Get Mystery Box with random crypto!

Fezekir _ فَذَكِّرْ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mdjemal — Fezekir _ فَذَكِّرْ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ mdjemal — Fezekir _ فَذَكِّرْ
የሰርጥ አድራሻ: @mdjemal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-11-17 12:54:46
27 views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 12:24:47 #Hijab_ሒጃብ

ለሙስሊም ሴቶች ሒጃብ መልበስ ከኢስላማዊ ግደታዎች ውስጥ አንዱ ተግባር ነው።ነገር ግን ቅን ባልሆኑ ፖለቲከኞችና አመራሮች ምክንያት በሚደርስ እንቅፋት ሙስሊም ሴቶች ላይ በትምህርት ቤት ውስጥ ሂጃብ ለብሳችሁ አትማሩም በማለት ብዙ ጊዜ በደልና መጉላላት ይደርስባቸዋል። ይህን ሁሉ ውጣውረድ እንኳ ተቋቁመውም ተምረው በሀገሪቱ መስሪያ ቤቶች ስራ ለመቀጠር ሲሞክሩ ደግሞ ሂጃባችሁን አውልቁ የሚሉ መስሪያ ቤቶች ብዙ ናቸው። በተለይ #የኢትዮጵያአየር መንገድ ብዙሀነትን በሚገፋ የአንድን ህዝብ ባህልና አለባበስ ብቻ ካለበሳችሁ ከስራ ቅጥር አግዳለሁ እያለ 8 ሂጃብ ለባሽ ሙስሊም እህቶቻችን እያጉላላ ነው።

ለመሆኑ አየር መንገዱ የሶማሌውን፣ የአፋሩን፣ የደቡቡን፣የኦሮምውን ....አለባበስና ባህል መቸ ነው የሚያከብረው?
//
አለባበስን በተመለከተ ሀይማኖታችን የሚያዘንን እንፈፅማለን። አላህ ሱወ በተከበረው ቁርአኑ ስለ ሴቶች አለባበስ እንድህ ይላል:

" አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡"

ትምህርት ተምረን ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ መስሪያ ቤቶች ተወዳድረን ስራ የመቀጠር መብታችን ይከበር።

#Ethiopian_airline #Respectmuslimwomens'_right!
29 viewsedited  09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 11:10:03 ነብዩ ሙሐመድ ﷺ

ጌታቻው በሰማይ ቀበሌ ያናገራቸው፣
ድንጋይ ሰላምታ ያቀረበላቸው፣
የዛፍ ግንድ ያለቀሰላቸው፣
ደመናው ያጠለላቸው፣
ከጣቶቻቸው መሀል ውሃ የፈለቀላቸው፣
ጨረቃ የተሰነጠቀችላቸው፣
ከቀብር መጀመሪያ የሚነሱ፣
በጀነትየመጀመሪያ አሸማጋይ፣
በመጀመሪያ የጀነትን በር ከፋች፣
የታላቅ ስነምግባር በላቤት፣
የፍጥረታት ሁሉ አለቃ፣
ምድርን በፍትህና እኩልነት እንድትበራ ያደረጉ መሪ፣

የአላህ ሰላምና ደህንነት በእርስዎ ላይ ይሁን።

  اللهم صل على محمد وعلى آل محمد، كما صليت على إبراهيم، وعلى آل إبراهيم، إنك حميد مجيد

ጆይን

https://t.me/MdJemal
35 views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 10:58:22
36 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 10:48:50 #ኃጢአትን እንራቅ!

أن المعصية  تورث الذل ولابد، فإن العز كل العز في طاعة الله، قال تعالى ...{  مَن كَانَ يُرِيدُ الْعِزَّةَ فَلِلَّهِ الْعِزَّةُ جَمِيعًا ۚ }
أي فليطلبها بطاعة الله، فإنه لايجدها إلا في طاعة الله.

" ማሸነፍን የሚፈልግ የኾነ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው፤ (እርሱን በመግገዛት ይፈልገው)፡፡  [ሱረቱ አል-ፈጢር : 10]

وكان من دعاء بعض السلف: اللهم أعزني بطاعتك، ولا تذلني بمعصيتك.

الداء والدواء لبن القيم.

https://t.me/MdJemal
13 views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 11:04:34 #الرفق في الدعوة



الداعي:  "أن يكون رفيقا في دعوته ليكون أدعى إلى القبول، فقد قيل: إن المأمون وعظه واعظ، فعنف في القول، فقال له: يا رجل.
ارفق، فقد بعث الله من هو خير منك إلى من هو شر مني، وأمر بالرفق فقال: {فقولا له قولا لينا لعله يتذكر أو يخشى} [طه: 44].

