Get Mystery Box with random crypto!

የአገር መሪ ናቸው። ፍትህን ያነገሱ የሐቅ ሰው። በእውነት ብርሀን ስር የዳኙ መሪ። አንድ ምሽት ላ | ⛤Ιѕℓαмιc нιѕтory⛤

የአገር መሪ ናቸው። ፍትህን ያነገሱ የሐቅ ሰው። በእውነት ብርሀን ስር የዳኙ መሪ። አንድ ምሽት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው በሻማ ብርሃን እየታገዙ የአስተዳደራቸውን የግምጃ ቤት የገቢና ወጪ ሂሳብ በመስራት ላይ ናቸው። በር ተንኳኳ። እሳቸውን ለማነጋገር የሚፈልጉ ሁለት ሰዎች ነበሩ። በአስተዳደሩ ስልጣን ውስጥ ሁነኛ ቦታ የማግኘት ምኞት ነበራቸው። የመጡትም ይህንን ህልማቸውን ያሳካልናል ያሉትን አንድ ሃሳብ ይዘው ነው። ይህንን ሃሳባቸውን በመቀበል በመንግስታቸው ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የሚስጧቸው ከሆነ እነርሱ በፊናቸው ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ቃል እንደሚገቡ በመግለፅ ለመደራደር ነበር። 

   ሰዎቹ እንደተቀመጡ የበራው ሻማ ጠፋና ሌላ ሻማ ተለኮሰ። በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሰዎች በመገረም ሰሜት እርስ በእርሳቸው ተያዩ።  ምክንያቱን ለማወቅ የበለጠ ጉጉት ያደረበት አንደኛው ሰው የመጣበትን ጉዳይ ከማንሳቱ ቀደም ብሎ የሚበራውን ሻማ አጥፍተው ሌላ ሻማ የለኮሱበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠየቀ። እሳቸውም "እናንተ ወደቤት ስትገቡ ይበራ የነበረውን ሻማ ከመንግስት ግምጃ ቤት ገንዘብ ወጪ ተደርጎ የተገዛ የህዝብ ሀብት ነው። ይህ የምትመለከቱትን የግምጃ ቤት የወጪና ገቢ ሂሳብ ለመስራት ስል ነበር ያበራሁት አሁን እናንተ የመጣችሁበት ጉዳይ የግል ጉዳያችሁ በመሆኑ የበፊቱን ሻማ በማጥፋት ይህንን ከራሴ ገንዘብ ወጪ አድርጌ የገዛሁትን ሻማ ለኮስኩት" በማለት ለቀረበው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጡ። በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሰዎች ቀደም ሲል እንዳደረጉት እርስ በእርሳቸው ተያዩ የመጡበትን ዓላማ ማንሳት ቀርቶ አንዲት ሌላ ቃል እንኳ መተንፈስ ተሰኗቸው ወጥተው ሄዱ። ሰውየው አሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ነበሩ። አላህ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው።

   ኢስላም አለምን ሲመራ እንዲህ ነበር ፍትህ የነገሰው

╔════ ════╗
             ɪsʟamic history
             ɪsʟᴀᴍɪᴄ history
╚════ ════╝

•┈•❈••✦✾ቴሌግራማችንን ✾✦••❈•┈•
      Join & share
https://t.me/+jPQLXna9F-E3ZDQ0
✿✶┈┈┈┈•✶✶✾✶✶•┈┈┈┈✶✿