#እስልምና_الاسلام አላህ ከዋለልን መልካም ፀጋ ሁሉ ትልቁ ውለታ ልባችንን ለኢስላም ክፍት | Fezekir _ فَذَكِّرْ
#እስልምና_الاسلام
አላህ ከዋለልን መልካም ፀጋ ሁሉ ትልቁ ውለታ ልባችንን ለኢስላም ክፍት ማድረጉ ነው!
{ فَمَن يُرِدِ اللَّهُ أَن يَهْدِيَهُ يَشْرَحْ صَدْرَهُ لِلْإِسْلَامِ }
[ አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለኢስላም ይከፍትለታል፡፡ ] ሱረቱ አል-አንዓም: 125
*****
ቀጥተኛውን #የኢስላም_መንገድ የያዘ አጓጊ ፍፃሜ ያገኛል። ምክንያቱም ትክክለኛውን የመጓዣ ፍኖት በእጁ ይዟልና። #ሰላም የሰፈነበት #ሐሴት የሞላበት ዘላለማዊ ህይወት። የአላህ ውደታና አጋርነት (ዊላየቱላህ) ሙሉ በሙሉ የሚንፀባረቅበትን ዓለም መውረስ የሚገኘው #በኢስላም ውስጥ ነው፣ በተለይ ኢስላምን ስንማረው፣ ስንተገብረውና ስንኖረውም ጭምር።
{ وَهَذَا صِرَاطُ رَبِّكَ مُسْتَقِيمًا ۗ قَدْ فَصَّلْنَا الْآيَاتِ
لِقَوْمٍيَذَّكَّرُونَ }
" ይህም (ያለህበት) ቀጥተኛ ሲኾን የጌታህ መንገድ ነው፡፡ ለሚያስታውሱ ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘርዝረናል፡፡ "
۞ لَهُمْ دَارُ السَّلَامِ عِندَ رَبِّهِمْ ۖ وَهُوَ وَلِيُّهُم بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
" ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሰላም አገር አላቸው፡፡ እርሱም (ጌታህ) ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ረዳታቸው ነው፡፡ "
[ሱረቱ አል-አንዓም:126 & 127
ከ2 አመት በፊት ፌስቡክ ላይ የፃፍኩት ነው! ሳነበው ለራሴው የኢስላምን ኒዕማ ሳስታውስ ሸር በድጋሜ አደረግኩት!
https://t.me/MdJemal