فتح المنعم شرح صحيح مسلم



#በዳእዋ ላይ እዝነትና መለሳለስ ተገቢ ነው!
=============================

"አንድ ዳዒ የሰዉ ልጆችን ወደ እ ስልምና ሲጣራ ጥሪው ተቀባይነት እንድኖረው በእዝነት እንድሆን ታዟል። በአንድ ወቅት ኸሊፋው መእሙንን ጋር አንድ ሰው መጣና በቁጣና በስድብ መንፈስ መከረው። እሱም እንድህ አለው " አላህ ከአንተ የተሻለውን ሰው (ሙሳን) ከኔ በከፋው ሰው (ፊርዐውን) ላይ ሲልክ እንኳ ጥሪውን በእዝነት እድያደርግ አዞታል" አለው። የሚከተለውንም አንቀፅ አነበበት:

{ فَقُولَا لَهُ قَوْلًا لَّيِّنًا لَّعَلَّهُ يَتَذَكَّرُ أَوْ يَخْشَىٰ}

«እርሱም ይገሰጽ ወይም ይፈራ ዘንድ፤ ለእርሱ ልዝብን ቃል ተናገሩት፡፡»  [ሱረቱ ጧሀ:44]

⊰━━━━━━⊱

           Join

https://t.me/MdJemal
39 viewsedited  08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 10:33:14 #ስማችን!!

ሙስሊሞች በዚህ ምድር ላይ ስንኖር  ሀይማኖታዊ መርህና አላማ አለን። በስም አወጣጥ ላይ እንኳ  ሳይቀር እስላማዊ ምልከታን እንከተላለን። ለዚያም ነው ነብዩ ሶዐወ በሀድሳቸው ከስሞች ሁሉ በላጩን እንድህ በማለት የገለፁት :

رواه الإمام مسلم في صحيحه (2132) من حديث ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( إِنَّ أَحَبَّ أَسْمَائِكُمْ إِلَى اللَّهِ عَبْدُ اللَّهِ وَعَبْدُ الرَّحْمَنِ ) 

"አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስሞች አብዱላህና አብዱረህማን ናቸው።"
በጣም የተጠሉ ስሞች ደግሞ መራራ፣ ሀርብ ....የመሳሰሉትን ይይዛል።

በኢስላማዊ ስም መጠራት ሀይማኖታዊ መሰረት ያለው ሲሆን   ልጀን የግድ  ቶላ፣ ጫልቱ፣ዋቁ፣ ከበደ፣ አስቴር፣ታደሰ... እያልኩ እንድጠራ ማንም ሊየስገድደኝ ወይም ሊመርጥልኝ አይገባም። አይችልምም።

ሀይማኖታችን ለተከታዩ የሚያስተላልፈው መልእክት ቢኖር ድነል  ኢስላም  ከሁሉም ነገር በላይ ነው። ከሀገር፣ ብሄር፣  ከእናት ልጅና አባትም ጭምር። እነዚህ ተወዳጅ ነገሮች ከኢስላማዊ መርህ ጋር ከተጋጩ ሀይማኖት ይቀደማል። ለውድድርና ንፅፅርም ፈፅሞ አይቀርቡም።

አላህ እንድህ ይላል:


قُلْ إِن كَانَ آبَاؤُكُمْ وَأَبْنَاؤُكُمْ وَإِخْوَانُكُمْ وَأَزْوَاجُكُمْ وَعَشِيرَتُكُمْ وَأَمْوَالٌ اقْتَرَفْتُمُوهَا وَتِجَارَةٌ تَخْشَوْنَ كَسَادَهَا وَمَسَاكِنُ تَرْضَوْنَهَا أَحَبَّ إِلَيْكُم مِّنَ اللَّهِ .....

«አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛው በርሱ መንገድም ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ እንደኾኑ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ» በላቸው፡፡
[ሱረቱ አል-ተውባህ: 24

{ لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ}

" በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡"
[ሱረቱ አል-ሙጀድላህ :  22]

አንዳንድ  ሰዎች አካላቸው ገዝፎ አስተሳሰባቸው  የወረደ ሲሆን ለውድድር የማይቀርብን ነገር ጭራሽ አስበልጠው ማየታቸው ሳያንስ የሌሎችን መብት ማሳነስና ማጥላላታቸው  ባልተገባ ነበር።

"ያላዋቂ ሳሚ  ን.. ጥ ይለቀልቃል።"

ربيع الأول:29,1444
          ጥቅምት 15/2015 E.c
                   كتبه أبو عبد الله محمد

⊰━━━━━━⊱
          
             
https://t.me/MdJemal
69 viewsedited  07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 09:06:50 #የጀነት_ዛፍ

