Get Mystery Box with random crypto!

ተባበሯቸው! «بسم الله الرحمن الرحيم እነሆ ተጀመረ! ለኢብኑል ጀዘሪይ የቁርአንና | ⛤Ιѕℓαмιc нιѕтory⛤

ተባበሯቸው!

«بسم الله الرحمن الرحيم
እነሆ ተጀመረ!

ለኢብኑል ጀዘሪይ የቁርአንና የዲን ትምህርት ማዕከል ግንባታ የሚሆን የቦታ ግዢ እንቅስቃሴ ከዛሬው ቀን ጀምሮ በይፋ መጀመሩን እያበሰርን አቅማችን በፈቀደው ልክ የዚህ ዘመን ተሻጋሪ ፕሮጀክት አካል እንድንሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ማዕከሉ አሁን ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በቁርአን ሒፍዝና በተለያዩ የዲን ትምህርቶች በኢስላማዊ ተርቢያ እያስተማረ ይገኛል።


ቁርአንን መሰጠት ከአላህ የሆነ ስጦታ እንደመሆኑ መጠን በዚህ ላይ መሳተፍ በራሱ ትልቅ የሆነ እድል ነው።

አላህ እንዲህ ይላል፦

ثُمَّ أَوْرَثْنَا الْكِتَابَ الَّذِينَ اصْطَفَيْنَا مِنْ عِبَادِنَا ۖ فَمِنْهُمْ ظَالِمٌ لِّنَفْسِهِ وَمِنْهُم مُّقْتَصِدٌ وَمِنْهُمْ سَابِقٌ بِالْخَيْرَاتِ بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَضْلُ الْكَبِيرُ

ከዚያም እነዚያን ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው፡፡ ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አልለ፡፡ ከእነርሱም መካከለኛ አልለ፡፡ ከእነሱም በአላህ ፈቃድ በበጎ ሥራዎች ቀዳሚ አልለ፡፡ ያ (ማውረስ)፤ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው፡፡

የአላህ መልዕክተኛም(ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦

خيركم من تعلم القرآن وعلمه
ከእናንተ በላጫችሁ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ነው።

መስጂዳችን የራሱ የሆነ መድረሳ የሌለው እንደመሆኑ ከተማሪው ብዛት የተነሳ በወንዶችም በሴቶችም በኩል በአግባቡ ሰላት ለመስገድ እስከመቸገር ድረስ አድርሶናል።መስጂዱ ሲጀመርም ጠባብና ምንም አይነት የግቢ ቦታ የሌለው እንደመሆኑ ከፍተኛ የሆነ መጨናነቅ አለ።በዛ ላይ አካባቢው ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሙስሊም ማኅበረሰብ የሚገኝበት ሲሆን በተለይ ረመዳን ሲመጣ ከመስጂዱ አቅም በላይ የሚሆንበት ሁኔታ ዘወትር የሚስተዋል ተጨባጭ ነው።

ይህ ከፍተኛ የቦታ ጥበት ባለበት ሁኔታ ከመስጂዱ ጎን ያለ 200ካሜ የግለሰብ ቦታ አስገዳጅ በሆነ ምክንያት ለሽያጭ ቀርቧል።ያም ብቻ ሳይሆን ሽያጩ በአስቸኳይ መፈፀም የግድ የሆነበት ሁኔታ ተፈጥሯል።በመሆኑም በጥቂት ቀናት ውስጥ ይህን ግዢ ማሳካት ካልቻልን ቦታውን ዳግም ልናገኘው የማንችልበት ሁኔታ ከፍ ያለ ነው።አሁን ላይ ያሉብን መጠነ ሰፊ ችግሮችም ተባብሰው የሚቀጥሉ ይሆናሉ።እንዳጋጣሚ ሆኖ ከዚህ ቦታ ሌላ መስጂዱ ዙሪያ ምንም አይነት አማራጭ ቦታ አለመኖሩ ደግሞ የዚህን ቦታ አስፈላጊነት ይበልጥ የግድ ያደርገዋል።

ስለሆነም የመጀመሪያው አላማችን የቦታውን ግዢ ማሳካት ነውና የሚቻለንን ሁሉ ማድረግ የግድ ይለናል።እናም እንደየ አቅማችን አላህ ያግራልንን ያህል አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንበርታ።

ከራሳችን ባለፈ ሌሎችን በማሳተፍም ከሰጪዎቹ እኩል ምንዳን እናግኝ።ይህ እጅግ ብልህ የሆኑ ሰዎች ንግድ ሲሆን ትርፋማነቱም የተረጋገጠ ነው።

ኢብኑል ጀዘሪይ የቁርአን ትምህርት ማዕከል ከኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር ቅርንጫፎች አንዱ ሲሆን ማኅበረሰቡን በተስተካከለ ዐቂዳና በመልካም ስነ ምግባር ለመቅረፅ ሌት ተቀን እየሰራ ያለ ማዕከል ነው።አድራሻውም ጀሞ ከመስታወት ፋብሪካ ጀርባ ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  "ከራህማ መስጂድ" ጎን ነው።
=============


ኢብኑል ጀዘሪይ የቁርአን ትምህርት ማዕከል
1000492485687 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

[የቦታው የሽያጭ ዋጋ፦4,200,000ብር]

፨፠ ገቢ ያደረጋችሁበትን ደረሰኝ ወይም Screen shot በሚከተሉት አማራጮች ያድርሱን፦

https://t.me/+suWUfRlR1xJjNTg0
@mirajnesru
@Nesraahmed
@abdellah638

0937213444»