም ያፍረሰው!

***
#መስጅድ ፈረሳውን ማን ያስቁመው!?

أبو عبد الله محمد
ግንቦት 11/2015
شوال 29/1444
30 viewsedited  14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 12:32:40 #በደል_ያጠፋል፣ ፍትህ ይክሳል!

ሀገራችን ባለፉት አመታት ካሳለፈችው አስከፊ ጦርነት ተላቃ በጦርነቱ ሳቢያ የተመሰቃቀሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ለማስተካከል ብዙ ሸክም ይጠብቃታል::

ይህ ከባድ ሸክም በመንግስት ላይ ብቻ ሳይሆን ይበልጡኑ በህዝቡ ላይ ጫናው የበረታ ነው:: በኑሮ ውድነት፣ በብልሹ አሰራር እና በፖለቲካ ሴራዎች ህይወትን መግፋት ከባድ እየሆነበት ላለው ህዝብ አግባብነት በሌላቸው ውሳኔዎች እና የግል ፍላጎቶች ዜጎች እንዲማረሩ እየተደረገ ይገኛል:

መንግስት ለዜጎቹ ጥላ እና ከለላ መሆን ሲገባው መጠለያ እና ከለላ ነሺ ከሆነ፣ በመግባባት እና በመተማመን መፈታት የሚገባቸውን የማህበረሰብ ችግሮች ኃይልን ብቻ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ለመፍታት ከተሞከረ፣ አቅመ ደካሞችን እና ድሆችን አቅፎ ከችግራቸው ለማላቀቅ ከመልፋት ይልቅ በችግር ላይ ችግር በእነሱ ላይ መጨመር አማራጭ ተድርጎ ከተያዘ፣ የዜጎች በሰላም ወጥተው የመግባት መብታቸው አደጋ ውስጥ ከወደቀ፣ በፈለጉት የሀገሪቷ ቦታዎች ተዟዙሮ የመኖር እና የመስራት ህጋዊ መብቶች ከተነፈጉ፣ ከህግ አግባብ ውጪ በታጣቂዎች እና በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች የሚወሰዱ የዘፈቀደ እስር እና ግድያዎች መበራከት፣ የእምነት ተቋማት እየተደፈሩ በግብረሀይል የሚወድሙ ከሆኑ፣የሀይማኖት ነፃነትን በሚጋፋ መልኩ ሀይማኖታዊ አለባበሶችን የሚገድቡ አመራሮች እዚህም እዛም መኖራቸው፣ በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለው የመተማመን ስሜት እንዲጠፋ እና እንዲሸረሸር ያደርጋል::

ዜጎች የሚደርስባቸውን በደል እና ግፍ ለማስቆም ስሞታቸውን ሲያሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ መጓዝ፣ የበላይ አመራሮች እና ሀላፊዎችም የህዝብን እሮሮ አድምጠው የማስተካከያ እና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ አፋጣኝ አቅጣጫ ከመስጠት ይልቅ ዳተኛ መሆናቸው ሀገሪቷን ለሚመራው መንግስትም ትልቅ ዕዳ ይዞ መምጣቱ አይቀርም::

በደል መጨረሻው ውርደት እና ጨለማ ነው:: ከግለሰብ አንስቶ እስከ ማህበረሰብ በጅምላ የሚፈፀሙ በደሎች እና ግፎች ድምር ውጤታቸው በበዳዮች ላይ ኪሳራን እንጂ አይጨምርላቸውም::

ጌታችን አላህ ሱወ በቅዱስ ቃሉ ይህን ይለናል

"አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው" (ሱረቱል ኢብራሂም:42)

ስልጣን ህዝብን ማገልገያ መሳሪያ ነው:: ይህን ትልቅ ሃላፊነት የተረከበ አመራር ሃላፊነቱን ለመወጣት ቃለመሀላ ሲፈፅም ለህዝብ ታማኝ ሆኜ በቅንነት ላገለግል ቃል እገባለው ያለውን መዘንጋት የለበትም::ሃላፊነቱን በመረከቡ ትልቅ ተጠያቂነትም ይኖርበታል:: ከታችኛው የመንግስት መዋቅር ሲያጠፋ የላይኛው አመራር ተጠያቂነትን እንዲሰፍን ካላደረገ ህዝብን ወደ ምሬት ማስገባቱ አይቀርም::