የአላህ መልእከተኛ ሶዐወ ስለ ጀነት ዛፎች በከፊል ሲገልፁ ልቦች በናፍቆት ወደ ጀነት እንድበሩ ያደርጋል።
የጀነት ዛፍ ግንዱ (ሳቁ) የወርቅ ነው።


وأشجار الجنة ساقها من ذهب كما في الحديث الآتي :

 
عن أبي هريرة رضي الله عنه أنَّ النَّبِيِّ   صلى الله عليه وسلم قَالَ: مَا فِي الْجَنَّةِ شَجَرَةٌ إِلَّا وَسَاقُهَا مِنْ ذَهَبٍ.
حدث صحيح...رواه الترمذي


ነብዩ እንድህ ብለዋል:
አቡሁረይረተ ረ.ዐ ከመልክተኛ ሶዐወ ይዘው እንደዘገቡት:
" በጀነት ውስጥ ዛፍ የለም ግንዱ የወርቅ ቢሆን እንጅ"

⊰━━━━━━⊱
             
              
https://t.me/MdJemal
56 viewsedited  06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 17:06:27 #አላህን_መታዘዝ

በምድር ላይ የተፈጠርንበት ዋና አላማ አላህን መገዛት ሲሆን እሱን የምንገዛበት መንገድ የአላህንና መልክተኛውን ትዛዝ በተገቢው መንገድ በመፈፀም ነው።

አላህና መልክተኛውን ስንታዘዝን በምድር ላይ የመኖራችንን አላማ እንፈፅማለን።

አላህ ባሪያውን መውደዱን ከሚገልፅባቸው ምልክቶች አንዱ ለትዕዛዞቹ መገራት ነው። (تيسر طاعة الله) ይህም ተግባር ታላቅ ስኬትን (እድልን) ያጎናፅፈናል።

አላህ ሱ.ዐ እንድህ ይላል:

{ وَمَنْ يُطِعِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ فَازَ فَوْزًا عَظِيمًا}
(وَمَنْ يُطِعْ اللَّهَ وَرَسُولَهُ) فيعمل بما أمره به وينتهي عما نهاه
(فَقَدْ فَازَ فَوْزًا عَظِيمًا) يقول فقد ظفر بالكرامة العظمى من الله


"አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ፡፡"
[ሱረቱ አል- አሕዛብ: 71]

⊰━━━━━━⊱
             

https://t.me/MdJemal
85 viewsedited  14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 22:32:35 #ነብዩ ለምን ተላኩ?
======================

አላህ ሱወ ነብዩ #ሙሐመድን ሶዐወ ለሰው ልጆች ሁሉ መልእከተኛ አድርጎ መላኩ ለዚህ ኡማ የተሰጠ ትልቅ ፀጋ ነው። አዎ በነብዩ መላክ ምክንያት ቁርአንና ሀድስን እንድንድናውቅ፣ ነፍሳችንን ከሽርክና መጥፎ ባህሪ እንድትፀዳና በብእር መፃፍን እንድንማር የኢስላምን ጎዳና አሳይተውን አልፈዋል።


አላህ ሱወ ነብዩን ነብይ አድርጎ በመላኩ እንድህ ሲል ይመፃደቃል:-

{ هُوَ الَّذِي بَعَثَ فِي الْأُمِّيِّينَ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِهِ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا مِن قَبْلُ لَفِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ }


{ እርሱ ያ በመሃይሞቹ ውስጥ አንቀጾቹን (ቁርኣንን) በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፣ (ከማጋራት) የሚያጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልክተኛ (ሙሐመድን) ከእነርሱው ውስጥ የላከ ነው፡፡ እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነበሩ፡፡}
[ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 2]

⊰━━━━━━⊱

አንቀፁ በሚከተሉት ሀሳቦች ላይ ያተኩራል።

ሰዎችን የሚያንፅ(ተርቢያ) የሚያደርግ ዓሊም (ዳኢ ) እውቀትን ከተግባር ጋር መፈፀም አለበት!
ኢስላም ከሚያተኩርባቸው ተግባራት አንዱ ነፍስን ማጥራት (ተዝኪየቱ ነፍስ) ሲሆን አስተሳሰባዊ (አቂዳን) እና ስነምግባርንም ያካትታል።
ወህይን (መለኮታዊ ራእይን) ለሰው ልጆች ሁሉ በማድረስ የታዘዝን ሲሆን ነፍሳችን በማጥራት መጀመር እንዳለብን ይህ የቁርአን አንቀፅ ያስገነዝበናል።

27/1/2015 E.c


https://t.me/MdJemal
4 viewsedited  19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