Get Mystery Box with random crypto!

#ነብዩ ለምን ተላኩ? ====================== አላህ ሱወ ነብዩ #ሙሐመድን ሶዐወ | Fezekir _ فَذَكِّرْ

#ነብዩ ለምን ተላኩ?
======================

አላህ ሱወ ነብዩ #ሙሐመድን ሶዐወ ለሰው ልጆች ሁሉ መልእከተኛ አድርጎ መላኩ ለዚህ ኡማ የተሰጠ ትልቅ ፀጋ ነው። አዎ በነብዩ መላክ ምክንያት ቁርአንና ሀድስን እንድንድናውቅ፣ ነፍሳችንን ከሽርክና መጥፎ ባህሪ እንድትፀዳና በብእር መፃፍን እንድንማር የኢስላምን ጎዳና አሳይተውን አልፈዋል።


አላህ ሱወ ነብዩን ነብይ አድርጎ በመላኩ እንድህ ሲል ይመፃደቃል:-

{ هُوَ الَّذِي بَعَثَ فِي الْأُمِّيِّينَ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِهِ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا مِن قَبْلُ لَفِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ }


{ እርሱ ያ በመሃይሞቹ ውስጥ አንቀጾቹን (ቁርኣንን) በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፣ (ከማጋራት) የሚያጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልክተኛ (ሙሐመድን) ከእነርሱው ውስጥ የላከ ነው፡፡ እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነበሩ፡፡}
[ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 2]

⊰━━━━━━⊱

አንቀፁ በሚከተሉት ሀሳቦች ላይ ያተኩራል።

ሰዎችን የሚያንፅ(ተርቢያ) የሚያደርግ ዓሊም (ዳኢ ) እውቀትን ከተግባር ጋር መፈፀም አለበት!
ኢስላም ከሚያተኩርባቸው ተግባራት አንዱ ነፍስን ማጥራት (ተዝኪየቱ ነፍስ) ሲሆን አስተሳሰባዊ (አቂዳን) እና ስነምግባርንም ያካትታል።
ወህይን (መለኮታዊ ራእይን) ለሰው ልጆች ሁሉ በማድረስ የታዘዝን ሲሆን ነፍሳችን በማጥራት መጀመር እንዳለብን ይህ የቁርአን አንቀፅ ያስገነዝበናል።

27/1/2015 E.c


https://t.me/MdJemal