Get Mystery Box with random crypto!

ውዷ እህቴ ለትዳርሽ ብቁ ነሽን?               ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ግዜ በእጅሽ | ⛤Ιѕℓαмιc нιѕтory⛤

ውዷ እህቴ ለትዳርሽ ብቁ ነሽን?
             
ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ግዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ፊቱ ላይ የተመለከትሽውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ
{ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታበይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

ባለቤትሽ በተቆጣ ግዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት ከሆነ፣ድምፅሽን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

ከባለቤትሽ አጠገበ በተቀመጥሽ ግጔዜ ጠረንሽ ጥሩ ካልሆነ፣የልብስሽን ንፅህና ካልጠበቅሽ፣እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

ከሱ ጋ በተጣላሽ ወቅት ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የሱን ቤተሰቦች መልካምን በማድረግ የማትንከባከቢ ከሆነ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

አላህን በመታዘዝ ላይ የማታበረታቺው ከሆነ፣ ክልክል ነገራቶችን እንዲተው የማታደርጊ እና ወደ ተውበት የማትገፋፊው ከሆንሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

ሲራ TUBE
t.me/+ab1ZviUdLYExZWJk
t.me/+ab1ZviUdLYExZWJk