Get Mystery Box with random crypto!

Fezekir _ فَذَكِّرْ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mdjemal — Fezekir _ فَذَكِّرْ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ mdjemal — Fezekir _ فَذَكِّرْ
የሰርጥ አድራሻ: @mdjemal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-02-08 15:09:34 #ጥበባዊ_ምክር #الحكمة



ሉቅማኑልሐኪም ከእለታት አንድ ቀን ከነብያት ጋር ነበርኩ ይላሉ። ከእነሱም 8 ንግግሮችን ተማርኩ።

4 ነገሮችን ጠብቅ
1, ሶላት ላይ ስትሆን ልብህን፣
2, ሰዎች ጋር ስተሆን አይንህን፣
3, መጅሊስ ውስጥ ስትሆን ምላስህን፣
4, ስትመገብ ሆድህን ጠብቅ ( ከሀራም፣ ሹብሀና ኢስራፍ ነገሮች) ።
  
     2 ነገሮችን ማስታወስ እንዳትረሳ!

1,ሞት፣
2, ዚክርን ( አላህን ማወደስ)

2 ነገሮችን ደግሞ አታስታውሳቸው!

1, ለሰው ልጆች የዋልከውን መልካም ስራ፣
2, ሰዎች በአንተ ላይ ያደረሱብህን በደል!

የአረብኛው ቪድዎ ከታች አለ፣ ተመልከቱት!
በጣም ደስ ይላል!

Join me

https://t.me/MdJemal
26 viewsedited  12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 13:43:01
34 views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 13:40:50 #Earthquake

በቱርክና በሶሪያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ4300 በላይ ሰዎች ሲመቱ ከ5000 በላይ ህንፃዎች ወድመዋል።

===========================


فَكُلًّا أَخَذْنَا بِذَنبِهِ ۖ فَمِنْهُم مَّنْ أَرْسَلْنَا عَلَيْهِ حَاصِبًا وَمِنْهُم مَّنْ أَخَذَتْهُ الصَّيْحَةُ وَمِنْهُم مَّنْ خَسَفْنَا بِهِ الْأَرْضَ وَمِنْهُم مَّنْ أَغْرَقْنَا ۚ وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيَظْلِمَهُمْ وَلَـٰكِن كَانُوا أَنفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ


" ሁሉንም በኅጢኣቱ ያ ዝነው፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጠጠርን ያዘለ ነፋስን የላክንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ጩኸት የያዘችው አልለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ምድርን የደረባንበት አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ ያሰጠምንው አልለ፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡"
[ሱረቱ አል-ዐንከቡት - 40]

ጌታየ ሆይ የቱርክና ሶሪያ ወንድሞቻችንን  በረህመት አይንህ እያቸው።   እዘንላቸው። የሞቱትን ማራቸው።
30 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 20:10:36 #ሐሜትን እንጠንቀቅ
____

قال سعيد بن جبير - رضي الله عنه - :

يؤتى ب
العبد يوم القيامة فيُدفع له كتابه، فلا يرى فيه صلاته ولا صيامه، ولا يرى أعماله الصالحة؛ فيقول: يا رب هذا كتاب غيري، كانت لي حسنات وليست في هذا الكتاب فيقال له: «إن ربك لا يضل ولا ينسى ذهب عملك باغتيابك الناس».

بحر الدموع لابن الجوزي


ሰዒድ ብኑ ጁበይር ረሂመሁላሁ እንድህ ይላሉ:

የቂያማ ቀን ለአላህ ባሪያ የስራ መዝገቡ ይሰጠዋል። መዝገቡ ውስጥ የሰገደውን ሶላትም ሆነ  ፆም  አያገኘውም፣ መልካም ስራውን ሁሉ ማየት አይችልም።
የዚህ ጊዜ ጌታየ ሆይ! ይህ የኔ የስራ መዝገብ አይደለም የሌላ  ሰው ነው ይላል።እኔ መልካም ስራዎች ነበሩኝ፣ ነገር ግን በዚህ መዝገብ ውስጥ የሉም።
የዚህ ጊዜ  "ጌታህ አይሳሳትም አይረሳምም " ስራህ የተበላሸው ( የጠፋው) ሰዎችን #በማማትህ  ምክንያት ነው ይባላል።

ሀሜት መልካም ስራዎቻችንን ያጠፋል፣ እንጠንቀቀው!   ከዚህ መጥፎ ስነ ምግባር አላህ ይጠብቅን!

