2022-09-30 20:19:59
ከሰለፎች ምርጥ አጋጣሚዎች…
አንዱ ተጠየቀ …" ለሰዎች መልካምን ነገር አውለህ ስታበቃ ውለታህን ሲረሱብህ አታዝንምን ??? "
እሱም ፦ " ሲጀመርም ምስጋናቸውን ስላልጠበቅኩ አላዝንም ። አላህ በጎ ሰሪዎችን መውደዱ ብቻ ይበቃኛል " አላቸው
•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•
የየሱፍ ወንድሞች « እኛ ለሱ ጠባቂዎች ነን» ሲሉ አባታቸው ደግም « አላህ ከጠባቂዎች ሁሉ በላጭ ነው» አላቸው
እነሱ ዩሱፍን ሲጥሉ አላህ ግን ጠባቂው ሆነ
የምንወዱትን ነገር ለአላህ አደራ ስጡ
•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•
{ ٱقْرَأْ كِتَٰبَكَ كَفَىٰ بِنَفْسِكَ ٱلْيَوْمَ عَلَيْكَ حَسِيبًۭا }
«መጽሐፍህን አንብብ፡፡ ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ በቃ» (ይባላል)፡፡
ዛሬ አንተ ስራህን ታፅፋለህ ነገ ደግሞ ያፃፍከውን ታነባልህ ። ስለዚህ ነገ በምታነበው እንድትደሰት ዛሬ የምታፅፈውን አሳመር !
•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•
ሰዎች ጠየቁት… "ሰላትህ ላይ እንዴት ቀጥ ልትል ቻልክ ???"
እሱም ፦ « አንድ ሸይኽ " አንተ ሰላትህን የተውከው ሰው ሆይ ! ያንተ መከራ እኮ ከ ኢብሊስ የበለጠ ከባድ ነው። ምክንያቱም ኢብሊስ ለአደም ሱጁድ ውረድ በተባለ ጊዜ እምቢ ሲል አንተ ደግሞ ለአደም ጌታ ሱጁድ ለማድረግ እምቢ አልክ ። እንደው በአንተና በጌታህ መካከል ምን ቢኖር ነው እርሱን መገናኘትን የጠላኸው ! ?" ብለው ሲናገሩ ሰምቼ ነው » አላቸው
•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•
አንዲት እናት 10 ልጆች ቢኖሯት አስሩንም ተንከባክባ ትይዛለች ። የሚገርመው ነገር ግን ምን አልባት 10 ልጆች አንድ እናታቸውን መንከባከብ ያቅታቸዋል ።
አላህ ወላጆቻችን ለመንከባከብ ይወፍቀን…
ከእናቱ እግር ስር ሁኖ እሷን የተንከባበከ … ከሰዎች ሁሉ በላይ ሁኖ ይኖራል።
•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•
{ وَأَدْخَلْنَٰهُ فِى رَحْمَتِنَآ ۖ إِنَّهُۥ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ }
«በችሮታችንም ውስጥ አገባነው፡፡ እርሱ ከመልካሞቹ ነውና፡፡»
ከአላህ እዝነት ድርሻህ የሚሆነው በመልካምነትህ ልክ ነው…
•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•
{ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥ نِدَآءً خَفِيًّۭا }
«ጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡»
ዱዓህን አሳንሰህ አትመልከት ። ይህ ዝቅ ያለው ድምፅ የሰማያት በሮች ተከፍተውለታል።
•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•
{ إِذْ يَقُولُ لِصَٰحِبِهِۦ لَا تَحْزَنْ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَنَا ۖ }
« ለጓደኛው አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና ባለ ጊዜ አስታውስ »
ምርጥ ጓደኝነት ማለት የዱንያን ውጣውረድ የሚያቀልልህና ወደ አላህ የሚያቀርብህ ነው።
•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•
{وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِى فَإِنَّ لَهُۥ مَعِيشَةًۭ ضَنكًۭا وَنَحْشُرُهُۥ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَعْمَىٰ}
«ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን፡፡»
ጭንቀትና ሀዘን ባጋጠመህ ጊዜ ፈጥነህ ከቁርዓን ጋር ያለህን ሁኔታ አስተካከል።
┄┉┉✽» ✿ »✽┉┉┄
t.me/+jPQLXna9F-E3ZDQ0
https://bit.ly/3PJRnHE
3.7K viewsالحب الأسود, 17:19