Get Mystery Box with random crypto!

#አብደላህኢብኑሰሉል እና መሰሎቹ በሁሉም ዘመን አሉ። ≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅ ነብዩ ሶዐወ መካ ውስ | Fezekir _ فَذَكِّرْ

#አብደላህኢብኑሰሉል እና መሰሎቹ በሁሉም ዘመን አሉ።
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅

ነብዩ ሶዐወ መካ ውስጥ እያሉ በደረሰባቸው ግፍና በደል ወደ መድና ተሰደዱ! መድናም ውስጥ የነበሩት ደጋግ አንሷሮች ስደተኞችን ተቀብለው አስተናገዱ።  ነብዩንም በገንዘባቸውና በህይወታቸውም ጭምር ረዱ።  ድነልኢስላምም በመድና ምድር ማበብ ጀመረ።

ነብዩ ሶዐወ  በበኒ ሙስጦሊቅ ዘመቻ ላይ እያሉ  በአንድ አንሷርንና ሙሀጅር መካከል ጠብ ተቀሰቀሰ። ሁሉም በየ ብሄሩ መጣራት ጀመረ፣ ይህን ሲመለከቱ  ነብዩ  ሶዐወ በጣም ተቀየሙና እኔ  በመካከላችሁ እያለሁ እንድህ የመሀይ ጥሪ ትጣራላችሁ አሉ። ዘረኝነትን ተዋት እሷ ጥንብ ነች አሉና የተጣሉትን አስታረቁ።

ይህን የሰማው  አብደላህኢብኑሰሉል የተባለው በመድና የሚኖር  ሙናፊቅ  "ጠንካሮቹ ደካሞቹን ከመድና ያስወጣሉ"  ሲል ዛተ።
ከመካ የተሰደዱትን ስደተኞች ለማለት ነው።በዚህ ጊዜ ለሱና መሰሎቹ  የሚከተለው የቁርአን አንቀፅ ወረደ:-

{ يَقُولُونَ لَئِن رَّجَعْنَا إِلَى الْمَدِينَةِ لَيُخْرِجَنَّ الْأَعَزُّ مِنْهَا الْأَذَلَّ ۚ وَلِلَّهِ الْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَـٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ}

«ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከእርሷ ያወጣል» ይላሉ፡፡ አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛውና ለምእምናን ነው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም፡፡
[ሱረቱ አል-ሙናፊቁን - 8]

የኢብኑ ሰሉል መሰሎች በየትኛውም ጊዜና ቦታ አሉና አላህ በፈጠረው ምድር፣ ጠፍ የሆነን መሬት አልምተው የሚኖሩን ማህበረሰቦች መሬታችንን  ካለቃቃችሁ በሚል የዘረኝነት ጭምብል ጭፍጨፋ እየፈፀሙባቸው ነው። ጌታየ እባክህ የተንኮል ኢብኑ ሰሉሎች  በዝተዋልና እጃቸውን ያዝልን! የስራቸውን ስጣቸው።

                كتبه أبو عبد الله
              ህዳር 29/ 2015
        
      
https://t.me/MdJemal