Get Mystery Box with random crypto!

ከሰለፎች ምርጥ አጋጣሚዎች… አንዱ ተጠየቀ …' ለሰዎች መልካምን ነገር አውለህ ስታበቃ ውለታህን | ⛤Ιѕℓαмιc нιѕтory⛤

ከሰለፎች ምርጥ አጋጣሚዎች…

አንዱ ተጠየቀ …" ለሰዎች መልካምን ነገር አውለህ ስታበቃ ውለታህን ሲረሱብህ አታዝንምን ??? "
እሱም ፦ " ሲጀመርም ምስጋናቸውን ስላልጠበቅኩ  አላዝንም ።  አላህ በጎ ሰሪዎችን መውደዱ ብቻ ይበቃኛል " አላቸው

•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•

የየሱፍ ወንድሞች « እኛ ለሱ ጠባቂዎች ነን»  ሲሉ አባታቸው ደግም « አላህ ከጠባቂዎች ሁሉ በላጭ ነው» አላቸው
እነሱ ዩሱፍን ሲጥሉ አላህ ግን ጠባቂው ሆነ
 
የምንወዱትን ነገር ለአላህ አደራ ስጡ

•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•

{ ٱقْرَأْ كِتَٰبَكَ كَفَىٰ بِنَفْسِكَ ٱلْيَوْمَ عَلَيْكَ حَسِيبًۭا }

«መጽሐፍህን አንብብ፡፡ ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ በቃ» (ይባላል)፡፡

ዛሬ አንተ ስራህን ታፅፋለህ  ነገ ደግሞ ያፃፍከውን ታነባልህ ። ስለዚህ ነገ በምታነበው እንድትደሰት ዛሬ የምታፅፈውን አሳመር !  

•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•


ሰዎች ጠየቁት… "ሰላትህ ላይ እንዴት ቀጥ ልትል ቻልክ ???"

እሱም ፦ « አንድ ሸይኽ " አንተ ሰላትህን የተውከው ሰው ሆይ ! ያንተ መከራ እኮ ከ ኢብሊስ የበለጠ ከባድ ነው። ምክንያቱም ኢብሊስ ለአደም ሱጁድ ውረድ በተባለ ጊዜ እምቢ ሲል አንተ ደግሞ ለአደም ጌታ ሱጁድ ለማድረግ እምቢ አልክ ። እንደው በአንተና በጌታህ መካከል  ምን ቢኖር ነው እርሱን መገናኘትን የጠላኸው ! ?" ብለው ሲናገሩ  ሰምቼ ነው »  አላቸው

•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•


አንዲት እናት 10 ልጆች ቢኖሯት አስሩንም ተንከባክባ ትይዛለች ። የሚገርመው ነገር ግን ምን አልባት 10 ልጆች አንድ እናታቸውን መንከባከብ ያቅታቸዋል ።

አላህ ወላጆቻችን ለመንከባከብ ይወፍቀን…

ከእናቱ እግር ስር ሁኖ እሷን የተንከባበከ … ከሰዎች ሁሉ  በላይ ሁኖ ይኖራል።

•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•

{ وَأَدْخَلْنَٰهُ فِى رَحْمَتِنَآ ۖ إِنَّهُۥ مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ }

«በችሮታችንም ውስጥ አገባነው፡፡ እርሱ ከመልካሞቹ ነውና፡፡»

ከአላህ እዝነት ድርሻህ የሚሆነው በመልካምነትህ ልክ ነው…


•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•

{ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥ نِدَآءً خَفِيًّۭا }

«ጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡»

ዱዓህን አሳንሰህ አትመልከት ። ይህ ዝቅ ያለው ድምፅ የሰማያት በሮች ተከፍተውለታል።

•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•


{ إِذْ يَقُولُ لِصَٰحِبِهِۦ لَا تَحْزَنْ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَنَا ۖ }

« ለጓደኛው አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና ባለ ጊዜ አስታውስ »

ምርጥ ጓደኝነት ማለት የዱንያን ውጣውረድ የሚያቀልልህና ወደ አላህ የሚያቀርብህ ነው።

•┈┈• ❀ ❀ •┈┈•


{وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِى فَإِنَّ لَهُۥ مَعِيشَةًۭ ضَنكًۭا وَنَحْشُرُهُۥ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَعْمَىٰ}

«ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን፡፡»

ጭንቀትና ሀዘን ባጋጠመህ ጊዜ ፈጥነህ  ከቁርዓን ጋር ያለህን ሁኔታ አስተካከል።


┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
t.me/+jPQLXna9F-E3ZDQ0
https://bit.ly/3PJRnHE