Get Mystery Box with random crypto!

#ስማችን!! ሙስሊሞች በዚህ ምድር ላይ ስንኖር  ሀይማኖታዊ መርህና አላማ አለን። በስም አወጣጥ | Fezekir _ فَذَكِّرْ

#ስማችን!!

ሙስሊሞች በዚህ ምድር ላይ ስንኖር  ሀይማኖታዊ መርህና አላማ አለን። በስም አወጣጥ ላይ እንኳ  ሳይቀር እስላማዊ ምልከታን እንከተላለን። ለዚያም ነው ነብዩ ሶዐወ በሀድሳቸው ከስሞች ሁሉ በላጩን እንድህ በማለት የገለፁት :

رواه الإمام مسلم في صحيحه (2132) من حديث ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( إِنَّ أَحَبَّ أَسْمَائِكُمْ إِلَى اللَّهِ عَبْدُ اللَّهِ وَعَبْدُ الرَّحْمَنِ ) 

"አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስሞች አብዱላህና አብዱረህማን ናቸው።"
በጣም የተጠሉ ስሞች ደግሞ መራራ፣ ሀርብ ....የመሳሰሉትን ይይዛል።

በኢስላማዊ ስም መጠራት ሀይማኖታዊ መሰረት ያለው ሲሆን   ልጀን የግድ  ቶላ፣ ጫልቱ፣ዋቁ፣ ከበደ፣ አስቴር፣ታደሰ... እያልኩ እንድጠራ ማንም ሊየስገድደኝ ወይም ሊመርጥልኝ አይገባም። አይችልምም።

ሀይማኖታችን ለተከታዩ የሚያስተላልፈው መልእክት ቢኖር ድነል  ኢስላም  ከሁሉም ነገር በላይ ነው። ከሀገር፣ ብሄር፣  ከእናት ልጅና አባትም ጭምር። እነዚህ ተወዳጅ ነገሮች ከኢስላማዊ መርህ ጋር ከተጋጩ ሀይማኖት ይቀደማል። ለውድድርና ንፅፅርም ፈፅሞ አይቀርቡም።

አላህ እንድህ ይላል:


قُلْ إِن كَانَ آبَاؤُكُمْ وَأَبْنَاؤُكُمْ وَإِخْوَانُكُمْ وَأَزْوَاجُكُمْ وَعَشِيرَتُكُمْ وَأَمْوَالٌ اقْتَرَفْتُمُوهَا وَتِجَارَةٌ تَخْشَوْنَ كَسَادَهَا وَمَسَاكِنُ تَرْضَوْنَهَا أَحَبَّ إِلَيْكُم مِّنَ اللَّهِ .....

«አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸው ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛው በርሱ መንገድም ከመታገል ይበልጥ የተወደዱ እንደኾኑ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ» በላቸው፡፡
[ሱረቱ አል-ተውባህ: 24

{ لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ}

" በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡"
[ሱረቱ አል-ሙጀድላህ :  22]

አንዳንድ  ሰዎች አካላቸው ገዝፎ አስተሳሰባቸው  የወረደ ሲሆን ለውድድር የማይቀርብን ነገር ጭራሽ አስበልጠው ማየታቸው ሳያንስ የሌሎችን መብት ማሳነስና ማጥላላታቸው  ባልተገባ ነበር።

"ያላዋቂ ሳሚ  ን.. ጥ ይለቀልቃል።"

ربيع الأول:29,1444
          ጥቅምት 15/2015 E.c
                   كتبه أبو عبد الله محمد

⊰━━━━━━⊱
          
             
https://t.me/MdJemal