ህዝብን በእኩልነት እና በፍትህ ማስተዳደር በበደል የጎበጡ ትከሻዎችን እና የቆሰሉ አካሎችን ይጠግናል:: በደልን የሚጠየፍ መሪ ከተጠያቂነትም ይድናል:: ሁሉም ባለድርሻ አካላት ባሉበት የሀላፊነት ደረጃ እኩልነትን፣ ፍትህን እና አገልጋይነትን መርሃቸው አድርገው ሊጓዙ እንደሚገባ ለማሳሰብ እወዳለሁ

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
46 views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 11:42:44
46 views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 11:42:22 #የተርክዬ ምርጫ

በዛሬው እለት በተርክዬ ውስጥ በስድስቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረትና በባባ ኤርዶጋን (ኤኬፔ ፓርቲ) መካከል ከፍተኛ የሆነ ፍክክር ያለበት ምርጫ እየተካሄደ ነው።

#ኤርዶጋን የምርጫ ቅስቀሳውን በሀጅያ ሶፊያ መስጅድ ማታ ላይ ሱረቱ ፋቲሀን በመቅራትና ዱአ በማድረግ ያጠናቀቀ ሲሆን
መፍቀረ አታቱርኩ ከማል ኪሉዳግሩ ደግሞ የአታቱርክ መቃብር በመጎብኘት አጠናቋል።

ከማል ኪሉዳግሩ መፍቀረ ምእራባዊ ሲሆን፣ በፀረ ሙስሊምነትና ኢስላምን ከሽብርተኝነት ጋር ይያዛል በማለት የሚታወቅ ሰው ነው።ግብረሰዶም መብት ነው ይላል። ለምርጫ ቅስቀሳው ሂጃብ መልበስ አንከለክልም ቢልም እንደ አያቱ (አታቱርክ) ፀረ ኢስላምና ቱርክን ወደኋላ የሚያስቀራት እስልምና ነው ብሎ ያምናል።

በተቃራኒው አሁን ቱርክ ወደ ቀድሞ ሀያልነቷ እየመለሰ ያለው ብርቱ ሰው #ኤርዶጋን ደግሞ የተርኪዬ ሃያልነትና ብልፅግና ልከ እንደ ቅድመ አያቶቻችን ወደ ኢስልም መመለስ ነው ብሎ ያምናል። አላህ ያግዘው።

ግንቦት 06/2015 EC (may 14/2023)

Join me

https://t.me/MdJemal
•┈┈• ❀ ❀•┈┈•
•┈┈• ❀ ❀•┈┈•
45 views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 14:12:11 #ዱዓእ


የአላህ ነብያት ልጆቻቸውን በተርቢያ ከማሳደጋቸው ጋር ዘሮቻቸው እንድስተካከሉ ዘወትር አላህን በዱዓ ይማፀኑታል። ነብዩላህ ዘከሪያ ዐ.ሰ እንድህ አሉ፦

{ هُنَالِكَ دَعَا زَكَرِيَّا رَبَّهُ ۖ قَالَ رَبِّ هَبْ لِي مِن لَّدُنكَ ذُرِّيَّةً طَيِّبَةً ۖ إِنَّكَ سَمِيعُ الدُّعَاءِ}

طيبة...مباركة

"እዚያ ዘንድ ዘከሪያ ጌታውን ለመነ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለኔ ስጠኝ አንተ ጸሎትን ሰሚነህና» አለ፡፡"
[ሱረቱ አሊ-ዒምራን : 38]

ادع الله ربك  بهذ الدعاء النبوي   
                  
አላህ ዘሮቻችንን የተባረኩና እና ሷሊሆች እንድያደርግልን ዘወትር እንለምነው።
ይህን ነብያዊ ዱአ እናዘውትረው።

Join me

https://t.me/MdJemal
•┈┈• ❀ ❀•┈┈•
•┈┈• ❀ ❀•┈┈•
14 views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 14:10:17 ስለ #ሒጃብ የተከፈለ መስዋዕትነት

   ይህ ለሒጃቧ ስትል የተሰዋችው ለኒቃቧ ስትል የሞተችው የአንደሉሷ ሙስሊም ሴት እውነተኛ ታሪክ ነው። ከስላና ተቃጥላ ስለሒጃብ ስለክብሯ የወደቀች ድንቅ ሴት! ታሪኳ ሲደመጥ የብዙዎች ቀልብ አንብቷል። ስቃያቸው በስቃይዋ ተደምጧል። ለሒጃባቸው ክብር ያልሰጡ እንስቶች ይገሰፁበት ዘንድ ታሪኳን እንካችሁ
ክስተቱን በአንደበቷ እንዲህ ትተርከው ይዛለች።