Join me

https://t.me/MdJemal
13 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 15:48:59 #ሶላቱል_ጁሙዐ



ዛሬ ኢማማችን በከሚሴ ኹለፋኡራሽድን መስጅድ #የጁሙዓን ሶላት ሲያሰግዱን እያለቀሱ ነበር፤ በተለይ የሚከተለውን አያት ሲቀሩ፣

{ يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي}


«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡
[አል-ፈጅር - 24]

ነገ የውመል ቂያማ የሰው ልጆች ሁሉ ይፀፀታሉ። መልካም የሰራው ሰው ዱንያ ላይ ተመልሸ መልካም ስራ በጨመርኩ ብሎ ሲመኝ ምንም ኸይር ስራ የሌለው ደግሞ ዋሀስረታ (ዋልዳማየ) ይላል።

ይህ ጊዜ ሳይመጣ በዱንያ ላይ እድሉ እያለን በኢባዳ እንበርታ!

Join me

https://t.me/MdJemal
25 viewsedited  12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 16:47:20
22 views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 12:42:48 #የልብ_መድረቅ!
_____

ሀሰነል በስሪ አላህ ይዘንላቸውና  እንድህ ይላሉ:



ልብ በስድስት ምክንያቶች ይበላሻል:

ከዛሬ ከነገ እንፀፀታለን (እንቶብታለን) በማለት ኃጢያት ላይ መዘውተር፣

እውቀትን እየተማሩ ነገር ግን  አለመተግበር፣

ቢተግብሩ እንኳ ኢኽላስ አለመኖር( ስራን ለአላህ ብቻ ብሎ አለመስራት)፣

የአላህን ፀጋ (ሪዝቅ) እየተጠቀሙ እሱን አለማመስገን፣

የአላህን ውሳኔ አለመቀበል፣

ሙታንን ይሸኛሉ ነገር ግን ለራስ አለመገሰፅ

ከፌስቡክ መንደር ወደ አማርኛ የተረጎምኩት ነው!
Join me

https://t.me/MdJemal
30 views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 18:27:00 #የዋሻወቹ_ወጣቶች
_____

የዋሻው  ባለቤቶች ጌታቸውን እንድህ ሲሉ ለመኑ:

{ربنا آتِنا من لدُنك رحمة}

"ጌታችን ሆይ! ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን፤ "
[ ሱረቱ አል ከህፍ፥  10 ]

ጌታቸውም መርሀባ አላቸው።

فاستجاب الله لهم وقال:

{ فَأْوُوا إِلَى الْكَهْفِ يَنشُرْ لَكُمْ رَبُّكُم مِّن رَّحْمَتِهِ}

"…ወደ ዋሻው ተጠጉ፡፡ ጌታችሁ ለእናንተ ከችሮታው ይዘረጋላችኋልና፤ …"
[ሱረቱ አል ከህፍ፥  16]

የአላህ ሱ.ወ እዝነት በህንፃ ውስጥ ሳይሆን በዋሻው ውስጥ ነበር። በእዝነቱ  የወጣቶቹን ሁኔታ ከፍ አደረገው፤ መታወሳቸው ዘላለለማዊ ሆነ፤  ልባቸውን አፀናው፤ ከጠላቶቻቸውም ጠበቃቸው፤ የነሱን ታሪክ ዘውታሪ አድርጎት እስከ ቂያማ ቀን በቁርአን ውስጥ እንድናነበው አደረገ።


رفع شأنهم، خلَّد ذكرهم، ثبَّت قلوبهم، حماهم من عدوهم، وجعل خبرهم خالدا في قرآن نتلوه إلى يوم الدين.

የምንማረው ቁም ነገር

ጌታችሁን ለምኑት፣ ለእናንተ በመረጠላችሁ ነገር ተደሰቱ፣ ከዚያም አመስግኑት!

ادعوا ربكم، واستبشروا بحسن اختياره لكم، ثم اشكروه".

Join me

https://t.me/MdJemal
41 views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 15:01:24 كان مالك بن دينار يقوم طول ليله قابضًا على لحيته، ويقول: «يا رب قد علمت ساكن الجنة من ساكن النار، ففي أي الدارين منزل مالك».

منقل
72 views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 12:10:23 #ደስታ #السعادة


ሰኣዳህ የሚለው የአረብኛ ቃል  ደስታ፣ እድለኛ መሆን፣ ደህንነት፣ መባረክ ....የመሳሰሉትን ትርጉሞች ይይዛል።

የሰው ልጆች በህይወታቸው ውስጥ በምድር ላይም ሲኖሩም ሆነ በመጭው አለም  ከሚያስፈልጓቸው  ውድ ነገሮች አንዱ  #ደስታንናስኬትን መጎናፀፍ ነው። ይህን ትልቅ ፀጋ አላህ ሱወ " ስራን ከማሳመር ጋር" አቆራኝቶታል።

" ربط السعادة مع اصلاح العمل"     



{ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ}

" ከወወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡"
[ሱረቱ አል-ነሕል: 97]

Join me

https://t.me/MdJemal
23 views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