2023-02-26 07:07:19
#ዚክር
አላህን በማንኛውም ሁኔታ እናወድሰው!
አላህን ከማስታወስ አለማዊ ነገሮች ሊያዘናጉን አይገባም። የቂያማ ቀን ልቦች ሁሉ በሚፈሩበት ሰአት ከፍርሃት የሚድኑት አላህን በዱንያ ላይ በብዛት የሚያወድሱ ሰዎች ናቸው።
አላህ ሱወ እንድህ ይላል፦
{ رِجَالٌ لَّا تُلْهِيهِمْ تِجَارَةٌ وَلَا بَيْعٌ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَإِقَامِ الصَّلَاةِ وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ ۙ يَخَافُونَ يَوْمًا تَتَقَلَّبُ فِيهِ الْقُلُوبُ وَالْأَبْصَارُ }
"አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የኾኑ ሰዎች (ያጠሩታል)፡፡"
[ሱረት አል-ኑር: 37]
من أسباب الأمان يوم القيامة: الخوف من الله تعالى في الدنيا، { يَخَافُونَ يَوْمًا تَتَقَلَّبُ فِيهِ الْقُلُوبُ وَالْأَبْصَارُ }
قال ابن عقيل الظاهري:-
''وأخذت على نفسي أن لا أجعل في حياتي لحظة صمتٍ.. ماشيا، ومنتظرًا وراكبًا ... إما مستمعًا تلاوة وإما ذاكرًا لله ومسبحًا وحافظت على ذكر الله؛ فأثمر كل ذلك سعة صدر وبسطة رزق، ونشاطًا ورأيت الفرق الشاسع بين هذه الحياة وحياة الغفلة واللهو.. ''
فلنعمل بها.
(منقل)
ኢብኑ ዐቂል አዟሂርይ እንድህ ይላል፦
"በህይወት ዘመኔ ውስጥ ጊዜየን ዝም ብየ
የማባክን አልነበረም።እየሄድኩም፣ በመጓጓዣም ላይ ሁኘም፣ አንድ ነገር እየጠበቅኩም..... ቁርአን እየሰማሁ፣ ዘወትር በዚክር ላይ ሁኘ እንጅ አላሳልፍም ነበር! በዚህም ላይ ዘወተርኩ። ይህ ስራየም ፍሬ አፈራ! ልቤም ሰፋ ፣ ርዝቄም ጨመረ! በኢባዳየ ነሿጧ ( መነቃቃት) አገኘሁ።ጊዜን በኢባዳ የማሳለፍንና ፣ በመዘናጋትና ለግጦ (ለህው) መካከል ያለውን ረጅም ርቀት ተገነዘብኩ።"
እንተግብረው! የሁለት ሀገር ስኬት እናገኛለን!
የካቲት 19/2015 E.C
Join me
https://t.me/MdJemal
21 viewsedited 04:07