    "የትውልድ ቀዬዬ አንደሉስ ምድር ነው። በሃያዎቹ የዕድሜ  እርከን ውስጥ የምገኝ በሰውነት ቅርጼ ሞላ ደልደል ያልኩ ለግላጋ እንስት ወጣት ነኝ። ግና ይህን ሰውነቴን በጅልባብ ሸፍኜና ጠብቄ ሒጃቤን በአግባቡ እለብሳለሁ። የአንደሉስ ሙስሊሞች የስቃይን ፅዋ በመስቀላዊያኑ እጅ ሲጎነጩ እኔም አልቀረልኝም። ለሁለት ዓመታት የለበስኩትን ጅልባብ ሳላወልቅ ሳላጥብና ሳልቀይር እሥር ቤት ከረምኩ። በወታደሮች ግልምጫና ድብደባ መደፈርና መወገር ብዙ መከራዎችን አልፌ የመጨረሻዋ ዕለት ላይ ደረስኩ።

   የለበስኩት ጅልባብ ተሰብስቦ ጉልበቴ ጋር ደርሷል። ሰውነቴ በጭቃ ተለውሶ በእግረ ሙቅ ተጠፍሬያለሁ። እጄ የፊጥኝ ታስሮ አንገቴ ላይ በጠለቀው ሠንሠለት  እየተጎተትኩ ወደፊት እነዳ ይዣለሁ። በብረት ፍርግርጉ ኋላ ሳልፍ ታሳሪዎቹ በሾሉ ዓይኖቻቸው አፍጥጠው እየተመለከቱኝ የስድብ ናዳ አወረዱብኝ ተፉብኝ። አፈር እየበተኑ ድንጋይ ወረወሩብኝ። የእሥር ቤቱ ጠባቂዎች ጅራፍ በእጃቸው ይዘው ከበቡኝ።

   ቀሳውስቱ በአንድነት ቆመው መዝሙራቸውን ያሰማሉ። ባለሥልጣናትና ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው በሚደርስብኝ ስቃይ ለመደሰት ወደ እኔ በትኩረት ይመለከታሉ። ከአንድ ግንድ ጋር ታስሬ ማገዶ በዙርያዬ ተበትኗል። ዘይትና ጋዝ ተርከፍክፎበታል።

   ከቀሳውስቱ አንዱ ወደእኔ ተጠጋ። ሁለት ምርጫ አቀረበልኝ። ጅልባቤን አውልቄ በህዝብ ፊት ይቅርታ እጠይቅ ዘንድ አሊያም ተቃጥዬና ሰውነቴ ነዶ በመሞት መካከል ምርጫ ሰጠኝ። ሒጃቤን እንጂ ሌላን አልመረጥኩም። ከፈለጋችሁ አቃጥሉኝ አልኩ ስለሒጃቤ መሞቴ ለኔ ክብር መሆኑን አላወቁም። አልንበረከክም ፈፅሞ የጌታዬን ትዕዛዝ አልጥስም ብትፈልጉ ሰውነቴን ቆራርጡት ቢያሻችሁም አካሌን አንድዳችሁ አክስሉት። አዎ! በፍፁም በሒጃቤና በክብሬ አልደራደርም። የክብር መገለጫዬ በከፍታ የሚውለበለብ ኢስላማዊ ዓርማዬ ነው ብዬ መለስኩለት።

   ቄሱ የእሳቱን ነበልባል አንስቶ እንጨቱን ለኮሰው። ሰውነቴ መቃጠል ጀመረ። በቀላሉ እንድሞት አልፈቀዱልኝም እሳቱን አጠፉልኝ። ወደእሥር ቤቱ ወሰዱኝ። ይህ የእሥር ቤቱን አጥር ተደግፌ የፃፍኩት እውነተኛ ታሪኬ ነው...." ይህን ማስታወሻ የእስር ቤቱ ግርግዳ ላይ አስፈራው ተገኘ።

   በነጋታው ጠዋት በተመሳሳይ ቦታ የፊጥኝ ታስራ ተሰቃይታ በእሳት ነደደች። ዛሬ ግን እንደትላንቱ አላጠፉላትም። ለዓመታት የኖረችበት ስቃይ እነሆ አበቃ። ግና ነጻነቷን እንደሰጧት አላወቁም።
እኔ ለጻፍኩት እጄ ተንቀጠቀጠ። የጋለ ስሜቴ አንደበቴን ቆለፈው። አጀብ ለእኛ ክብር ስንቶች አልቀዋል። 

አላህ መልካም ስራዋን ተቀብሎ ቀብሯን ኑር ማረፊያዋን ፊርደውሰል አዕላ ያድርግላት።
Mahi Mahisho
22 views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