Get Mystery Box with random crypto!

#ዳእዋ_ቲቪን እንገዝ በደ/ር   ሸህ ሙሀመድ ሀሚድን መሪነት የተቋቋመው የዳእዋ ቲቪ  | Fezekir _ فَذَكِّرْ

#ዳእዋ_ቲቪን እንገዝ


በደ/ር   ሸህ ሙሀመድ ሀሚድን መሪነት የተቋቋመው የዳእዋ ቲቪ  በዛሬው እለት በደሴ ከተማ ቅርንጫፍ ቢሮ ከፍቷል! ለአካባቢው ማህበረሰብ የትውውቅና ድጋፍ ኘሮግራም በወሎ ባህል አምባ አካሂዷል።

የሰው ልጆችን ወደ ቀጥተኛው የህይወት ጎዳና እንድመጡ ከመጥራት የበለጠ ያማረ ጥሪ የለም። ዳእዋ  የነብያትና ተከታዮቻቸው መንገድ ነው። ኢብኑል ቀይም እንዳሉት ሰዎችን  ወደ ድን መጥራት  የአላህ ባሮች ትልቁ ደረጃ ነው ብለዋል።

አላህ ሱወ በተከበረው ቃሉ እንድህ ይላል:

{ وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ }

" ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?"
[ سورة فصّلة : 33]  
አቡ አብደላህ
12/6/2012 E.C

Join me
https://t.me/MdJemal